Sunday, January 17, 2016

Home » ጦማሮች፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም... » “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ) “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ) ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

“ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” በሚል ርእስ ይህች ጦማር የፈለቀችበት ዘመን፤ ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገር የሚያዋስኗት ድንበሮችና፤ በውስጥም ዜጎቿ ተከባብረውና ተዋደው የሚኖሩባቸው ወሰኖች የፈረሱበት፤ ረዥም ዘመን የኖሩ ዛፎች የተጨፈጨቡት፤ መልሰው እንዳያቆጠቁጡ፤ (እንዳያንሰራሩ) ግንዶች ከነስራቸው የነገሉበት ዘመን ነው። ለ 25 ዓመት ኢትዮጵያን የገዛው የወያኔ መንግሥት፤ አገሪቱን ከተቆጣጠረበት ቅጽበት ጀምሮ በቅርብ የሚታየው ከሩቅ የሚሰማው መፍረስና መገሰስ ቢሆንም፤ በየዘመኑ ድንበር እየጣሱ ከመጡ ወራሪዎች ጋራ ለዳር ድንበር ስትፋለም የኖረች ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተውህዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ወቅት ምን ትላለች?የሚለው ጥያቄ በኢትዮጵያውያን መካከል ብቻ ሳይወሰን፤ የኢትዮጵያን ታሪክ በሚያውቁ በውጭ አገር ሊቃውንት መካከልም መነጋገሪያ ሆኗል።http://ecadforum.com/Amharic/archives/16098/
Ethiopian Border Affairs Committee
በዚህ ወቅት የፈለቀችው ይህች ጦማር፤ ይህች ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ስለ ድንበር የተሸከመችው ሀሳብ የራሴ ፈጠራ አይደለም። በሱባዔ፣ በህልም የተከሰተልኝ አይደለም።አልበቃሁምና መንፈስ ቅዱስ ገለጾልኝም አይደለም። የቅኔ ችሎታቸውን ከመንደር ቧልትና ነገረ ዘርቅ ያላቀቁ ሊቃውንት የህዝቡን አሉታ እየተመለከቱ፤ በሰረዙ ቅኔያቸው ሲዘርፉበት የተማርኩት ነው። የትርጓሜ መምህራንም ባንድምታ ትርጉማቸው የሚያመሠጥሩት፤ ለእለታዊ ጥቅም ተልእኳቸውን ያልሸጡ ቀሳውስትም በጸሎታቸው ሲገልጹት የሰማሁትና “ድንበር ሲፈርስ መሐሉ ዳር ይሆናል፤ የዛፍ ጫፉ ሲጨፈጨፍ ግንዱ ጫፍ ይሆናል”እያሉ የመንደር አዛውንትም ሲናገሩ የሰማሁትን ነው። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]1 ድንበር “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ nigatuasteraye@gmail.com ጥር ፳፻፰ ዓ.ም. ማሳሰቢያ ስለኢትዮጵያ ድንበር መፍረስ፤ መገሰስና መጠገን በተደረጉበት ዘመናት ሁሉ የነበረች አሁንም ታፍና በመታዘብ ላይ ያለች፤ ወደፊትም የምትኖር ይህች ጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፤ አሁን ህዝቧ ስለሚነጋገርበት ስለ ድንበር ምን ትላለች? የሚለውን ለመዳሰስ ይህችን ጦማር ሳዘጋጅ በውስጧ የተሸከመቻቸውን ሀሳቦች በተጻፉባቸው ቋንቋዎች እንዳሉ አቅርቤያቸዋለሁ። ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰነዘረውን አፈና ለመከላከል የጠቀስኳቸውን ሀሳቦች በተጻፉባቸው ቋንቋዎች እንዳሉ በማቅረቤ (ግእዙን ግን ትርጉሜዋለሁ) ይቅርታ በመጠየቅ ያጎደልኩትን እየሞላችሁ፤ የተሳሳትኩትን እያረማችሁ ታነቧት ዘንድ በታላቅ ትህትና አቀረብኩላችሁ።
መግቢያ “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” በሚል ርእስ ይህች ጦማር የፈለቀችበት ዘመን፤ ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገር የሚያዋስኗት ድንበሮችና፤ በውስጥም ዜጎቿ ተከባብረውና ተዋደው የሚኖሩባቸው ወሰኖች የፈረሱበት፤ ረዥም ዘመን የኖሩ ዛፎች የተጨፈጨቡት፤ መልሰው እንዳያቆጠቁጡ፤ (እንዳያንሰራሩ) ግንዶች ከነስራቸው የነገሉበት ዘመን ነው። ለ 25 ዓመት ኢትዮጵያን የገዛው የወያኔ መንግሥት፤ አገሪቱን ከተቆጣጠረበት ቅጽበት ጀምሮ በቅርብ የሚታየው ከሩቅ የሚሰማው መፍረስና መገሰስ ቢሆንም፤ በየዘመኑ ድንበር እየጣሱ ከመጡ ወራሪዎች ጋራ ለዳር ድንበር ስትፋለም የኖረች ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተውህዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ወቅት ምን ትላለች? የሚለው ጥያቄ በኢትዮጵያውያን መካከል ብቻ ሳይወሰን፤ የኢትዮጵያን ታሪክ በሚያውቁ በውጭ አገር ሊቃውንት መካከልም መነጋገሪያ ሆኗል። በዚህ ወቅት የፈለቀችው ይህች ጦማር፤ ይህች ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ስለ ድንበር የተሸከመችው ሀሳብ የራሴ ፈጠራ አይደለም። በሱባዔ፣ በህልም የተከሰተልኝ አይደለም።አልበቃሁምና መንፈስ ቅዱስ ገለጾልኝም አይደለም። የቅኔ ችሎታቸውን ከመንደር ቧልትና ነገረ ዘርቅ ያላቀቁ ሊቃውንት የህዝቡን አሉታ እየተመለከቱ፤ በሰረዙ ቅኔያቸው ሲዘርፉበት የተማርኩት ነው። የትርጓሜ መምህራንም ባንድምታ ትርጉማቸው የሚያመሠጥሩት፤ ለእለታዊ ጥቅም ተልእኳቸውን ያልሸጡ ቀሳውስትም በጸሎታቸው ሲገልጹት የሰማሁትና “ድንበር ሲፈርስ መሐሉ ዳር ይሆናል፤ የዛፍ ጫፉ ሲጨፈጨፍ ግንዱ ጫፍ ይሆናል”እያሉ የመንደር አዛውንትም ሲናገሩ የሰማሁትን ነው። ክርስቶስ “እውነት እልሀለሁ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውን እንመሰክራለን” (ዮሐንስ ም 3፡ ቁ 11)። እንዳለው፦ ከአባቶቻችን የተማርንውን፣ የምናውቀውንና ያየነውን ባባቶቻችንም የተጻፈውን ከውጭ ከተሸከምነው ለይተን ብንናገር፤ ወይም ከውጭ በሰማነው ባንሸፍነው፤ በወያኔ ፖለቲካ የተናጋቸውን ኢትዮጵያን፤ በነ ገብረ ኪዳን ደስታ፣ ስብሐት ነጋና አባይ ፀሐዬ የተናወጠችውን ቤተ ክህነታችንን፤ በሰይጣን ውሸት ከመበከሏ በፊት የነበረችውን ገነት ባደረግናቸው ነበር። ነበር ከሚለው ከጸጸት ንግግር ተላቀን ዛሬም አለ! ማለት እንችል ዘንድ ከዚህ በታች በዘረዘርኴቸው፦ o ፩ኛ ኢትዮጵያዊነት የተመሰረተበት ስርዓተ አምልኮ o ፪ኛ የኦሪቱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ስለ ድንበር ምን ይላሉ? o ፫ኛ ድንበር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓተ ጸሎት 2 o ፬ኛ ድንበር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክና ባህል በሚሉ አንቀጾች ያዘጋጀኋትን ይህችን ጦማር በስርዓተ አምልኳችን እጀምራለሁ። ፩ኛ:- ኢትዮጵያዊነት የተመሰረተበት ስርዓተ አምልኮ ኢትዮጵያዊ ስርዓተ አምልኮ፡ ስርዓተ ሰብ፡ ወይም ሰው ሰራሽ ባህል አይደለም። የእሳታውያን ባለ ስድስት አክናፍ መንበረ ጸባዖት (አርባዕቱ እንስሳት) ኪሩቤል ስርዓተ አምልኮ ነው። መንበረ ጸባኦት (አርባዕቱ እንስሳት) ቀደማዊና ድሐራዊ ነው። ይህም ማለት ጥንትና ፍጻሜ የሌለው ማለት ነው። ነገረ መለኮቱም በኪሩቤል ለሚመለከው አምላክ መግለጫ ነው። ስርዓተ አምልኮቱም ነገረ መለኮቱም መለኮታውያን ሲሆኑ፤ በሰው ሰውኛ አገላለጽ authentic orthodoksy ይባላሉ። ይህም ጥንተነት ያላቸው ቀጥ ያሉ ናቸው ማለት ነው። ዘመናውያን የነገረ መለኮት መምህራን ”If we have theology that does not take into account this oppressive situation and the hundreds of oppressive laws then we cannot be authentic”(The Third World Liberation Theology, page 269)እንደሚሉት፦ ኢትዮጵያውያን ነገረ አምልኮታችንና ስርዓተ አምልኮታችን ከመሰረቱ ያፈነገጡ ከህብረተ ሰብ ህይወት የራቁ አይደሉም። ኪሩቤላዊው ስርዓተ አምልኮታችን በመንፈሳችን፤ በሥጋችን፤ በቃላችንና በተግባራችን የሚገለጽ ነው። በቃል የሚገለጸው አምልኮት “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” የሚለው ሲሆን። በተግባር የሚገለጸው ደግሞ “ይሰሩ አንጻረ ኅቡረ” (ኢሳ 6፡2- 4) ብሎ ነቢዩ ኢሳይያስ እንደገለጸው የምጥቀትና የጥልቀት ወሰን አልባ የሆነው እንቅስቃሴ ነው። “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” የሚለው ቃለ አምልኮ “እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ብሎ ከመለኮት የመጣ ትእዛዝ ነው። (ዘሌ 19፡ 2 ) ጥንትነት ያለው ቀጥ ያለ ኪሩቤላዊ ስርዓተ አምልኮ ነው። ይህ የኪሩቤላዊ ስርዓተ አምልኮት ቅዱስ በሚል ቃል ብቻ የተወሰነ አይደለም። ነቢዩ ኢሳይያስ “ይሰሩ አንጻረ ኅቡረ” (ኢሳ 6፡2- 4) እንዳለው፦ በእንቅስቃሴም የታጀበ ነው። በዑደታዊ እንቅስቃሴ የታጀበውን ስርዓተ አምልኮታችንን ሌላው መጽሐፋችን “አኮ ዘቦቱ ለመለኮት ምስፉሕ ወምስትጉቡዕ አላ 3 0ውስተ ኩሉ በሀውርት መለኮቱ” (ቅ ማ ገጽ 171 ቍ 50)ሲል ይገልጸዋል። የምናመልከውን omnipresent (ምሉዕ በኩለሄ) የሚባለውን አምላክ የሚያንጸባርቅ፤ ኢትዮጵያዊው ስነ ልቡና የተቀረጸበት፡ ማህለቅት የሌለውን የመለኮትን ምጥቀት፡ ስፋትና ጥልቀት የሚገልጽ ነው። የኢትዮጵያዊነት ሉዐላዊ ስነ ልቡና የተመሰረተበትን ኪሩቤላዊ ስርዓተ አምልኮ የሚመራው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካህን በስእሉ እንደምናየው፤ ስድስት ረዣዥም ምላስ (ላባ) ያለው ለምድ የተደረበበት ካባ ይለብሳል። ይህ ባለ ላባ ካባ በመንቀልቀል ላይ ያለውን እሳት ያመለክታል። የሚንቀለቀለው የእሳት ምላስ ላንቃ፤ ነበልባልና ወላፈን ይባላል። ካህኑ ይህን ለብሶ “አሁዱ አብ ቅዱስ፤ አሁዱ ወል ድ ቅዱስ፤ አሁዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” እያለ አምልኮቱን ይመራዋል። “የተቀደሰውን ለተቀደሰው ለመስጠት ተጠንቀቅ” እያለ ካህኑን በተራዳኢነት የሚላላከው ዲያቆንም፤ አምስት ረዣዥም ላባዎች ያሉት ምላስ ለምድ ይለብሳል። የጥንታዊት ኢትዮጵያውያዊት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችን ስርዓተ አምልኮዋን ጀምራ የምትጨርሰው፤ ኢትዮጵያዊውን ጥንታዊ ስነ ልቡናችንን በሚያንጸባርቀው በኪሩቤላዊው ስርዓተ አምልኮ ነው። በካህኑና በዲያቆኑ ትክሻ የሚታዩት ላባ የሚባሉት ዘርፎች በአምልኮታችን ስርአት እንደታዩ በአርበኞች ትክሻ ላይም ይታያሉ። በቦታው ለመዳሰስ አልፈዋለሁ። የተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነትና ሥርአት “እኛስ ሁላችን ከሙላቱ ተቀበልን በጸጋ ላይ ለጸጋ ተሰጥቶናል። ሕግ በሙሴ ተሰጥቶብ ነበር። ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ተሰጠን” (ዮሐ 1፡ 16)። እያሉ ከተናገሩት ኪሩቤላዊ ስርዓተ አምልኮት ካላቸው ከነ ቅዱስ ዮሐንስን እምነትና ስርአት አምልኮ የተለየ እንዳልሆነ ልናስተውል ይገባናል። ይህን ስርዓተ አምልኮ ያስተማሩኝ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት፤ ህዝቡ “ድንበር ሲፈርስ መሐሉ ዳር ይሆናል” ወይም “የዛፍ ጫፉ ሲጨፈጨፍ ግንዱ ጫፍ ይሆናል” የሚለውን ባንድምታ በታትነው ያስተማሩን ከኦሪቱ በመጀመር ነው። ኢትዮጵያን ከጎረቤቶቿ ልዩና ቅኝ ገዥወችንም እንድትመክትና ጥንታዊትም ያደረጋት ከዚህ በላይ በገለጽኩት ስርዓተ አምልኮታችን በተቀረጸው ስነ ልቡና ነው። ኢትዮጵያ ሁሉንም የምትጀምረው የመጀመሪያ ጸጋ በታበለው በሙሴ መጽሐፍ በኦሪቱ ነው። የኦሪቱ ትርጓሜ መምህራን እነ የኔታ ጥበቡ የድንበርን ነገር እንዴት እንደሚገልጹት ከዚህ በታች እንመልከት። ፪ኛ:- የኦሪቱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ድንበርን እንዴትእንደሚገልጹት “ኢትትሀለፍ ደወለ ቢጽከ ዘሠርኡ አበዊከ በውስተ ርስትከ ዘተዋረስከ። ዘወሀበከ እግዚ አምላክከ መክፈልተከ” (ዘዳ 19፡12)። አባቶችህ የሰሩትን ድንበር ጥሰህና ተሻግረህ ያንተ ያልሆነውን መሬት አትውሰድ። የወረሰከውን ወሰን ጥሶ መሬትህን ቆርሶ ለመውሰድ ለሚመጣብህ ወራሪም ለልጅህ የምታወርሰው ትውፊት እንዲወስድብህ አትፍቀድ። ይህን ሥርአት አፍርሰህ የሰው ወሰን ብትደፍር፤ ያንተንም ብታስደፍር፤ የጎረቤትህን ወሰን በመድፈርህና፤ ያንተንም በማስደፈርህ ለሚከተለው ትውልድ የሚያስከትለው አደጋ፤ የተጣሰው ድንበር የሚያዋስናቸውን ሁሉ የሚያጠፋ ነው። አንተም ከቀደሙ አባቶችህ የወረስከውን ለልጆችህ ማውረስ ያልቻልክ “ርጉመ ለይኩን ዘይሰርቅ ደወለ ቢጹ” (ዘዳ 27፡15)። እንዲል የተረገምክ ዘረ ቆርጥም ትባላለህ። “ወይብሉ ኩሉ ህዝብ አሜን ወአሜን” በሚል በተፈጥሮና በሰው የፈቃድ ስምምነት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ፤ በኃይልህ ተመክተህ አባቶችህ የወሰኑልህን ወሰን ሰብረህ የሌላውን ወዳንተ ብታስገባ፤ ወይም በዝሁል (ግዴለሽነት)አመለካከትህ ወሰንህን ሰብሮ ለሚገባ የተረገመ ወራሪ የራስህን አሳልፈህ ብትሰጥ፤ መገሰስ የሌለበት የተፈጥሮ ህግ ነውና፤ በራስህ ልጆች ስትረገም ትኖራለህ። ድንበር ማፍረስ በሚጎራበቱት መካከል የመቅሰፍት ግርግዳ ተክሎ፤ ይቅርታ የሌለው ትልቅ በደልና ኃጢአት ለልጅ ማውረስ ነው። ኃጥእ የምትለው ቃል የጽድቅ መራቆትን፤ የሞራል ውድቀትንና እለታዊ ጉርስንና አመታዊ ልብስን ማጣትን የምታሳይ ኀብራዊ ትርጉም ያላት ቃል ናት። ኃይልን ተመክቶ የጎረቤት ወሰን መጣስም ሆነ፡ በዝሁል አዕምሮ የራስን ማስጣስ፤ ማለትም ማስወሰድም መውስድም ሞራለ ቢስ ርጉም መሆን ነው። ወሰን የሚጥሱትንና የሚያስጥሱትን ለተኩላወች መግለጫ የሆነውን መሳጢ የሚለውን ቅጽል በመስጠት ኢዮብ “ወተዓደው ኃጥአን እምወሰኖሙ ወመሰጡ ኖላዌ ምስለ መርዔቱ ወሄዱ አድገ ዕጓለ ማውታ “(ኢዮብ 24፡2)። እያለ ገለጻቸው። ወሰን ጥሰው እረኞችን ከመንጋወቻቸው ጋራ ነጠቋቸው አለ። ወሰን የሚሰብሩና የሚያሰብሩ ሰዎች፤ እንስሳትን ብቻ ከሚነጥቁ ተኩላዎች፤ እረኞችንም አብረው የሚነጥቁ እጅግ ከተኩላ የከፉ መሳጢዎች ናቸው ይላቸዋል። ዳዊት ድንበር መፍረስ የሚያስከትለውን የማይቆም የእርስ በርስ ቅጥቅጥና ግድያ በመመልከት “እስመ ርኢኩ ዓመጻ ወቅስተ ውስተ ሀገር። እስመ መአልተ ወሌሊተ ዕጉት ውስተ አረፋቲሃ። ወስራህ ወኃጢአት ማእከላ። ወኢይርህቅ እመርህባ ጒሕሉት። አስጥሞሙ እግዚኦ 4 ወምትር ልሳናቲሆሙ” (መዝ 54፡9 -10) ብሎ ተናገረ። ይህም ማለት፦ “በአገር ውስጥ “አሜን ወአሜን” ብለው ተስማምተውና ተከባብረው በሚኖሩት ዜጎች መካከል፤ በቀንና በሌሊት የማያባራ ወቅት እየጠበቀ የሚፈነዳ የታመቀ የገሞራ እሳት በየድንበሮቻቸው (ውስተ አረፋቲሃ) ሲንፈቀፈቅ አየሁ። ይህን ጥፋት የሚያቀነባብሩትን ተንኮለኞች ያልተገረዘ ውልብልብ ምላሳቸውን፤ ቅልብልብ እጃቸውን፤ ተቅነዝናዥ እግራቸውን ገርዘህ አሳርፋቸው” ። ይህ የዳዊት መጽሐፍ ምላሳችንን ከግእዙ ጋራ ለመግራት፤ ስናነብ ትንፋሻችንን የት ላይ ለመግታትና ተነሽ ወዳቂውን እንድንረዳ የሚያዘጋጀንን ውርድ ንባብ የሚባለውን ትምህርት ከተማርን በኋላ የምንማረው ነው። ምላሳችን መገራቱን ከግእዙ ጋራ መስማማቱን፤ ተናባቢዎችን ተነሽና ወዳቂ ቃላትን መረዳታችን ሲያውቁ መምህሮቻችን ወደዚህ ትምህርት ይከቱናል። ለምስጋና የሚቀርቡት ዜማወች የተዘጋጁት ብዙዎቹ የተወሰዱት ከዳዊት ስለሆኑ እንዳንረሳችው በጸሎት መልክ እንድንደግመው ያበረታቱናል። የሰሎሞንና የሲራክ መጻሕፍትም ለምሳሌ የምጠቅሳቸው ከዚህ በታች እንደሚታዩት፤ ባጫጭር አረፍተ ነገሮች የተቀመሩ ምክር በመሆናቸው፤ ለቅኔ ማደበሪያ ስለሚረዱ ባንድምታ ትምህርት ሳንዳስሳቸው እንዳናልፍ ያስገድዱናል። ሰሎሞን በወሰን አፍራሾች ርኩስ ሕሊና የሚጸነሰው መርገም የሚያስከትለውን መዘዝ “አብያተ ጸአልያን ያንህል እግዚአብሔር ፤ ወያጸንእ ወሰነ ለመበለት”(ምሳሌ 15፡25) እያለ ተናገረ። ይህም ማለት፤ ድንበር የሚጥሱ ሰዎች የሚፈጥሩት ችግር፤ በሚጎራበቱት ሰዎች ላይ ለጊዜው ቢከብድም፤ መከራና ሥቃዩ በህይወት እያሉ ተንኮሉን በሰሩት በራሳቸው ላይ ይመጣባቸዋል። ከሞቱ ደግሞ በልጆቻቸውና በሚዛመዳቸው ላይ የማታ ማታ መፈንዳቱ አይቀርም። አጋጣሚ አገኘን ብለው በግፍ የወሰዱትን የጀግኖች ድንበር ይቅርና፤ መዋጋት አቅም የሌላትን የደካማዋን ድንበር ሳይቀር እግዚአብሔር በኪነ ጥበቡ እንደሚመልስላት ይገልጻል። ጥበበኛው ሰሎሞን በድንበር አፍራሾ ች ላይ የሚደርሰውን መከራ ከተናገረ በኋላ፤ መስማትና ማስተዋል ለሚችሉት ሰዎች “ወኢትንስት ሥርአተ ዘለዓለም ዘአንበሩ አበዊከ “ (ምሳሌ 22፡28)። ብሎ መከረ። ይህም ማለት፦ “መርገም ባንተ ላይ እንዳይደርስ፤ ካንተ በፊት የነበሩ አባቶችህ የሰሩልህን ድንበር ጥሰህ የጎረቤት ወሰን አትንካ፤ ካባቶችህ የተሸከምከውን የውርስ እዳ የምትከፍለው፤ ለሚመጣው ትውልድ በማውረስ ነውና፤ ውርሱን የበላ ዘረ ቆርጥም ተብለህ በራስህ ልጆች ላለመወቀስና ላለመረገም ያንተንም አታስደፍር” በማለት ባንድምታው አስተምረውናል። ባንድምታው ብቻ አይደለም፤ ላንድምታው ትምህርት መክፈቻ ቁልፍ በሆነው በሰምና ወርቅ ቅኔ አስተምረውናል። በቅኔውና ባንድምታው ትምህርት ብቻ የተወሰነ አይደለም። ከዚህ በታች እንደምገልጸው ህሊናችንን ሰብስበን ራሳችንን እየፈተሽን ከህሊናችን ጋራ በማዛመድ የድንበራችንን ነገር ለፈጣሪ እንድናቀርበው ከእለታዊ ጸሎታችን ጋራ አዛምደው አውርሰውናል። ፫ኛ:- ድንበር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርአተ ጸሎት በኪሩቤል አምሳል ተሰይሞ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያለ አምልኮቱን የሚመራው ኦርቶዶክሳዊ ካህን፡ በመንበሩ ላይ የሚሰይማት ህብስት የክርስቶስ አማናዊ ሥጋነቷ እንዳለ ሆኖ፤ በኢትዮጵያና በዓለም ዙሪያ ለተበተኑት ክርስቲያኖች መዘክርነት አላት። ይህች ህብስት የምትሰየምባት፤ ካህናቱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ በዑደት የሚዞሯት መንበር በወርቅነት ሰማያዊነቷ መንበረ ጸባኦትን ስታሳይ፤ በምድራዊ ሰምነቷ ደግሞ፡ የኢትዮጵያ ልጆች የሚኖሩባትን ኢትዮጵያዊቷን መልክአ ምድር ታሳያለች። “አንብር ለነ ዲበ መንበሩ ህየንቴሁ ኖላዌ ኄረ ኢንኩን ከመ መርዔት ዘአልቦ ኖላዊ ፤ ወኢይምስጠነ ተኲላ መሣጢ። ወኢይጽዐሉነ ሕዝብ ነኪራን እለ ውጹአን እምኔነ”(ሥ ቅ ገ 49፡ቁ 113)። በሚለው በስርዓተ ቅዳሴያችን፤ መንበር በኅብራዊ ይዘቷ ወርቅነትና ሰምነት ትዳሰሳለች። ይህም ማለት በቀደመው ደገኛ (ላገር ለድንበር ለዜጋ ተላልፎ የሚሞት) መሪ ፋንታ፤ ደገኛ መሪ ሰይምልን። መሪና አሰማሪ እንደሌላቸው በጎች፤ ድንበር ጥሰው በሚመጡብን ተኲላወች ተበልተን በማለቅ፤ ከድንበራችን ከባህላችንና ከእምነታችን ውጭ ለሆኑ ሰዎች መዘባበቻም አታዳርገን (አታጋልጠን)። በዚህ አረፍተ ነገር፤ ከደመና በታች ያለውን ምድሪቱ ያፈራቸውን ለዜጎች እኩል የሚያካፍለውን መሪ በሰምነት፤ ለማታልፈው ሰማያዊት መንግስት መምህር የሆነውን ፓትርያርክ ደግሞ በወርቅነት ይገለጻሉ። ይህም ማለት የቤተ ክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ አባትነትና መሪነት፤ በሞራሉ፡ በሃይማኖቱ፡ በታማኝነቱ፡ በክርስትና እምነቱ ለተጠመቁት ብቻ ሳይሆን፤ የሃይማኖት የጎሳ የዘር ልዩነት ሳያሳይ እግዚአብሔር በአርያው ለተፈጠረው ሁሉ እንዲሆን ያስጠነቅቃል። በቅድስናው በልዕለ አዕምሮው ምሳሌነቱ፡ የሁሉ ፈጣሪ የሆነውን የቅዱስ አምላክን ፈቃድ ማንጸባረቅ አለበት። በመንበሩ ላይ ለሚቀመጠው ሰው ቅዱስ የሚለው ቅጽል የተሰጠውም በዚህ አቋሙና ባህርይው ነው። በቃሉና በግብሩ ይህን ቅድስና የምይገልጽ ከሆነ፤ በቦታው ስለተቀመጠ ብቻ ቅዱስ የሚለውን ቅጽል መስጠት ከስርአታችን፤ ከእምነታችንና ከታሪካችን ጋራ የሚያጋጭ፤ በኢትዮጵያዊነት ሁለንታና መሳለቅ ነው። 5 የቅድስና ባህርይ የሌለው ፓትርያርክ በመንበሩ እንዳይሰየምና። ከተሰየመም በምትኩ ቅዱስ ለሆነው ተልእኮው ተስማሚ አባት እንዲሰይምልን ፤ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በተኲላወች ተበልተን ከማለቅ ሰውረን፤ ከድንበራችን ከባህላችን ከእምነታችን ውጭ የሆኑ ሰዎች መዘባበቻም አታድርገን እያልን እንድንጸልይ ኢትዮጵያዊው ስርዓተ አምልኳችን ያዝዘናል። ኢትዮጵያ ፈታኝ የበዛባት በመሆኗ በየዘመኑ የሚነሱት ቀሳውስት ከነሱ በኋላ ለሚመጡት ቅርስና እምነት ወራሾች ለሆኑ ልጆቻቸው “ጸግወነ እግዚኦ ለነ ለአግብርቲከ ወለእለ ይመጽኡ ድኅሬነ ወእስከ ለዓክ መዋዕለ ጸጉ”(ሥ ቅ ገ 50) እያሉ ይጸልዩ ነበር። ይህም ማለት፦ ለኛ ብቻ አይደለም፤ ከኛ በኌላ የሚነሱት ልጆቻችንም መሪና አሰማሪ እንደሌላቸው በጎች በተኲላወች ተበልተው ከማለቅ ሰውራቸው፤ ከድንበራቸው ከባህላችቸው ከእምነታችን ውጭ በሆኑ መሳጢዎች መዘባበቻም አታዳርጋቸው። እያሉ ይጸልያሉ። በሚለብሱት ልብሰተክህኖው ላይ የሚታዩት ስድስቱ ላባዎች ፤ የሱራፌልን ባህርይ፤ የአምልኮታቸውን ጥልቀትና ምጥቀት የሚገልጹትን ስድስቱን አክናፍ (ላባወችን) የሚያንጸባርቁ ናቸው። በዲያቆናቱ ትክሻ ላይ የሚታዩት አምስቱ ላባዎችም፤ ሌላው የጸሎታችን መጽሐፍ “እለ አቅለሉ ክንፊሆሙ ለተልእኮ ዛቲ ጠረጴዛ” እንዳለው። ስሜታቸውና ተልእኳቸው ከተዛምደላቸው ኪሩቤላዊው ምሥጢር በቀር የሚጨነቁበትና የሚጠለፉበት እንደሌላቸው የሚያሳይ ነው። በስርዓተ አምልኮታችን በካህኑ እና በዲያቆኑ ላይ የሚታዩት ላባዎች በወርቅነት እሳታውያን የተባሉትን ኪሩቤልን ያሳያል። ላባ የምትለው ቃል ለድንበር ቤዛ ከሆነው ከብሔራዊ ልዕለ አዕምሮ ጋራ የተዛረፈች ስለሆነች በቦታው ለመግለጽ አልፋታለሁ። በካህኑ ላይ የሚታዩትን ስድስቱ ፤ በዲያቆኑ ላይ የሚታዩት አምስቱን ላባዎች የሚያንጸባርቁትን የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት “አድኅነነ ወባልሐነ እምኵሉ እኩይ እምተመውዖ ለሰይጣን እምሕርትምና ወድቀት” (ሊጦን ገጽ 398)። እያሉ ይጸልያሉ። ይህም ማለት “አምላካችን ሆይ! ከፈታኝ ክፉ ነገር አድነን። በቅኝ ገዥወች በወራሪዎች ከመሸነፍ በእጃቸው ወድቀን ከመጎሳቆልና ከመዋረድ አድነን፤ እያሉ የአርበኝነትን ምኞት (ጸሎት) ለአምላካቸው ያደርሳሉ። ጸሎት ለአምላክ የሚቀርብ ምኞት ነው። መፈክርም ይሆናል። ለንግድም ላንዳንድ ጉዳይ ከአገር ለራቁ ሁሉ ምንም እንዳይደርስባቸው፤ የትግራይ ነጻ አውጭ በበሻንጉል፤ በወልቃይት፤ በጸገዴዎች፤ በቅማንቶች፤ በኦሮሞዎችና ባማሮች ላይ እየደረሰ ያለው ወረራና መፈናቀል አይነት እንደደረሰባቸው ማለት ነው። “እመሂ በባህር ወእመሂ በአፍላግበላያት በፍኖት በዘኮነ ይነግዱ መንገደ ይነግዱ ያብጽሆሙ ውስተ መርሶ መድህን” ( ገጽ407) እያሉ ይጸልያሉ። ይህም ማለት፦ በባህር በየብስ የሚንቀሳቀሱት ሰዎችም አደጋ ሳይደርስባቸው በሰላም ከሚፈልጉት ወደብ አድርሳቸው” “ባቁዐ ላቲ ወጸግዋ አግርር ጸራ አሕዛበ ዘመንገለ ዐረፍታ” ማለትም፦ከድንበራችን ውጭ ያሉ ሰዎች ድንበር ጥሰው ጥፋትና ጉዳት ለመፍጠር የሚያቅዱትን አድክምልን። ሀሳባቸውንም ወደ በጎ ነገር ለውጥልን። ካሉ በኋላ፤ ድንበር ጥሰው ከውጭ በሚመጡት ወራሪዎች ብቻ በአገር ላይ ችግር አይፈጠርምና፤ ድንበር ሰብረው ለሚወሩ ባእዳን ወራሪዎች፤ ከዜጎችም መካከልም ቀዳዳ የሚከፍቱበት ክፉ ዘመን አለ። ይህን በመሰለ ዘመን ወራሪዎች የሚፈጽሙትን ግፍና መከራ መናገርና መገሰጽ የሚገባቸው ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች አፋቸውን ያፍናሉ። ስለዚህ “ወተናገር ጽድቀ ውስቴታ በእንተ ቤተ ክርስቲያንከ ” (ገጽ411) እያልን እንድንጸልይ ስርአቱ ይነግረናል። የጎረቤት አገሮች መሪዎችም ቀን ገጠመን ብለው በስጦታም ሆነ በወረራ የጎረቤት ድንበር ከመውሰድ ህሊናቸውን እንዲሰበስቡ ፈጣሪ ይረዳቸው ዘንድ “ሀብ ምክረ ለመኳንንተ አሕዛብ አግዋረነ” (ገጽ 414)። እያልን ስለ ድንበር ደህንነት ምኞታችንን ጸሎታችንን እንዳናቋርጥ ኢትዮጵያዊው ስርአተ ጸሎታችን ያስገነዝበናል። አሁን ድንበርን በታሪካችንና በባህላችን አንጻር እንቃኛለን። ፬ኛ:-ድንበር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክና ባህል የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን Indigenous (አገር በቀል) እየተባሉ ከሚነገርላቸው ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ናት። ነገረ መለኮቱም የሚገለጸው ከኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ፣ ባህልና ዘይቤ ጋራ በታዘመደ መንገድ ነው። ይህም በውጭ አገር አነጋገር Cultural Theology ይባላል። “ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኳችሁ ጊዜ ካላመናችሁ ስለ ሰማያዊ ነገር ብንነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?(ዮሐ 3፡12)እያለ ክርስቶስ በዘመኑ የነበረውን የትምህርት ሰው ኒቆዲሞስን እንደመዘነው፤ ከሐዋርያት በኋላ የተነሱት የተዋህዶ ነገረ መለኮት ሊቃውንትም ተፈጥሮን ለማወቅ በክፍተኛ ትምህርት ቤቶች ገብተው የተማሩ፤ ራሳቸውን መዝነው፤ የክርስትንናን እምነት ሰው ከባህሉ ከኑሮው ጋራ በማዘመድ እንዲወሀደው ያደረጉ እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፤ እነ ቅዱስ ባስልዮስ ናቸው። ቅዱስ ባስልዮስ “ቦኑ ይትከሀለነ ንጠይቅ ስፍሀ ሰማይ ወእመቀ ቀላይ እመሰ ኢንክል ንጠይቅ ኀዳጠ እምፍጡራን እፎመ ይትከሀለነ ንብጻህ ኀበ አዕምሮተ እግዚ አብሔር” (ባስልዮስ 33፡ 12)። እያለ ካወቀው ከተማረው በመነሳት፤ የሚያስተምር ስለ natural science 6 የጠለቀ እውቀት የነበረው ሰው ነው። ይህም ማለት፤ “በውኑ የህዋውን ምጥቀትና ስፋት፤ በውቅያኖስ እመቅ ውስጥ ያለውን ፍጥረት ጠንቅቀን መረዳት ችለናልን ? ታዲያ ፍጥረትን አጠናቀንና ጠንቅቀን ካልተረዳን፤ ፈጣሪያቸውን ለመረዳት አቅማችን እንዴት ይችላል? አለ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ስለ Astronomy (ሥነ ጠፈር ጥናት) ያወቀ ሊቅ ስለነበረ “ወሶበሂ ይፈቅድ ህሊና ይብጻህ ሃቤሁ ይደልዎ ብርሃኑ እፎኑ ይክል ሰብእ ይነጽር ጸሐየ ወይጠይቅ አምሳሊሁ እመሰ ኢንክል ጠይቆቶሙ ለፍጡራን እፎ ይትከሀለነ ጠይቆቶ ለገባሬ ኩሉ”(ሃ. አ. ም. 62፡10)እያለ አስተማረ። ሰው የማሰብና የመመራመር ችሎታው ዝግጁ ሆኖለት፤ ስለ astronomy (ሰማያውያን ከዋክብት) የጠለቀውን እውቀት ተማርኩ ቢልም፤ ሁሉንም ሊያውቅ እይችልም። የተፈጥሮን ጥልቀት ተምረን የማንዘልቀው ከሆነ የፈጣሪንማ እንዴት አዕሞሯችን ሊረዳው ይችላል? ” አለ። ከብሉያትና ከሐዲሳት ንቅንቅ ሳይሉ የኦርቶዶክስን ነገረ መለኮት cualtural theology የቀመሩት እነዚህ ሊቃውንት ናቸው ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት መምህሮቻችንም፤ የነተዋነይን፣ የነ ቅዱስ ያሬድን ድርሰት ቅኔውን ተምራችሁ፤ የኦሪቱን እውቀት፤ የነብያትን ትንቢት፤ የሐዋርያትን ስብከት፤ በነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርተ መለኮት ይዘት ካልተቀረጻችሁ፤ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ በስሜ የሚመጡ ብዙዎች ናቸውና ተጠንቀቁ ከሚላቸው ከዘመናውያን ወራሪዎች መምህራን ወጥመድ አታመልጡምና ራሳችሁ ጠፍታችሁ ኢትዮጵያን እንዳታጠፏት ተጠንቀቁ ያላሉ። በባህል በሃይማኖትና በታሪክ መካከል ያለውን ቁልፍልፍ ለይታችሁ ማሳየት አትችሉም። መምህራን ነን ብላችሁ ወደ ህዝብ አትቅረቡ። ከውጭ ሰርጎ የሚገባውንም እያገበሰብሳችሁ በህዝብ ላይ በመድፋት የነበረውን የተዋህዶውን እምነት ታበላሻላችሁ፤ የኢትዮጵያዊነትንም ስነ ልቡና ሰላቢዎች ትሆናላችሁ” ይላሉ። ኢትዮጵያ ወቅት እየጠበቀች እንደጨረቃ ቅርጿን በመለዋወጥ የምትታይ ናትና በሙሉነት የነበረችበትን ያባቶቻችሁን ዘመን አትርሱ ይላሉ። ይህን አባባል አባቶቻችን ብቻ የሚናገሩት አይደለም። ከኛ ጋራ ታሪካዊ ንክኪ ያላቸው ጸሐፊዎችም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሃማኖት የታሪክ እና የባህል ቤተ መዘክር ብቻ አለመሆኗንና፤ የገጸ ምድር ወሰንም ምስክር መሆኗን በታሪካቸው ጽፈውታል። ከኛ ጋራ ታሪካዊ ንክኪ ካላቸው ብዙወቹ አንዱ Iris Habib el Masri የተባሉ፤ FROM THE ARAB CONQUEST TO THE PRESENT TIME በሚለው መጽሐፋቸው፤ በ1632 ዓ ም በነበሩት ኢትዮጵያውያን መሪዎችና ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ ሲነገሩ እንዲህ ብለዋል። “JESUITSን እና ከነሱ ጋራ ወደ ኢትዮጵያ የገቡትን ወራሪዎች ከነጋዴዎች በቀር ጥርግርግ አርጎ ከኢትዮጵያ አስወጣ” ካሉ በኌላ “After reestablishing security within his borders, he sent a letter to Abba Mattheos telling him what he had done and requesting him to consecrate a Coptic Bishop for him ድንበሩን አስከበረ “Ethiopia celebrated the expulsion of the Jusits and aother spiese entrudas by an epigram which said ‘the sheep of Ethiopia have been deliverated from the hyenas of the west by the doctrines of St. Cyril the great the pillares of the Alexandrian Church (page 262) እያሉ ተናገሩ። የነቅዱስ ዮሐንስንና የነ ቅዱስ ቄርሎስን ትምህርተ ነገረ መለኮት ከራሳቸው ኢትዮጵያዊ ስነ ልቡና ጋራ ያዋሀዱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ዓለምን ከወረራት የምእራብ ጅብ አገራቸውን አዳኗት“ እያሉ ስለ ድንበር ስለወሰን ስለሚያስቡ ኢትዮጵያውያን ክህናት ምስክርነታቸውን ገልጸዋል። ይህ ምስክርነት እውነት ነው። “እስመ ከመዝ ጸሐፈ ቅዱስ ጳውሎስ እንዘ ይብል አኮ መኑሂ እምኔነ ዘየሐዩ ለርእሱ ወኢመኑሂእምኔነ ዘይመውት ለርእሱ እመኒ ሐየውነ ለእግዚአብሔር ነሐዩ ወእመኒ ሞትነ ለእግዚአብሔር ንመውት”(ሃይ ም 72፡ 31)እያለ ቅዱስ ቄርሎስ ያስተማረውን፤ ኢትዮጵያውያን መምህራን በእጽፍ ድርብ አንድምታቸው ለዘላለማዊ ርስት መሞትን እንደ ወርቅ፤ የለበስነው አካላችን ለተከሰተባት ኢትዮጵያ ለምድራዊ ርስትነቷ መሞትን እንደ ሰም፡ አርገው አስተምረውናል። ስለ Indigenous (አገር በቀል) አብያተ ክርስቲያናት እና Cultural Theology አጥንተው ካቀረቡት ሊቃውንት መካከል Kofi Appiah – Kubi የተባሉ ሊቅ የተናገሩትን ልጥቀሰው። እኒህ ሊቅ የአገር በቀል አብያተ ክርስቲያን ውበት በገለጹበት ምዕራፍ ላይ የሚቀጥለውን አስፍረዋል። “Another important area of attraction is the emphasis these churches place on veneration of ancestor, who are sid to be the custodians of law, morality, and ethical order of the Akans. The mission churches, while overlooking the Akan ancestors, urge their members to venerate St. George of England, St.Adrew of Scotland or St. Christopher of the Vatican, who are very much removed from the converts’ daily wants and anxieties.” (Third World Liberation Theologies page 225) እያሉ የተናገሩት፤ የኛን ቤተ ክርስቲያን ሁለንተና፤ የነገረ መለኮታችንን አተረጓጎምና ስርዓተ አምልኳችንን በሚገባ ይገልጸዋል። ለወሰንና ለድንበር አጥርና መከታ ሆነው ያስረከቡንን አባቶች ለምሳሌ፤ እንደ አጼ ቴዎድሮስ፣እንደ እነ አጼ ምኒልክ፣ እነ ደጃች ባልቻ አባ ነፍሶ፣ እነ ፍታውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስን፣ እነ በላይ ዘለቀን፣ እንደ ፍታውራሪ ተክለ ሀዋርያት፣ እነ አቶ አክሊሉ ኃብተወልድ፣ እነ አቡነ ጴጥሮስንና እነመምህር ገብረ ኢየሱስን ለመመልከት ዓይነ ልቡናችንን የሚገልጥልንን ትምህርት ሰብስባ የያዘችው ይህችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ናት። 7 Kofi Appiah – Kubi የተባሉት ምሁር ”while overlooking the Akan ancestors, urge their members to venerate St. George of England, St.Adrew of Scotland or St. Christopher of the Vatican, እንዳሉት፤ ከላየ ከተጠቀሱት ከኛ አባቶች መመዘኛና መታዘቢያ የሚሆነን የተማርነው ከሌለን፤ ከላቲኖች መምህራን ከእንግሊዝኛ ሊቃውንት የምንማረው ስለድንበር መገሰስ ስለሀገረ መቃወስ የምንናገረው ቋንቋ እንዲኖረን አያግዘንም። ስሜቱን ሀለፊነቱን ልንረዳ የምንችለው እድሜ ዘመን መከራና ደስታ ያገናኛቸውን ከላይ የገለጽኴቸውን አርበኞቻችን ስንመለከት ነው። እነሱን መመልከት የምንችለውም እንዳናይ ወያኔዎች የሸፈኑብንን ጥቁር መጋረጃ ከፊታችን ቀዳደን ስንጥል ብቻ ነው። በቦታው እገልጻታለሁ ብየ ያለፍኳት ላባ የምትለው ቃል ከአርበኞች ጋራ ጥብቅ ግንኙነት ስላላት አርበኞችን ባወሳሁባት በዚህች አንቀጽ እዳስሳታለሁ። ድንበር ለሚጠይቀው ተልእኮ (ዲቁና) አገልግሎት በንቃት የተሰለፉ አርበኞች ከዚያ በፊት ግን ላሳስበው የምፈልገው ነገር አለ። በየዘመኑ የሚነሱት መሪዎች በትክሻቸው የሚታየው ኪሩቤላዊ ለምድ እንደሚያሳየው፤ ለክቡር ዜጋ ዘበኞች መሆናቸውን ረስተው፤ ኢትዮጵያን ለራሳቸው ክብር ጠረጴዛ፤ ህዝቡን ለራሳቸው ክብር ዘበኛ በማድረቻው አልተሳሳቱም ማለት ባንችልም፤ በሀገር፤ በድንበርና በኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ላይ ወያኔ የፈጸመውን ግፍና በደል አልፈጸሙም። በካህኑና በዲያቆኑ ትክሻ የሚታዩት ላባ የሚባሉት ዘርፎች በአምልኮታችን ስርዓት እንደታዩ በአርበኞች አባቶቻችን ትክሻ ላይም ይታያሉ። በቦታው ለመዳሰስ አልፈዋለሁ ያልኩትን ቦታው ነውና ከዚህ ላይ አወሳዋለሁ። በቤተ መቅደስ ውስጥ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ስርዓተ አምልኮውን የሚመሩት ካህንና ዲይቆን የለበሱት ባለ ምላስ ለምድ፤ ለኢትዮጵያ የክብር ዘበኞች መሆናቸውን የሚያሳየው ኪሩቤላዊው ባለ ምላስ ለምድ በቀድሞ መሪዎች ትክሻ ላይ ይታያል። ለኢትዮጵያውያን ዜጎች የክብር ዘበኞች የሆኑ ልዑካኖች ዘላለማዊነትን ለሚያንጸባርቀው ለመንፈሳዊ አገልግሎት ሰም ሆነው ይቀርባሉ። ይህም ማለት ኢትዮጵያውያን የሚኖሩባት የኢትዮጵያ ወሰን ከመደፈሯ በፊት እኛ እንደ ሰም እንቅለጥ እንደገልም እንቀጥቀጥ በሚል ቃል ኪዳን የታሰሩ፦ “ሥጋየን ይብሉና ደሜን ይጠጡጥቱ፤ መቃብር ሳልገባ ሳለሁ በሕይወት ኢትዮጵያ ተደፍራ ቆሜ ከማያት” እያሉ ለድንበራቸው ተላልፈው ለመሞት የተሰለፉ አርበኞች ናቸው። አርበኛ የሚለው ቃል እንደሌሎች ቃላት ሁሉ በዘመን ርቀት ዳሕጸ ልሳን የተለወጠ እንደሆነ ከመምህሮቼ ሰምቻለሁ። መሰረታዊ ቃሉ የሰማንያኛ ዘመን ግማሽ አርባኛ (40ኛ)ነው። ይህም ማለት ዳዊት “ሰው በሽታ ካላጠቃው ካሰበው ደርሶ መመለስ የሚችለው እስከ 80 ዘመኑ ነው” ያለውን መነሻ በማድረግ፤ ለመንቀስቀሳቀስ ለማሰብ ሙሉ ኃይል የሚኖረው አርባኛ (40ኛ) ዘመን ላይ እንደሆነ መምህራን ይናገራሉ። “ከ80 ዘመን በላይ ግን ወገብ መቆርፈድ፤ ቋንጃ መቀየድና በአዕምሮም መንዛዛት ነው” ይላሉ። አርባኞች ባንድ ዘመን ኢትዮጵያ የወለደቻቸው ናቸው። በዘመናቸው የገጠማቸውን ችግር ለመወጣት ባንድ ልብ ተሰልፈው ለኢትዮጵያ ድንበር የቆሙ ላባዎች ነበሩ። የነፍጣቸውን ጫፍ (ላባ) በወራሪዎች ላይ ደግነው የኢትዮጵያን ጫፍ ያላስደፈሩና ያላስነኩ 8 ኢትዮጵያውያን ለሚኖሩባት መንበር (ኢትዮጵያ) የተሰለፉ ዲያቆናት ነበሩ። “እለ አቅለሉ ክነፊሆሙ። ለተልእኮ ምስጢር በዲበ ዛቲ ጠረጴዛ” እንዲል፦ ጠረጴዛ በተባለቸው ላይ ሰፍረው ለሚኖሩት ዜጎች ለማገልገል ማቄን ጨርቄን የማይሉ ለፍጹም አገልግሎት የተሰለፉ ላባዎች ነበሩ። በስእሉ እንደሚታየው በአርባኞች ትክሻ ላይ ያለው ለምድ የነሱን ተልእኮ የሚያንጸባርቅ ነው። ለሀገራቸው ለድንበራቸው ነበልባሎች፤ ወላፈኖችና ላባወችም ነበሩ። “ወንድ ከሆንክ ናና ጫፌን ንካ” በማለት ለኢትዮጵያ ራሳቸውን ጫፍ ያደረጉ ላባወች ነበሩ። ዱሮ ላባ የምትባለው ቃል ሰፊ ትርጉም ነበራት። በግንብ በቅጽር (አጥር) መደምደሚያ ላይ የተተከለ ሹል ጫፍ ያለው መከላክያ ብረት ማለት እንደነበረ ክቡር ደስታ ተክለ ወልድ የተባሉት ባለ ውለታችን ታላቅ አባት ባዘጋጁልን መዝገበ ቃላት ንድምታ ከሚገለጽበት ጋራ በማያያዝ ጠቁመውናል። “ጠርሙስና የ ብርጭቆ ስባሪ” ብለውታል።(ያማረኛ መዝገበ ቃላት በደስታ ተክለወልድ ገጽ 700 ይመልከቱ። )“ለዘመጽአ ላእለ ቅጽር ይከልሎ በላባ” “ቅጽር ሰብሮ የሚመጣ ሌባ፤ እግሩ ይቆረጣል በላባ“ የተባለላቸው ኢትዮጵያውያን አርባኞች በድንበር ላይ የተሰኩ ላባዎች ነበሩ። ላባ የሰውነት ጫፍ ነው። ቆዳችን ሰውነታችን የተጎናጸፈው የሰውነታችን ጫፋ ነው። ይህ አባባል አርበኞች ጎረቤት አገሮችን ሲቀራመቱ ለነበሩ ወራሪዎች “እስቲ ወንድ ከሆ ንክ ጫፌን ንካ” እያሉ ሲያስጠነቅቁበት የነበረ ቃል ነው። ልጆች ሆነን ጨዋታችን ሲፈርስ፤ መድረን በመቆም “ወንድ ከሆንክ፤ ናና ጫፌን ንካት” የምንለው ከአርባኞች የወረሰነው ነበር። የወረሰነው ስል የኢትዮጵያዊነት ልዕለ አዕምሮ ኢትዮጵያ መከራ በገጠማት ወቅት 40ኛ ዘመናቸው አገናኝቷቸው በጅግንነት ተግባራቸው የሚቀዳጁት ማለት እንጅ፤ በሥጋ ልደት የማይወረስ ነው። በዚህም ምክንያት በዚህ መስመር የ40ኛ ተልእኴቸውን የፈጸሙ አባቶች፤ የ40ኛነታቸውን ለምድ ለቤተ ክርስቲያናቸው እንጅ በሥጋ ለወለዷቸው አላወረሷቸውም። ይህም ኢትዮጵያ በፈተና ስትወድቅ 40ኛ ዘመናቸው ያገናኛቸው እንደነ አጼ ቴወድሮስ charismatic ጥሪ የደረሳቸው ብቻ የሚቀዳጁት መሆኑን ለማሳየት ነው። እነዚህ ኢትዮጵያውያን አርበኞች፦“ማእስ ቤዛ ማእስ” እንዲሉ፦ በሰውነት ቆዳችንም ይመሰላሉ። ቆዳችን መጀመሪያ የሚታይ ሙቀትንና ቅዝቃዜን አጣጥሞ የሚቀበል በሰውነታችን ውስጥ ባሉት ብልቶቻችንና ከሰውነታችን ውጭ ባለው ዓለም መካከል የተሰተረ ሽፋን ነው። የሰውነት ቆዳችን ለጠቅላላ ደህንነታችን (homeostasis) ቤዛ ነው። የኢትዮጵያ ገላ የተሸፈነችበት ቆዳዋ ድንበሯ ነው። ድንበር በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ባሉት መካከል የተቀመጠ መከላካያዋ ጫፍ ነው። ኢትዮጵያዊ አርባኛነት በኢትዮጵያና በውጩ ዓለም መካከል ተሰትረው የቆሙ፤ በሩቁ የሚታዩ ከውጨ ዓልም የሚነፍሰውን የወራሪዎችን ሙቀትና ቅዝቃዜ የሚለኩ ጫፎች ናቸው። አርበኞች ድንበር ለሚጠይቀው ተልእኮ (ዲቁና) አገልግሎት ማቄን ጨርቄን ሳይሉ በንቃት የተሰለፉ ላባዎች ነበሩ። ጋሾ ለጦር፤ ጫማ ለጠጠር፤ ቆዳ ለቀን ሀሩርና ለሌት ቁር፡ ቤዛ እንደሆኑ፤ ድንበርም ወደ መሐል አገር የሚገሰግሰውን ጠላት ለመካከል ቤዛ ነው። አርበኞች ደግሞ ለኢትዮጵያ ቤዛ ለሆነው ድንበሯ ቤዛዎቿ ነበሩ። ቆዳው የተገፈፈ ሰው ህልውና እንደሌለው የአገር ድንበር ሲገሰስም መሐሉ ዳር በመሆን አገር ይፈርሳል” እያሉ ሊቃውንት በቅኔያቸው፤ በትርጓሚያቸው፤ ቀሳውስት በስርዓተ አምልኮታቸው፤ አዛውንት በብሂላቸው፤ ሲናገሩ የሰማሁትን አቅሜ የፈቀደልኝን ስለድንበር ያቀረብኩላችሁን ፈጸምኩ። በተረፈ እግዚአብሔር ከአርበኞች አባቶቻችን ረድኤትና በረከት ያሳትፈን! ለሌሎች የቂሲስ አስተርአየ ጽጌ ጦማሮች የሚከተለዉን ድረ-ገጽ ይመልከቱ፥ http://www.medhanialemeotcks.org/

No comments:

Post a Comment