Monday, January 11, 2016

የመቀሌ የባጃጅ አሽከርካሪዎች መስተዳደሩን አንበረከኩት | ‘የኦሮሞ ተማሪዎች ስልፎች የሕወሓት አስተዳደር በሹፌሮቹ እንዲንበረከክ ተፅእኖ አድርጎታል’ – አምዶም ገብረሥላሴ

mekeleየአረና ፓርቲ አመራር አባል አቶ አምዶም ገበረሥላሴ በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን መረጃ አስፍሯል::
የባለ ባጃጆች እምቢታ በመቐለ
=*=*=*=*=*=*

የመቐለ ወጣት ባለ ባጃጆች መስተዳድሩን ኣንበረከኩት። ( ‪#‎Bajaj_Protest‬ እንደ ማለት ነው)
የኢህኣዴግ መንግስት ዓይኑን ጨፍኖ የሚያወጣቸው ኣዋጆች፣ እቅድና ኣሰራሮች ህዝቡን ኣማርሮ ለዓመፅ እየገፋፋው ነው።
ሰሞኑ የመቐለ መስተዳድር በከተማዋ የሚገኙ ከ2500 በላይ ባለ ባጃጆች የሚመለከት ያወጣውና “ባጃጆች በታፔላና በሚወጣላቸው መስመር ብቻ እንዲሰሩ” የሚያስገድድ ኣሰራር ከፍተኛ ተቃውሞ ኣጋጥሞታል።

መስተዳድሩ “ባጃጆች እንደ ታክሲ ታፔላ ተለጥፎባቹ፣ በተመደባቹ መስመር ብቻ መሰራት ኣለባቹ፣ ማንኛውም ኮንትራት መስራት ኣይፈቀድም፤ ይሄ ኣሰራር ፀጥታችን ኣስተማማኝ እንዲሆንና የሽብር ጥቃቶች ለመቆጣጠር ይረዳል ተብሎ የወጣ ስለሆነ የማይቀለበስ መመርያ ነው” የሚል ኣምባገነናዊ መመርያ ኣውርደዋል።
ይህ መመርያ ለባለ ባጃጆቹ ” ካሁን በኋላ በመቐለ ከተማ ሰርታቹ መኖር ኣትችሉም ” የሚል ግልፅ ኣምባገነናዊና ትእቢተኝነት የወለደው ክልከላ ነው ብለው ገልፀውታል።
ሃላፊዎቹ ኣዋጃቸው ለመተግበር ባለ ባጃጆች ለስብሰባ ወደ ማዘጋጃ ቤት ተጠሩ።

የስብሰባው መሪዎች መሓሪና ወዲ ሓየሎም የሚባሉ የመንገድ ትራንስፖርት ሓላፊዎች ሲሆኑ “ይሄ መመርያ በውድና በግድ መቀበል ኣለባቹ እምቢ የሚል ባለ ባጃጅ ካለ ግን የማያዳግም እርምጃ ይወሰድበታል” ሲሉ ዝተዋል።
ወጣቶቹ… “ይሄ ኣሰራር መተግበር ማለት ከደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ተበድረው፣ የቤተሰባቸው የቤት ፕላን ኣስይዘው፣ ንብረት ሽጠው፣ ቤተሰብ ኣስቸግረው የገዟት ባጃጅ ሳትሰራ በኪሳራ ኣስቀምጧትና በእዳ ተዘፈቁ፤ ስራ ኣጥ ሁናቹ እየሰረቃቹ፣ እየዘረፋቹና ወደ ሱስ ገብታቹ እርባና ቢስ ሁኑ፤ ከዚህ በተረፈ ደግሞ ኣገር በመተው እግራቹ ወደ መራቹ እየተሰደዳቹ እንደ ሌሎች ወንድም እህቶቻቹ በበረሃ ሃሩር፣ ኣውሬ፣ ሙቀት፣ በባህር ዓሳ፣ በኣሸባሪዎችና በኩላሊት ነጋዴዎች ተበልታቹ ጥፉ ማለታቹ ነው”… ሲሉ በመግለፅ መስተዳድሩ ኣምርረው ኮንነዋል።
“ይሄ ኣሰራር ይተግበር ያለ ኣካል በወጣቶች ሞት እየፈረደ መሆኑ ሊያውቀው ይገባል” ሲሉ ኣሳውቀዋል።
ባለ ባጃጆቹ መመርያው ወደ ትግበራ እንዳይገባ የሚያሳስብ ደብዳቤ ፅፈው ለትግራይ ክልል ኣስተዳዳሪ ኣቶ ኣባይ ወልዱ፣ ለክልሉ ምክርቤት፣ መንገድ ትራንስፖርት፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ህወሓት ቢሮ ኣስገብተዋል።
ደብዳቤው
” * መንግስት ይሄ በትእቢት የወጣ መመርያ በቀጥታ ይሰርዝ።
* መንግስት ባጃጆቻቸን ይግዛንና ራሱ ሹፌር ቀጥሮ በመስመር ብቻ ያንቀሳቅሳቸው።
* መንግስት ኣልረከብም የሚይል ከሆነም እስከ 14/04/2008 ዓ/ ም ያሳውቀን።
* ካላሳወቀንና ትራፊክ ፖሊስ ታርጋ ለመፍታት ቢሞክር እስከ ድብደባ የሚደርስ ጥቃት እናደርሳለን።
* ለትግበራው ቢንቀሳቀስና በፖሊስ ሃይል ሊቆጣጠረን ቢሞክርና ለ16ና 17 /04 /2008 ዓ/ም ሰለማዊ ስልፍ እንደምናካሂድ ሊያውቀው ይገባል።
* ሰለማዊ ስልፍ ኣካሂደን ሊመለስልን ካልቻለ ባጃጆቹ በሙሉ ሰብስበን በጎዳናዎች ኣቃጥለን ወደ ምትመኝሉን ስደት እንሄድላቹሃለን። ” የሚል ነው።
የመቐለ ወጣቶች በዚህ መልኩ ቁርጠኝነታቸው በማሳየታቸው መስተዳድሩ ሳይወድ በግድ በትእቢት ተወጥሮ ያረቀቀው መመርያው እንዲተው፣ ካልሆነም እንዲያዘገይ ተገድደዋል።
የመቐለ ባለ ባጃጅ ወጣቶች እምቢታና ዓመፅ በድርቅናውና ህዝብ ባለ መስማት የሚታወቀው የህወሓት መንግስት ኣንበርክከውታል።
‪#‎Oromo_protest‬ ለዚህ የህወሓት መንበርከክና ሳይወድ ወጣቶቹ እንዲያዳምጥ የራሱ ኣወንታዊ ተፅእኖ ኣበርክተዋል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

No comments:

Post a Comment