Tuesday, January 12, 2016

የኢሳት ዜና

በሠርጉ ዕለት ዋዜማ ጭንቅላቱን በጥይት የተመታው መምህር ፍጹም አባተ በመቱ ሆስፒታል ቆይቶ ለቀዶ ጥገና ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተልኮ የሚረዳው አጥቷል። ጥቁር አንበሳ በበኩሉ ምንም እርዳታ ሳያደርግ ወደ አለርት ሆስፒታል ቢልከውም አለርት ሆስፒታል በተመሳሳይ መልሶ ወደ ጥቁር አንበሳ ልኮታል። ተገቢ ሕክምና የተነፈገው ፍጹም ደሙ በየዕለቱ እየቀነሰ ከመምጣቱ የተነሳ በሞት አፋፍ ላይ ነው።
*በአርባምንጭ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ ሁለት ወጣቶች በፌደራል ተይዘው እርቃናቸውን ተደርገው ወደ ማዕከላዊ ተወስደዋል። እነዚህ ወጣቶች ከዚህ በፊት ተይዘው የግንቦት 7 አባል ነኝ ብላችሁ እመኑ ተብለው ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። በርካታ የአርባምንጭ ከተማ ወጣቶች በተመሳሳይ ሁኔታ ግፍ እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ነዋሪዎቹ ይገልጻሉ። ከወር በፊት ተመሳሳይ እስር ሲፈጸም የ70 ዓመት እናት ታስረው እንደነበር ይታወሳል
ኢሳት ሬዲዮን ያድምጡ !

No comments:

Post a Comment