Thursday, January 28, 2016

ጃዋር መሐመድ ተናገረ “ተቃዋሚ ፓርቲዎች መግለጫ ማውጣታቸውን አቁመው ሕዝቡን የማስነሳት ሥራ መስራት አለባቸው” አለ | የሚደመጥ ቃለምልልስ

“የአውሮፓ ሕብረት መግለጫ ለኦሮሞ ሕዝብ ጭቆና ምስክርነት የሰጠበት ነው”

“ተቃዋሚዎች ስም ብቻ ደርድረው መቀመጥ ብቻ አይደለም:: ጠጠር መወርወር አለባቸው”

“መሪ ከላይ ቁጭ ብሎ ታች ያለውን ሕዝብ እንዲህ አድርግ እያለ የሚያዝበት የትግል ጊዜ አልፏል”
“ወያኔ ካሁን በኋላ የኦሮሞን ሕዝብ አስከትዬ እሄዳለሁ የሚል ከሆነ ተሳስቷል”
“የጎንደር ለም መሬት ለሱዳን መሰጠቱን ተከትሎ ሕዝቡ ያነሳውን ተቃውሞ ወደ ጎጃምም እንዲስፋፋ…”
“ይህን ትግል የሚያንቀሳቅሱት ልጆች ከወያኔ በእውቀትም በብልጠትም የተሻሉ ናቸው”
“ለማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲዎች ልምዳችንን ለማካፈል ዝግጁ ነን”

(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር ጃዋር መሐመድ ከሕብር ራድዮ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ ጋር ባደረገው ልዩ ቃለምልልስ ተቃዋሚዎች የመግለጫ ጋጋታቸውን አቁመው ህዝቡ ውስጥ ገብተው እንዲሰሩና በኦሮሚያ ክልል ከተነሳው ሕዝባዊ ቁጣ እንዲማሩ ጠየቀ:: “አሁን ትግሉ ከላይ ቁጭ ብለህ ታች ያለውን ሕዝብ እንዲህ አድርግ እያልክ የምታዝበት ጊዜ አይደለም… ታች ወርዶ መታገልን ይጠይቃል” ያለው ጃዋር በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣ ማቆሚያ የለውም ገና ይቀጥላል ብሏል:: የጎንደር ለም መሬት ለሱዳን መሰጠቱን ተከትሎ ሕዝቡ ያነሳውን ተቃውሞ እንደምሳሌነት ያነሳው ጀዋር የፖለቲካ ፓርቲዎች መግለጫ ማውጣታቸውን ትተው የጎንደርንም; የጎጃምንም ሌላውንም ሕዝብ ወደ ማስነሳቱ ሥራ መግባት ይኖርባቸዋል ብሏል:: ሙሉ ቃለምልልሱን አዳምጡት::http://www.zehabesha.com/amharic/archives/50325
 

Jawar Mohamed

No comments:

Post a Comment