Sunday, January 17, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ራዲዮ የብአዴን ባለስልጣናት የወጣቶች ሊግ እያሉ ያደራጇቸውን ወጣቶች በስብሰባ ጠምደዋቸው ዋሉ፡፡ ———————————————————————



Amdemariam Ezra's photo.
Amdemariam Ezra's photo.

አገዛዙ በአራቱም የአገሪቱ አቅጣጫ የተነሳበትን ህዝባዊ ቅዋሜ እና አርበኞች ግንቦት 7 እያካሄደ ያለውን ሁለገብ ትግል መቋቋም ተስኖት ከላይ ከታች እየረገጠ የሚገኝ ሲሆን በዚህም ጥር 5/2008 ዓ.ም ባህርዳር ከተማ ላይ ከዘጠኙ ክፍለ-ከተመ የተወጣጡ የወጣቶች ሊግ እያሉ ያደራጇቸውን ወጣቶች የብአዴን ባለስልጣናት በስብሰባ በመጥመድ፡-
‹‹በከተማችን የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት በመሰግሰግ በራሪ ወረቀ ቶችን በገፍ እየበተኑ ነው!!እናም ህዝቡን ከእኛ ለይተውታል!! በመሆኑም ይህ ሁሉ ሲሆን እናተ ምን እየሰራቹህ ነው?››እያሉ ያፋጠጡባቸው፣የገላመጡጧቸው መሆኑን ታውቋል፡፡
ይሁን እንጂ ወጣቶቹ የባለ-ስልጣናቱን ቁጣ የተሞላበት ጥያቄ፡- ‹‹ታዲያ ህዝቡ ከእኛ ከተለየ እንዴት አድርገን በግድ ቅረበን እንለዋለን? ደግሞስ እናተ ያል ቻላቹህትን እዴት እኛ ማሳመን እንችላል? ለምን የራሳቹህን ችግር ወደ እኛ ታላካላቹህ?›› በማለት ለባለስልጣናቱ ጥያቄ ጥያቂያዊ መልስ ሰጥተዋል፡፡
በአጠቃላይ ስብሰባው በጫጫታ እና በሁከታ ያላንዳች ስምነት መጠናቀቁን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ራዲዮ ዜና ምንጮች ከቦታው ዘግበዋል፡፡

No comments:

Post a Comment