Monday, January 18, 2016

በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና ሕዝቡ ጥያቄ ስላልተመለሰ ትግሉ ይቀጥላል ብለዋል፣ አገዛዙ ሙስሊሙና ክርስቲያኑን ለማጋጨት አዲስ ዶክመንተሪ ፊልም አውጥቶ የሙስሊሙን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከሽብር ጋር አመሳሰለ፣ አልሽባብ በኢትዮ ኬነያ ድንበር ላይ በርካታ ወታደሮችን መግደሉን እና መማረኩን ገለጸ

Hibir Radio Coverየህብር ሬዲዮ ጥር 8 ቀን 2008 ፕሮግራም
<...አዲሱ የፈጠራ ፊልምን ዶክመንተሪ አልለውም ሙስሊሙና ክርስቲያኑን ለማጋጨት ብለው በከንቱ የደከሙበት ነው …የኢትዮጵያ ሙስሊምና ክርስቲያን ከሃያ አምስት ዓመቱ የወያኔ ስልጣን በፊት ለረጅም ዘመን አብሮ የኖረ ነው። በየጊዜው በህወሃት ማሸበሪያ የውሸት ፊልም የሚጋጭ አይደለም…> ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ <<የማንቂያ ደውል>> ስለተሰኘው የአገዛዙ ዶክመንተሪ አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
በሎስ አንጀለስ የጥምቀት በዓል አከባበር(ቆይታ ከጋዜጠኛ ነጻነት ሰለሞን ጋር)

በዘንድሮ ታክስ አሰራርና የሕክምናና ለበጎ አድራጎት ወጪ የሆኑትን በተመለከተ ሊወሰዱ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች (ውይይት ከአትላንታ ከአቶ ተካ ከለለ የቲኬ ሾው አዘጋጅ ጋር ሙሉውን ያዳምጡት)
<...ከ140 በላይ ንጹሃን ከተገደሉና በርካቶች ከታሰሩ፣ከቆሰሉ ፣በርካቶች ከተደበደቡ በሁዋላ ኦህዴድ ማስተር ፕላኑን ትቼዋለሁ የሚለውን ቀልድ ነው። ማስተር ፕላኑን ትቼዋለሁ ማለት ያለበት ሕጉን ያወጣው የኦሮሚያ ም/ቤት ነው። የኦሮሚያ ክልል አሁንም በወታደራዊ እዝ ስር ነው ።አ መቼ ቀረ?ሕዝቡ ተቃውሞውን ቀጠለው በቂ መልስ ስላላገኘ ነው...ምዕራባውያን ተገቢውን ተጽዕኖ እየፈጠሩ አይደለም። ገዢው ፓርቲ አገሪቱን ወደ አደገኛ ሁኔታ እየመራት መሆኑን ያውቃሉ ችግሩ ያው ጠመንጃ ከያዘው ጎን የመለጠፋቸው ነው። አሁን አገሪቱ መስቀለኛ ሁኔታ ላይ ነች። ሰራዊቱም ቢሆን… > ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦህዴድን ማስተር ፕላኑ ቀርቷልና የቀጠለውን ተቃውሞ በተመለከተ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከአገር ቤት ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

የአሜሪካው ፕ/ት ባራክ ኦባማ የመጨረሻቸው በሆነው በዓመታዊ ንግግራቸው ላይ ያሰሟቸው ታሪካዊ ንግግራቸው እና የቀረቡባቸው ትችቶች (ልዩ ዘገባ)
ሌሎችም

ዜናዎቻችን
አወዛጋቢውን የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር በዚህ ወር እንዲያካልሉ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መመሪያ ተሰጠ
በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ተጠናክሮ ቀጥሏል

ዶ/ር መረራ ጉዲና ሕዝቡ ጥያቄ ስላልተመለሰ ትግሉ ይቀጥላል ብለዋል
የአቶ አንዳረጋቸው ጽጌ የጤንነት ሁኔታ አሳሳቤ እየሆነ መምጣቱን አንድ ታዋቂ እንግሊዛዊ የጤና ባለሙያ አሳሰቡ
“አንዳርቸው ጽጌ ባስቸኳይ ካልተለቀቁ ጤንነታቸው ዳግም ወደ ማይመለስበት ሁኔታ ሊሸጋገር ይችላል”ዶ/ር ቤንጃሚን

በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ረሃብ የአለማቀፉ የግብርና ተቋምን በእጅጉ አሳስቦታል
በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ባልታወቀ ሁኔታ የሞተው ወጣት ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ
አገዛዙ ሙስሊሙና ክርስቲያኑን ለማጋጨት አዲስ ዶክመንተሪ ፊልም አውጥቶ የሙስሊሙን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከሽብር ጋር አመሳሰለ
መምህር ግርማ ወንድሙ ከእስር ከተፈቱ በሁዋላ ተከታዮቻቸውን አመሰገኑ
አልሽባብ በኢትዮ ኬነያ ድንበር ላይ በርካታ ወታደሮችን መግደሉን እና መማረኩን ገለጸ
ኬኔያ በሽብር ቡድኑ ላይ አይቀጡ ቅጣት እርምጃ እንደምትወስድ አስታወቀች

No comments:

Post a Comment