Thursday, January 14, 2016

በዘረኞች ከሚደርስብን ለጆሮ ከሚቀፍ ሰቆቃ ለመላቀቅ የሁላችንንም ተሳትፎ ይጠይቃል

በዘረኞች ከሚደርስብን ለጆሮ ከሚቀፍ ሰቆቃ ለመላቀቅ የሁላችንንም ተሳትፎ ይጠይቃል
በመላው ሃገራችን ስብዕናችንን አዋርዶ፤ ህይወታችንን ዋጋቢስ አድርጎ በባርነት እየገዛን፡ ለመናገር እንኳ የሚሰቀጥጥ ሰቆቃ በመላው ህዝባችን ላይ የሚፈጽመውን የአፓርታይድ ስርዓት
ከጫንቃችን አሽቀንጥሮ ለመጣልና ከቅኝ ግዛት ለመላቀቅ የሁላችንንም (የሁሉንም ክልሎች፡ የሁሉም ሃይማኖት ተከታዮችን) ተሳትፎ ይጠይቃል።

እኛ የ ኢትዮጵያ ህዝብ ሁላችንም በጋራ ተባብረን ለዘመናት አንቆ ከያዘን በጠመንጃና በሃይል ከመገዛት አረንቋ መውጣት አለብን፡ አብዛኛዎቹ የአፓርታይድ ህወሃት መሪዎች ህዝባቸውን፤ አገራቸውን፤ አህጉሯን ጭምር አዋርደዋል ለውድቀት ዳርገዋል። አይወድቁ አወዳደቅ ወድቀወዋል፤ የስንቱን ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሰላምና በተስፋ የመኖር ህልሙን አጨልመዋል።
ይቺን እንደ ሃገር ያለመቀጠልና የመፍረስ አደጋ የተጋረጠባትን ሃገራችንን ለመታደግ መዋቅራዊ ቀውስንና ሰብአዊ ቀውስን ተዛምዶ በጥልቀት መረዳት ያሻል። መዋቅራዊ ቀውስ ኢፍትሃዊ በሆን ማህበራዊና ኢኮኖሚ የሚፈጠር ሲሆን ሰብአዊ ቀውስ ደግሞ ለማንነት ቀውስ፤ ከቤተሰቦቻችን፤ ከማህበረሰባችንና ከብሄራችን ባህርይ እና የሞራል ጥንካሬ ጉድለት የሚመጣ ነው: እኛ ኢትዮጵያውያን ልንክደው የማንችለው ሃቅ ትንሿን ነገር እንኳ እርስ በርስ መከባበር፡ ለሌሎች ዋጋ መስጠት እንኳ ተስኖናል።
በአኝዋክ አንድ ባህላዊ አባባል አለ፡ "ወደ ኮረብታ በመውጣት ምርጥ መሬት አናገኝም" ወደ ኮረብታ ሲወጣ ከፍታ ቦታ ከመደረሱ በፊት በሸለቆና በሜዳ መጓዝን ይጠይቃል። እኛ ኢትዮጵያውያን ከፍታ መሬት ወይም ገዢ መሬት ያስፈልገናል፡ ይህን ለማግኘት ደግሞ ሩቅ መጓዝ ወይም ሩቅ ቦታ ፍለጋ መሄድ እይጠበቅብንም።

ላስታውሳችሁ የምፈልገው ያ ገዢ መሬት ለያንዳንዳችን ከእግዚአብሄር የተሰጠን የመንፈስ ጸጋ ነው። የሞራል ልዕልና ከጎደለን የዘር ጥላቻና ክፍፍል ጠንሳሽና ጠማቂ እንደሆነውና ቅንጣት የስብዕና ርዕይ እንደሌለው እንደ አቶ መለስ ዜናዊ ወደ ቁልቁለት እንዘቅጣለን።
መለስ ዜናዊ ህዝቡን ወደ ተሻለ ህይወት ለመሳደግ ቃል ገብቶ ነበር ነገር ግን ስልጣን ኮርቻው ላይ እንደተፈናጠጠ ወዲያው የተዘፈቀው ወደ ግልጽ ሙስና፤ የውዥንብርና የማጭበርበር ባሀል ማህበራዊ ኢፍትሃዊነት ለሰው ህይወት ዋጋቢስ ማድረግ ነበር።
አሁን እኛ ኢትዮጵያውያን የሚያስፈልገን ከዚህ የተሳሳተ አቅጣጫ የሚመልስን የሚታመን የሞራል አቅጣጫ ጠቋሚ ነው። ይህን ካደረግን በርግጠነት ከዚህ ቀደም በጣት ከሚቀጠሩ እንደ ኒልሰን ማንዴላና ጁሊየስ ኔሬሬ ያሉ ብዙ ጥሩ ጥሩ ኢትዮጵያውያንና አፍረካውያን መሪዎች ማፍራት እንችላለን።
ኢትዮጵያ እንዲሁም አፍሪቃ አዲስ የሚራል ለውጥ ያስፈልገናል፡ ይህን እስካላደረግን ድረስ የሰብአዊ መብት ጥሰቱ፤ የዘር ጥላቻው፤ ክፍፍሉ ይቀጥላል። ለራስ ክብር አለመስጠት ወይም ራስን ማዋረድ ይቀጥላል፡ ይህ የህይወት ኡደት እንዳለ ቀጥሎ ለልጆቻችን ለልጅ ልጆቻችን ይተርፋል፤ አገራችንም አህጉራችንም ከዚህ አዙሪት አትላቀቀም።
እግዚአብሄር ውድ ሃገራችንን ይባርክልን።
obang metho

No comments:

Post a Comment