Thursday, January 21, 2016

ማስተር ፕላኑን ማን አጸደቀው? ማስተር ፕላኑንስ ኦፒዲኦ የማስቆም ስልጣን አለውን? | 5 ጥያቄዎች ለኦህዴድ አባላት

ከ- መርጋ ደጀኔ (ኖርዌይ )
ሲጀመር የአዲስ አበባ ማስተር ፕላኑን ያጸደቀው ወያኔ ነው፡ የማስተር ፕላኑንም አፈጻጸም የሚተገብረው በወያኔ ቁልፍ ሰዎች ነው፡ ሟች ጠቅላይ ሚኒስቴር የማስተር ፕላን አሰራር እንዲሁም በአዲስ አበባ የመሬት ቅርምት ውስጥ ተጠቃሚ የሚሆኑት ማን እንደሆኑ እና ማን በአስፈጻሚነት እንደሚሰሩ ቀድመው የዘረጉት መስመር ሲሆን የሟች ጠቅላይ ሚኒስቴር ራዕይ አስፈጻሚዎች ዛሬም በማስተባበር ላይ ይገኛሉ።
ODDO 4




አዲስ አበባ ሁሌም በህብረት የሚኖሩባት ማንም ከማንም የማይለይባት ኢትዮጵያኖች በአጠቃላይ በአንድነት የሚኖሩባት የአንድነት ተምሳሌነት የነበረች ሲሆን በማህበራዊ ህይወት እንደ እድር፤ እቁብ የመሳሰሉትን በመጠቀም ህብረተሰቡ በደንብ የተዋወቀ እና የአንድነት እና የፍቅር ተምሳሌኔት የሆነች ከተማ ነበረች። ይህችን ከተማ አብረው ተዋውቀው ተሳስበው ህብረተሰቡ በሙሉ በፍቅር ይኖርባት የነበረውን ከተማ በማስተር ፕላን ሰበብ በማፍረስ የጀመሩ የህብረተሰቡን ቤትና ንብረት ብቻ ሳይሆን አንድነቱን ፍቅሩን ኢትዮጵያዊ ጽናቱን ጭምር እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባናል።
መቼስ ከተማ መልማትንም ሆነ ማደግን የሚጠላ ህብረተሰብ አለ ለማለት ባያስደፍርም ልማቱ እና እድገቱ ለማን ነው?የሚለው ጥያቄ ሊመለስ ብቻ ሳይሆን ተመልሶ መሄድ ያለበት ጉዳይ ነው።

OPDO 2
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በልማት ስም ሲፈናቀሉ የተነሱትን ነዋሪዎችን እንደተላመዱት እንደተዋደዱት በአንድ ላይ ከማስፈር ይልቅ በመበታተን እንደ አዲስ ከሌላው ህብረተሰብ ጋር እንዲቀላቀሉ ማድረጋቸው የነበራቸውን አንድነት የማፍረስ ስራ እንደተሰራበት ሊታወቅ ይገባል፡ ወያኔ ሰው ሲዋደድ አንድ ሲሆን አይወድም የሰውን መዋደድና አንድ መሆን የሚጠላ ሰይጣን ብቻ ነው፡ እነዚህ ታዲያ በውስጣቸው ያነገሱት ለኛ የማይታይን ፍቅር የሚጠላ መለያየትን የሚወደውን አንግሰውት ይሆን?
ኦፒዲኦ ማስተር ፕላኑን እንደማይተገበር ብቻ ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ መቆሙን በውሸት ቀለቧ ቴሌቭዥን ETV ላይ ብቅ ብለው ነግረውናል። ለመሆኑ ማስተር ፕላኑን ማጽደቅ ሳትችሉ በመስፋፋቱ ዙሪያ ላይ ሃሳብ ሳትሰጡ አፈጻጸም ላይ እንደ ህዝብ ሰምታችሁ ሳለ ዛሬ እንደ ሙሉ ባለስልጣን ተነስታችሁ ማስተር ፕላኑ ተሰርዟል ብላችሁ ስትናገሩ ትንሽ አይከብዳችሁም ይሄንን ቅጥፈትን ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ አያውቅም ብላችሁ ይሆን ??ስለምን በህዝብ ላይ ቁማር ትጫወታላችሁ ?ጁነዲን ሳዶ ማስታወስ እንዴት አቃታችሁ ጁነዲን ሳዶን ተጠቅመው ከጨረሱ በሃላ እንደ እላቂ ዕቃ ጨርሰው ዛሬ የሚቀምሰውን መከራ ማስታወስ እንዴት አቃታችሁ፡ ጁነዲን ሳዶ የሚገረፈውን  ጸጸትን እንዴት ዞር ማየት ተሳናችሁ? ነገም እናንተ እንደ አለቀ ዕቃ  እንደምትጣሉ እንዴት ረሳችሁት?ስለዚህ ውለታም ከማያውቅ እውነትን ከሌለው የወያኔ አገልጋይ ሆናችሁ በኋላ የህሊና እዳ እንዳይኖርባችሁ ከድርጊታችሁ ትቆጠቡ ዘንድ ሳይመሽባችሁ የህዝብ አጋርነታችሁን ታሳዩ ዘንድ ጥሪ አደርጋለሁ።
OPDO1
ጥቂት ጥያቄ ለኦፒዲኦ፦
እውነት ስልጣን ካላችሁ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እናቀርባለን፡
  1. ማስተር ፕላኑ ያጸደቀው ኦፒዲኦ ነውን?ከሆነ መቼ?እንዴት/ለምን የሚለው መልስ ይመለስ ካልሆነ ደግሞ ያላጸደቀውን ማስተር ፕላን ቆማል ለማለት ማን መብት ሰጣችሁ ?
  2. ወያኔ ጥቅም ላይና ውሳኔ ላይ ሁሌም የበላይ ሆኖ ይቀመጣል ውሳኔዎችንም ይወስናል፡ ውሳኔውንም ህዝብ ሲቃወም ጥቅሙንም ህዝብ ሲያሳጣው ባዘጋጀው መዶሻ ህዝብን መምታት ይፈልጋል ዛሬ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እምቢተኝነት የተነሳው የህዝብ እምቢተኝነት ለመምታት እራሱን ኦፒዲዮ ውስጥ በመቅበር ኦፕዲኦ የተባለውን መዶሻ በማንሳት ህዝብን ለመምታት ሲነሳ እናንተም አዎ መዶሻ ነን ካላችሁ ምንም ጥቅም እንደሌላችሁ ልትቆጠሩ ስለምን እንቢ ማለት አቃታችሁ እንቢታችሁንም ተነጥቃችሃል ወይ ?
  3. እስከ ዛሬ በአዲስ አበባ ዙሪያ የተነሱት ነዋሪዎች የት ደረሱ?ምን ደረጃ ላይ ነው ያሉት? ምንስ ያህል ሰው ተነስታል በምትኩስ በቦታቸው ላይ ምን ተሰራ ?እነማን ሰፈሩ ሙሉውን መረጃ ስለምንፈልግ በተጣራ መረጃ በማቅረብ ለህዝብ ማሳወቅ ትችላላችሁ?
  4. የማስተር ፕላን ውሳኔ በማስተላለፍ ህዝብ እንቢ ሲል ብዙ ግፍና በደል ደርሶበታል ዛሬ ብቻ ሳይሆን ብዙ ዓመታት ከመጀመሪያው ጀምሮ በግፍ የተገደሉትን ኢትዮጵያዊ በትክክለኛ መረጃ ከነቁጥራቸው፡ ሟቾችንንና ተጎጅዎችን ማሳወቅ ይጠበቅባችሃል ለሞቱትም ቤተሰብ እና ለተጎዱት ህብረተሰብ ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፈላቸው ህጋዊ ትዕዛዝ መስጠት አለባችሁ ኦፒዲኦ ይሄንን የህዝብን መብት እና ጥያቄ መመለስ ይችላል?
  5. በማስተር ፕላኑ ዙሪያ ትዕዛዝ በመስጠት ህዝብን የገደሉና ያስገደሉ እንዲሁም በህዝብ ላይ ያልተገባ ዛቻ ያደረጉት ባለስልጣን በሙሉ ለፍርድ የማቅረብ ስራ ከተሰራ ተገቢውን ፍርድ ማሰጠት ከቻላችሁ እና የሰው ደም የጠማውን የወያኔ ጭፍጫፊ ሰራዊት ከኦሮሚያ ክልል ባአፋጣኝ ማስወጣት ይጠበቅባችኋል ይሄ ሳይሆን ግን መግለጫሁ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊቀበላችሁ ይችላልን?።
  6. OPDO
እነዚህን እና ከዚህ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው በህዝብ ላይ የተፈጸመውን በደልና ግፍ መመለስ ከቻላችሁ ያኔ መግለጫዎቻችሁን ህዝቡ በአመኔታ ይቀበላል::
OPDO 5
እንደዝህና የመሳሰሉት ተፈጻሚነት ሳያገኙ ግን ከኦፒዲኦ የሚሰጡትን መግለጫ የወያኔ መዶሻ ሆኖ ህዝብን እንደመምታት ነውና ይታሰብበት፡ የህዝቡን ጥያቄዎች በቀላሉ ካያችሁት ወይንም አሁን በተናገራችሁት መግለጫ ብቻ ማስተር ፕላኑ ሙሉ ለሙሉ ቆሟል በሚል የሚቋጭ መሰላችሁ ካሰባችሁ ተሳስታችሃል ትግሉ የማስተር ፕላን ብቻ ሳይሆን የፍትህ ጭምር ነው፡ ፍትህ የሚፈልግ ሰው ደግሞ ፍትህ እስካላገኘ ድረስ ከትግሉ ማንም አያቆመውም። ለዚህም ከበዳይ ጋር በዳይ ከገዳይ ጋር ገዳይ ከዘራፊ ጋር ዘራፊ ሆናችሁ በስልጣን መቀጠል የት ሊያደርሳችሁ አስባችሁ ይሆንን? ለነጻነቱ ከሚታገለው ህብረተሰብ ጎን በመሆን እራሳችሁንም ነጻ በማድረግ ህዝብ ከሚያነሳው የነጻነት ጥያቄ ጋር መቀላቀል በይፋ የምታሳውቁት መቼ ይሆን?። ሁሉም ሳይረፍድ ወደ እውነት በመምጣት የህዝብን ጥያቄ በመመለስ ዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለመመስረት ትግል ያድርግ ህዝብ ሁሌም አሸናፊ ነው።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
ከ -መርጋ ደጀኔ
21-01-2016

No comments:

Post a Comment