Monday, January 11, 2016

ስምንት ሺህ የሰራዊቱ አባላት በአንድ ዓመት ብቻ በአገዛዙ ዘረኛ አመራር ተማረው ከሰራዊቱ ከድተዋል፣በአመራሩ ላይ እርምጃ የወሰዱ ወታደሮች አሉ፣ሰራዊቱና ሕዝቡ በአንድ ላይ ሲቆሙ ጠመንጃው ወደ ዘረኛው ስርዓት መሪዎች ላይ ይዞራል፣ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊቷን አንገቷን ቀልታ መግደሏ ይፋ ሆነ፣የመን የሴት ቀሚስ ያጠለቁ አራት ኢትዮጵያውያን ወንዶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉዋን ገለጸች፣ግብጽና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከይሮ ላይ ኢትዮጵያን ያገለለ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ፣ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ የቀረበላትን ማሻሻያ ሀሳብ ውድቅ አደረገች፣ዶ/ር መረራና ኢ/ር ይልቃል በጋራ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በውጭ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተው ለሕዝቡ ጥሪ አቀረቡ፣ ቃለ መጠይቅ ከኮ/ል ደረሰ ተክሌ፣ ከአቶ ኦባንግ ሜቶ እና ሌሎችም አሉን

የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ሀብታሙ አሰፋ፣ከላይ አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ኮ/ል ደረሰ ተክሌ፣የአይኤሬስና የታክሲና ቴክኖሎጂ ኩባንያዎቹ ሎጎ፣ሰራዊቱ አባላት ዩኒፎርም ሲቃተል፣የአጋዚ ጦር ለአፈና ተሰማርተው፣የኢራኖች ተቃውሞ በሳውዲ ግድያ ላይ የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ሀብታሙ አሰፋ፣ከላይ አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ኮ/ል ደረሰ ተክሌ፣የአይኤሬስና የታክሲና ቴክኖሎጂ ኩባንያዎቹ ሎጎ፣ሰራዊቱ አባላት ዩኒፎርም ሲቃተል፣የአጋዚ ጦር ለአፈና ተሰማርተው፣የኢራኖች ተቃውሞ በሳውዲ ግድያ ላይ


የህብር ሬዲዮ ጥር 1 ቀን 2008 ፕሮግራም

<...በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ላይ በአገር ቤትና በውጭ የተደረገው የጋራ ውይይት ላይ ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በጋራ ተሰብስበው ጠቃሚ ውይይት አድርገዋል... ጊዜው በጋራ የምንቆምበት በጋራ ሊያስማሙን የሚችሉ ጉዳዮች ላይ በአንድ ላይ በአንድ ላይ በመቆም አገሪቱን ከችግር የምንታደግበት ወቅት ላይ ነው > አቶ ከባዱ በላቸው የሰማያዊ ፓርቲ በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳይ ላይ በአገር ውስጥና ከውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስላደረጉት የጋራ ውይይት እና የሰማያዊና የመድረክና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ተገኝተው ስለሰጡት ማብራሪያ አስመልክቶ ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)
<...ትላንት አማራው በበደኖና በተለያዩ ቦታዎች ተገደለ፣በደቡብ እንዲሁ በሸኮ መዠንገር ጎሳ ላይ አሰከፊ ግድያ ተደረገ፣በጋምቤላ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ የተወሰደው ጭፍጨፋ አይዘነጋም፣በሌሎችም ቦታዎች በስርዓቱ የተደረጉ ጭፍጨፋዎችን ማንሳት ይቻላል ዛሬ ደግሞ የኦሮሞ ተወላጆችንእየገደሉ ነው። በአንድ ላይ እስካልተነሳን ተራ በተራ እንዲህ ያለው ግድያ አይቀርም...ኢትዮጵያውአን መነጋገር መጀመር በጋራ መወያየት አለባቸው። ለመተማመን እንነጋገር ብለናል።የሰማያዊ ድጋፍ ሰጪ የጀመረው የጋራ ውይይት በሌሎችም ቦታዎች ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። በተቃዋሚው መካከል ብሄራዊ መግባባት ብሄራዊ እርቅ ማድረግና በጋራ መቆም እስካልተቻለ ግን...>
አቶ ኦባንግ ሜቶ የትብብር ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን አዳምጡት)
<...ብዙሃኑ የሰራዊት አባል ሆን ተብሎ መረጃ እንዳያገኝ የተነፈገ፣በሕወሃት ወታደራዊ መሪዎች ዘረኛ እርምጃ የተማረረ፣በተለያዩ ጊዜ ከዚህ ሰራዊት እየከዱ፣በአመራር ላይ ጭምር እርምጃ የሚወስዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የህወሓት መሪዎች ቀኝ እጅ ከሆነው አጋዚ ጋር ማመሳሰል አይገባም ሰራዊቱ ከሕዝቡ ጋር የሚሰለፍ ጠመንጃውን ወደ ዘረኛ መሪዎቹ በቃ ብሎ እንዲያዞር ሕዝቡና የሚመለከታቸው የለውጥ ሐይሎች በቂ መረጃ መስጠት አለባቸው...ሰራዊቱ ልቡ ከማን ጋር እንዳለ በምርጫ 97 አሳይቷል።ዛሬም...> ኮ/ል ደረሰ ተክሌ የመከላከያ የዕቅድና ምርምር ሀላፊ የነበሩ ሰራዊቱ በኦሮሚያ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ በተመለከተ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ( ቃለ መጠይቁን ያዳምጡ)
<...የታክስ ጉዳይ በጥንቃቄ መታየት አለበት። በ1099 ተጨማሪ ገቢ ያገኙ የሁበርና ሊፍት አሽከርካሪዎች ታክስ በሚያሰሩበት ጊዜ ሊወስዱት ጥንቃቄ አለ...አይ ኤር ኤስ በታክስ ጉዳይ ላይ ጥያቄ ካለው በግልጽ ደብዳቤ ይልካል እንጂ እንደነዚህ በስልክ እየደወሉ ከአይ፣ኤርኤስ ነን እያሉ እንደሚያጭበረብሩት አይደለም ከነዚህ ሕዝባችን መጠንቀቅ አለበት...> አቶ ተካ ከለለ ከአትላንታ የቲኬ ሾው አዘጋጅ ስለወቅቱ የታክስ ጉዳይ ካነሱት ጥያቄ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)

ሳውዲ አረቢያ ታዋቂው የሺያት ሙስሊም የሃይማኖት መሪ ሼክ ኒሚር አል ኒምርን ጨምሮ 47 ስዎችን መግደሏን ተከተሎ በኢራን እና በሳውዲ አረቢያ መካከል ሰሞኑን የተጋጋመው አካባቢያዊ እና ዓለማቀፋዊ የደፕሎማሲያዊ ቁርቋሶ(ልዩ ጥንቅር) ሌሎችም
ዜናዎቻችን
ስምንት ሺህ የሰራዊቱ አባላት በአንድ ዓመት ብቻ በአገዛዙ ዘረኛ አመራር ተማረው ከሰራዊቱ ከድተዋል
በአመራሩ ላይ እርምጃ የወሰዱ ወታደሮች አሉ
ሰራዊቱና ሕዝቡ በአንድ ላይ ሲቆሙ ጠመንጃው ወደ ዘረኛው ስርዓት መሪዎች ላይ ይዞራል
ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊቷን አንገቷን ቀልታ መግደሏ ይፋ ሆነ
የመን የሴት ቀሚስ ያጠለቁ አራት ኢትዮጵያውያን ወንዶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉዋን ገለጸች
ግብጽና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከይሮ ላይ ኢትዮጵያን ያገለለ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ
ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ የቀረበላትን ማሻሻያ ሀሳብ ውድቅ አደረገች
ዶ/ር መረራና ኢ/ር ይልቃል በጋራ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በውጭ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተው ለሕዝቡ ጥሪ አቀረቡ

ኤርትራ 400 ወታደሮቿን ወደ የመን ልካ ጦርነቱን መቀላቀሏ አነጋጋሪ ሆኗል
በኦሮሚያ የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተማጋቾችና በሚዲያው ትኩረት እያገኘ መጣ
ሌሎችhttp://www.zehabesha.com/amharic/archives/49902ም ዜናዎች አሉ


No comments:

Post a Comment