Saturday, January 9, 2016

ወገኖቼ እባካችሁ ለዘ-ህወሀት አምባሳደሮች እርጥባን ብትሰጡልኝ! ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

ከጥቂት ቀናት በፊት በውጭ ሀገር የሚኖሩ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ዴፕሎማቶች ከፍተኛ የሆነ ዓለም አቀፍ የውጭ ምንዛሬ የገንዘብ ፍሰት ችግር ውስጥ ተቀፍድደው የሚገኙ መሆናቸውን የሚገልጽ አሳዛኝ የሆነ ጽሁፍ አነበብኩ፡፡
http://ecadforum.com/Amharic/archives/16061/
Can You Spare a Dime for T-TPLF Ambassadors?
በብርሀን ፍጥነት በአንድ ጊዜ ከወባ ትንኝ ተመራማሪነት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት እንደተተኮሰው እንደ ቴዎድሮስ አድኃኖም ዘገባ በውጭ ሀገር የሚገኙት የኢትዮጵያ ዴፕሎማቶች የውጭ ምንዛሬ ገንዘብ ለማግኘት ባለመቻል በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀው እንደሚገኙ ይፋ ሆኗል፡፡
አድኃኖም ስለውጭ ምንዛሬ የገንዘብ ፍሰት ችግሩ ከፍተኛ በሆነ መልኩ በማማረር እንዲህ የሚል ዘገባ ለይስሙላው ፓርላማ ተብዬው አቅርቧል፣ “በያዝነው ዕቅድ መሰረት በበጀት ዓመቱ መቶ በመቶ የተሳካ አፈጻጸም እንደምናስመዘግብ እናውቅ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይህንን ለማድረግ እንዳንችል የሚከለክል ከፍተኛ ችግር ተደቀነብን…የዴፕሎማሲያዊ ተልዕኳችንን በአግባቡ እንዳንወጣ እና በተለይም በየኤምባሲዎቻችን እና በየኮንሱላር ጽ/ቤቶቻችን ዕቅዶቻችንን እንዳናሳከ አንዱ ከፍተኛ ችግር ሆኖ የቀረበው የውጭ ምንዛሬ ያለማግኘት ሲሆን በዚህም ችግር በከፍተኛ ሁኔታ በመሰቃየት ላይ እንገኛለን“ ብሏል፡፡
“በውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር መሰቃየት“ የሚለው ስተሮገም  “በገንዘብ ችግር ምክንያት እንዳንንቀሳቀስ እጅ ከወርች ተጠፍንገን ተይዘናል የሚለውን አባባል ይመስላል! ዓላማዎቻችንን ለማሳካት አንችልም፡፡ ይህንን ቆጥቋጭ ቁንጥጫ እየቀመስነው ነው፡፡ ያለችንን የውጭ ምንዛሬ ዶላር አሟጥጠን በመጠቀም ከችግር ላይ ስለሆንን ስኬታማ ልንሆን አልቻልንም፡፡ የዴፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ስራዎቻችን ሁሉ ዋጋቢስ ሆነዋል፡፡ ስለሆነም በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀን እንገኛለን፡፡“  ማለት ነው ::

ከሁሉም በበለጠ መልኩ አድኃኖም እንዲህ ይላል፣ “ዴፕሎማቶቻችን የፈረንሳይን ኮኛክ ለመግዛት የገንዘብ አቅም አይኖራቸውም፣ ስለዚህ ምንም ዓይነት ኮኛክ የለም፣ ምንም ዓይነት ጆኒ ወከር የለም፣ ምንም ዓይነት ስኮች ብሉ የለም፡፡“
በመጨረሻም በዘ-ህወሀት ዴፕሎማቶች ላይ ሰማይ ከስሩ ተመንግሎ ወድቆባቸዋል፡፡ ለዘላለም፣ ለዘላለም፣ ለዘላለም፣ ለዘላለም…
እስቲ ጎበዝ!  የዘ-ህወሀትን ዴፕሎማቶች ስቃይ ለማስወገድ ምን መደረግ ይችላል?
እነርሱን ለመርዳት ምን ማድረግ አለብኝ?
ደህና፣ የመጀመሪያው ምላሸ እንዲህ የሚል ነበር፣ “ለምን ኬክ አይበሉም?“
ማለቴ የእነርሱ የዴፕሎማሲ ተልዕኮ አስፈጻሚዎች በሚገኙባቸው ሀገሮቸ ሁሉ ለምን ገንዘብ እንደ ወረቀት እያተሙ እንደ ሰካራም መርከብ ነጅ ከኪሳቸው እያወጡ አይበትኑትም?
ዘ-ህወሀት ገንዘብ የሚያጠፋው ልክ እንደሚያትመው ተራ ወረቀት ነው፡፡ ጉድ እኮ ነው! ገንዘብን እንደ ወረቀት እንደፈለጋቸው ያትማሉ! ስለሆነም ሁሉንም ጥቅላይ ሊሆን የሚችል በርካታ ገንዘብ አትሙ፡፡ ዝም ብሎ ገንዘብ ማተም ነዋ!  ምን  ችግር አለ !
በእርግጥ የአሜሪካንን  ዶላር ገንዘብ ወይም ደግሞ የዩሮን ገንዘብ እንደ ወያኔ ወረቀት ብር ማተም አይቻልም፡፡ እነዚህ ገንዘቦች ስራ ተሰርቶ የሚገኙ ናቸው፣ ወይም ደግሞ የውጭ ምንዛሬ ግብይት በሚደረግባቸው የውጭ ምንዛሬ ገበያዎች ላይ ብቻ በልውውጥ የሚገኙ ናቸው፡፡
ታላላቆቹ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ የግብይት ስራዎችን በማቀላጠፍ በትሪሊዮኖች የሚቆጠሩትን የዶላሮችን እና የዩሮዎች ገንዘቦችን የቀን ከቀን አንጻራዊ የልውውጥ ዋጋ ይወስናሉ፡፡ ወዲያው በአንድ ጊዜ እንደሚደረግ ልውውጥ፣ እንደ ልውውጥ ገንዘቦች እና እንደ ሌሎች የግብይት ቁሶች ሁሉ ሁሉም ዓይነት የንግድ ስምምነት አላቸው፡፡
ግልጽ በሆነ መንገድ የውጭ የገንዘብ ምንዛሬው ገበያ ለዘ-ህወሀት ዴፕሎማቶች እንደ መና ከሰማይ ሊወርድላቸው አልቻለም፡፡
ከዓለም አቀፍ እርዳታ ሰጭ እና አበዳሪ ድርጅቶች የዘረፉትን እና ጨረታ ባልወጣባቸው የኮንትራክት ስምምነቶች ላይ ያግበሰበሱትን ጉቦ እና ቁሳዊ ሀብትስ እንዴት ለዘ-ህወሀት ዴፕሎማቶች የውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር ለመጠቀም አልቻሉም?
ያንን ማንም ሊያደርግ አይችልም፡፡
በኢትዮጵያ የወሮበሎች የገነት ዓለም ውስጥ ደቂቃ በደቂቃ፣ ሰዓት በሰዓት ስለስልጣን እና ስለገንዘብ፣ ስለገንዘብ እና ስለስልጣን ነው፡፡ ስለሌላው ጉዳይ እርሱት!
ደህና፣ ለአስር ዓመታት ያህል ከባለሁለት አሀዝ የምጣሄ ሀብት የቅጥፈት ዕድገት እየተባለ ሲመዘበር የቆየውስ ገንዘብ እንዴት ለእንደዚህ ዓይነቱ ችግር ለመዋል አልቻለም?
እ.ኤ.አ ጥቅምት 2015 የዘ-ህወሀት ኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ተሾመ ባቀረበው ዘገባ “የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ስኬታማ በሆነ መልኩ አጠናቀናል… ከቅርብ ዓመታት በፊት ስናስመዘግበው የነበረውን ባለሁለት አሀዝ የምጣኔ ሀብት ዕድገት አሁንም ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በ11 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ቀጣይነት፣ ፈጣን እና ባለሁለት አሀዝ ዕድገት እናስመዘግባለን“ ብለዋል፡፡
“ከቅርብ ዓመታት በፊት ስናስመዘግበው የነበረውን ባለሁለት አሀዝ የምጣኔ ሀብት ዕድገት” እና “በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት 11 በመቶ ዕድገት”! እንዴት ያለ የሚገርም ነገር ነው እባካችሁ! የዘ-ህወሀት ወፍራም ድመቶች በገንዘብ እጥረት ምክንያት ባህር ውስጥ እየሰጠሙ ነው፡፡
አዝናለሁ፣ እዚያ ምንም ዓይነት ገንዘብ የለም፡፡ ሁሉም ነገር ሀሰት ነው፣ ተራ ቅጥፈት እና የቁጥር ጨዋታ ነው!
ባለፈው ዓመት አድኃኖም ኢትዮጵያ ድህነትን ለማጥፋት እና እ.ኤ.አ በ2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ውስጥ እንደምትሰለፍ ተናግሮ ነበር፡፡
በቅርብ ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ውስጥ የምትሰለፍ አንድ ሀገር በውጭ ሀገር የሚገኙትን የአምባሳደሮቿን መሰረታዊ ወጭ ሊሸፍን የሚያስችል ወጭ ማሟላት እንዴት ይሳናታል?
አዎ! አድኃኖም አምባሳደሮቹን “እየተሰቃዩ” ነው ይላል፡፡ በችግር እጅ ከወርች ተጠፍንገው ተይዘዋል፡፡ በውጭ ሀገር የሚገኙት የዘ-ህወሀት ዴፕሎማቶች ምንም ዓይነት ገንዘብ የላቸውም፡፡
የዴፕሎማቶችን የገንዘብ እጦት ስቃይ ለማስወገድ ዘ-ህወሀት ለታላቁ የህዳሴ ግድብ እያለ በልመና ሲሰበስብ ሲበዘብዙ ከቆየው ገንዘብስ እንዴት መጠቀም አልቻለም? በሚሊዮን የሚቆጠር ጥቂት ዶላር የማግበስበሻ ሆዳም ባንኮች (የዓሳማ ባንክ አላልኩም) ውስጥ አለ፡፡
በዚህ ባለፈው መስከረም ወር ዘ-ህወሀት እንዲህ ብሏል፣ “የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ“  ወደ 600 ሚሊዮን ብር ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ለግሷል፡፡ ያንን ለጊዜው የተቀመጠውን ገንዘብ  ትንሽ ቀንጥበው አይጠቀሙበትም ?
ይህንን ማንም ሊያደርገው አይችልም! ያ ገንዘብ በነፋስ ተወስዷል፡፡
(ያ ገንዘብ ከአሜሪካ ወይም ደግሞ ከአውሮፓ አግሩን አላወጣም አላልኩም ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ለዘ-ህወሀት አለቆች ላስፈላጊ ጊዜ (የዝናብ ቀን) በአሜሪካ እና በአውሮፓ ባንኮች ውስጥ ተቀምጧል አላልኩም፡፡ ስለዝናብ ቀን ከተነጋገርን ዘንድ ዘ-ህወሀት አደገኛ ዝናብ እየዘነበበት መሆኑን መገንዘብ ይኖርበታል፡፡ ጊዜ ፊቷን እያዞረችበት ነው፡፡ በጣም አደገኛ፣ አደገኛ፣ አደገኛ የሆነ ዝናብ እየዘነበበት ነው፡፡ ከዚህ አደገኛ ዝናብ በኋላ የሚከተል ምንም ዓይነት ጎርፍ የለም፡፡ እግዚአብሄር ለኖህ የቀስተደመና ምልክት ሰጠው፡፡ ከዚያ በኋላ ምንም ዓይነት ውኃ የለም፣ በቀጣይም እሳት ይመጣል አለው ።  ይኸ ትንቢት በአሜሪካ የጥጥ እና የትምባሆ ልማት እርሻ ስራ ከአፍሪካ በባርነት እየተጫኑ ወደ አሜሪካ እየተጋዙ በስቃይ መከራን ሲያሳልፉ ለነበሩት ባሮች የተነገረ እና የሚዘመር የግጥም መዝሙር ነበር፡፡
ዘ-ህወሀት ከአሜሪካ በሚሰበሰብ ቁርጥራጭ ሳንቲም በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ግዙፍ ግድብ እገነባለሁ ብሎ የተነሳ ድርጀት ነው፡፡
ዘ-ህወሀት ለወደፊት ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚያስችለው እንዲህ የሚል መፈክር ቢጠቀም ጥሩ ነው ፣ “ለግድቡ ስራ ቤሳ ሳንቲም ማውጣት ትችላችሁን?“
በእውነት ከዚህ በኋላ ምንድን ነው መደረግ ያለበት?
ብቸኛ የቀረው መንገድ ቢኖር ቆብን አውልቆ መንገድ ላይ በመጣል እነርሱ የደርግን ሰራዊት በየመንገዱ እያሰለፉ ሲያደርጉት እንደነበረው ሁሉ መለመን ነው ብዬ እገምታለሁ፡፡ ለዘ-ህወሀት የልመና ባለሙያዎች ሽንጣቸውን ገትረው ልመናቸውን ማጧጧፍ እንዳለባቸው ሁላችንም እንፈልጋለን፡፡ ይቅርታ፣ ዴፕሎማቶች በእንዱስትሪ ከበለጹ ሀገሮች እርዳታ እና ብድር መለመን ዋና ስራቸው የሆኑትን  ማለቴ ነው፡፡
ዘ-ህወሀት ለመለመን ምንም ዓይነት ኩራት የለውም፡፡ “የለማኝ መንግስት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ አዘጋችቼ የነበረውን ትችቴን ማንበብ ትችላላችሁ፡፡
አድኃኖም በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት በከፍተኛ ሁኔታ በገንዘብ ችግር እርኃብ ተወጥሮ ይገኛል ብሏል፡፡ (በአሁኑ ጊዜ 15 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሚልሱት የሚቀምሱት አጥተው በረኃብ ችግር ውስጥ ተወጥረዋል አላልኩም፡፡)
አድኃኖም በውጭ ላሉት አምባሳደሮች እና የዴፕሎማሲ ሰራተኛ ወንድሞች እና እህቶች የሚሆን ቤሳ ሳንቲም፣ ቁራጭ ገንዘብ ወይም ሌላ ምጽዋት በመጠየቅ (በመለመን አላልኩም) ላይ ይገኛል፡፡ ጥቂት የቻምፓኝ፣ የኮኛክ እና የውስኪ ጠርሙሶችን ለማግኘት ጥቂት ገንዘብ ይፈልጋሉ፡፡ በእርግጥ በአሁኑ ጊዜ እነዚህን ጠንካራ መጠጦች የሚፈልጓቸው ለማረፍ፣ ለመዝናናት እና ለመልካም መስተንግዶ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን እነዚህን መጠጦች በአሁኑ ጊዜ የሚፈልጓቸው ተጋርጦባቸው ያለውን ችግር ለመርሳት በማሰብ ነው፡፡
አዎ! ትክክል ነው፡፡ ዘ-ህወሀት በ”መሰቃዬት” ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብም በመሰቃየት ላይ ይገኛል!
ሌላስ? በውጭ ሀገር ለሚገኙ ደኃ እና በመሰቃየት ላይ ለሚገኙ የዘ-ህወሀት ዴፕሎማቶች እርጥባን ስጡ እባካችሁ!
እነዚህ ዴፕሎማቶች ዘርፈው ይበላሉ የሚል ተስፋ የለኝም፡፡ እ.ኤ.አ ጥቅምት 2014 በዋሽንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው የዘ-ህወሀት ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተኩስ የከፈተውን “ዲፕሎማት” ታስታውሳላችሁ? ስለዚህ ጉዳይ “የህወሀት የወሮበላ ዴፕሎማሲ“ በሚል ርዕስ ስለጉዳዩ የሚዘግብ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡
ነገሮች ሁሉ ገፍተው የሚመጡ ከሆነ እና የገንዘብ ማግኛ መንገዱ ሁሉ ደረቅ ሆኖ የሚቀጥል ከሆነ እነዚህ ሰዎች ከዴፕሎማሲያዊነት ወደ ወሮበላ ዴፕሎማሲያዊነት ሊሸጋገሩ ይችላሉ፡፡ ይህንን ነገር በአንክሮ ተመልከቱት እላለሁ!
እ.ኤ.አ ጥር 2/2016 የህወሀት ፕሬዚዳንት የሆኑት ተሾመ በብሄራዊ ቤተመንግስት በመገኘት አዲስ ለተሾሙት አምባሳደሮች የሽኝት ስነስርዓት ላይ ንግግር አድርገው ነበር፡፡ በዚያ የሽኝት ስነስርዓት ላይ አዲስ የተሾሙ አምባሳደሮችን እንኳን ደስ ያላችሁ በሄዳችሁበት ተልዕኮም ስኬታማ እንድትሆኑ እመኛለሁ ብለው ነበር፡፡ ተሾመ ይህንን ያለው በእውነት ሊሆን አይችልም!   ይህንን የሚለው የዴፕሎማቲክ ተልዕኮ አስፈጻሚዎች በታላቅ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የሚጠቁመውን የአድኃኖምን ማስታወሻ አላገኘም ማለት ነውን?
ተሾመ እንደዚያ በማለት ዴፕሎማቶችን ሲያሰናብት ችግር የሌለበት ዴፕሎማሲያዊ ተልዕኮን እንደሚያሳኩ አድርገው የላካቸው ይመስላል፡፡
አድኃኖም በዚያው የሽኝት ስነስርዓት ላይ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ እንዲገነቡ እና ኢትዮጵያ እያስመገበች ያለውን የምጣኔ ሀብት ዕድገት እና ልማት እመርታ ማሳወቅ እንዳለባቸው ጠቁሟል፡፡
በእርግጠኝነት! አምባሳደሮቹ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ችግር ውስጥ አይደሉም እናም እውን ስለምጣኔ ሀብት ዕድገቱ እና ልማቱ ሽግግር የፕሮፓጋንዳ ስራ ሊሰሩ ይችላሉን? (ይልቁንስ ወደ ለማኝነት ስለሚደረገው ሽግግር የፕሮፓጋንዳ ስራ ቢሰሩ የተሻለ ይመስላል፡፡)
ይህ ጉዳይ በዘ-ህወሀት ፕላኔት (ምድር) ላይ በዘ-ህወሀት አምባሳደሮች ብቻ ሊሰራ ይችላል!
ለማሰብ ያህል! “በውጭ ሀገር የሚገኙ የዘ-ህወሀት የዴፕሎማሲ አስፈጻሚዎች በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት እየተሰቃዩ የሚገኙ ከሆነ በሀገር ውስጥ የሚገኙት የዘ-ህወሀት አለቆች በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ምን ይህል ይሰቃዩ ይሆን?“
እ.ኤ.አ መስከረም 2015 ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ያወጣውን ዘገባ መስመር በመስመር እየተከታተልን በአንክሮ ብናነብ ዘ-ህወሀት በጣም በአስጊ ችግር እጅ ከወርች ተጠፍንጎ ተይዞ እንደሚገኝ እንገነዘባለን፡፡ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ስለዘ-ህወሀት እንዲህ ይላል፣ “የመካከለኛ ጊዜ ዓላማው ለቀጣዩ ዓመት ወደ ሀገር ውስጥ ገቢ ለሚሆኑ ምርቶች እና አገልግሎቶች ማስፈጸሚያ የሚሆን ለሶስት ወራት ያህል ሊያቆይ የሚችል የውጭ ምንዛሬ ክምችት ማግኘት ነው፡፡“
በሌላ አባባል በአጭር ጊዜ ውስጥ ዘ-ህወሀት ገነትን በሚያጠፋው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ውስጥ እጅ ከወርች ተጠፍንጎ ይገኛል፡፡
ያም ሆነ ይህ ዘ-ህወሀት ዴፕሎማቶች ኮሮጃቸዉን ይዘው መገድ ዳር ሲለምኑ ብታገኗቸው አባካችሁ እርጠቧቸው፡፡
ለነፍሳችሁ ይሆናችዋል!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ታህሳስ 29 ቀን 2008 .

No comments:

Post a Comment