Barak Obama of The White House says no to US ground forces to combat Shabaab: “We don’t send our marines in to do the fighting. The Ethiopians are tough fighters.”በሶማሊያ ምድር በአልሸባብ ለተገደሉ ለተማረኩ ወታደሮች ቤተሰቦች እንኳን ካሳ ሊከፈል የጡረታ መብት አልተከበረላቸውም::የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነቱን እንዳይጎናጸፍ አሜኬላ እሾህ ከሆኑት አንዱ የአሜሪካ መንግስት እና መሪዎች ናቸው:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
…… አሉ እርሳቸው እርግጥ አቋማቸው ያው ነው የውጪ ጉዳይ ፖሊሲያቸውም አልተለወጠም::ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አለም አቀፍ ደሆችን እና መንግስታቶችን አስመልክቶ የተናገሩት እንዳለ ነው::የአሜሪካ ብሄራዊ ጥቅም እስከተከበረ ድረስ በማንኛውም የአምባገነን አገዛዝ ሂደት ውስጥ እጃቸውን እሳቸው ይሁኑ አገራቸው እንደማያስገቡ….ስለምርጫ እና ዲሞክራሲያዊ ተግባራት ይልቅ የደሆች መሰረታዊ ፍላጎት መጠበቅ አለበት ከዛ በኋላ ህዝቡ ራሱ ነጻነቱን መፈለግ ይችላል እንጂ አሜሪካ … ምናምን .. ጣልቃ አትገባም .. ይህ የኦባማ ፕሪንሲፕል አሁንም ጽኑ እንደሆነ ከስልጣን ሊሰናበቱ ነው::
ታዲያ የአሜሪካ ጥቅም እስከተከበረ ድረስ የኢትዮጵያ ደሃ ወታደር በሶማሊያ ምድር ቢያልቅ ምን አገባቸው::ወታደር ማለት የአንድ ሃገር ሉአላዊነት አካል ነው::ይህን ደሞ ኦባማም ያምናሉ::ስለዚህም ነው የአሜሪካ ወታደሮች ወደሶማሊያ አይላኩም የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ ተልከው ያልቃሉ:: የኢትዮጵያ ወታደሮች ምርጥ ተዋጊዎች ናቸው::የአሜሪካ ምርጥ ተዋጊዎች አይደሉም? ማነው በዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ የሰለጠነው? በደሃው የኢትዮጵያ ወታደር ደም የአሜሪካ ጥቅም ማስጠበቅ ሌላ ሕዝባዊ ጥያቄ እንዲነሳ በሩን ያንኳኳል::ከዚሁ ጋር በተያያዘ የደሃው ወታደር ደም በሽብርተኝነት መዋጋት ሰበብ ለአሜሪካ ጥቅም የተገበሩ ወታደሮች ጎን ለጎን የወያኔ አምባገነን ሌቦች ስልጣን እንዲረዝም ሌላ አስታውጾ አድርጓል::የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነቱን እንዳይጎናጸፍ አሜኬላ እሾህ ከሆኑት አንዱ የአሜሪካ መንግስት እና መሪዎች ናቸው::ይህንን ደሞ በጋራ ልንታገለው እና ልናሸንፈው የሚገባ የኛ የኢትዮጵያውያን የውስጥ ጉዳይ ነው::የአሜሪካ መንግስት ብሄራዊ ጥቅሙ እስካልተነካ ድረስ ወያኔ 100 አመት ስልጣን ላይ ቆይቶ ቢያስር ቢገድል ቢያሳድድ አይመለከተውም::በተዘዋዋሪ ደሞ እንደ ኦባማ አይነቱ ብሄራዊ ጥቅሙን ለማስከበር የሚሄድበት መንገድ የአምባገነኖችን እድሜ ማራዘሚያ የፖለቲካ ስልት ነው::
የደሃው ወታደር ደም በሶማሊያ ምድር በአልሽባብ ጥይቶች ሲዝራ ከአሜሪካ የሚመጣው ዶላር ኪሳቸውን የሚያደልበው ይወያኔ ባልስልጣናትን ነው:;በሶማሊያ ምድር በአልሸባብ ለተገደሉ ለተማረኩ ወታደሮች ቤተሰቦች እንኳን ካሳ ሊከፈል የጡረታ መብት አልተከበረላቸውም::ከዚሁ ዘመቻ ጋር በተያያዘ እጅግ ከፍትኛ ችግር ውስጥ የገቡ በሺዎች የሚቆጠሩ የደሃው ወታደር ቤተሰቦች ቤት ይቁጠረው::ስለዚህ ወታደሮች ይሁን ቤተሰቦቻቸው ይህንን የአሜሪካንን ጥቅም ለማስከበር ለኢትዮጵያ ፋይዳ አልባ ለሆነው ጦርነት ራሳቸውን አስልፈው ከመስጠታቸው በፊት ሊያስቡበት እና ሊመክሩበት ይገባል::አሜሪካ ብሄራዊ ጥቅሟን ከፈለገች ወታደሮቿን ታዝምት::በደሃው ወታደር ደም የአሜሪካ ጥቅም የወያኔ ስልጣን ሊጠበቅ ነው? እስከመቼ ? በጋራ ቆመን በመቻቻል መንፈስ እየታገልን ነጻነታችንን እናረጋግጥ !!! #ምንሊክሳልሳዊhttp://www.mereja.com/amharic/462106
No comments:
Post a Comment