ካመረርን እና በአንድነት ከተነሳን ነፃነታችን በእጃችን ነው፡-
የ25 ዓመቱን የመበቃቀል፣የግፍና የመከፋፍል ቀንዲል የሆነውን የወንበዴዎች ቡድን ከስልጣን በማውረድ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች (ዘረኛና ግፈኞችን ጨምሮ) በእኩልነት የሚኖሩባት፤ የነፃ አስተሳሰብና የብልፅግናዋ ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑባት እና ዘመናዊ አስተዳደር የሰፈነባት ሀገር አንዲኖረን የእያንዳንዳችን የጋራና የተናጠል ትግል አስተቃፅኦን ይፈልጋል፡፡ ስለ ታላቋ ሀገራችን ያለንን አመለካከት ገምግመን እራሳችንን እንይና እንመርምር፡፡የአንደነት ሀይሉም ጭምር ለስልጣን፣ለዝናና ክብር ሳይሆን ለለውጥ መቆሙን ይመርምር፡፡ከዛም ቀጥሎ ተገቢውን እርምጃ እንውሰድ፡፡ ስንት ዘመን፤ ስንቶቻችን አንገታችንን ድፍተን መኖሩ እንዳልጠቀመን ከህሌናችን በላይ ምስክር አያስፈልገንም፡፡ ትግላችንን ወደ ማይቀረው የነፃነት አደባባይ በአጭር ጊዜ ለማድረስ መወሰን፣መንቀሳቀስ፣መናበብና በአንድንት መሥራት ይጠበቅብናል፡፡
ይህን የሚጠበቅብንን የትግል አስተዋፅኦ ለማበርከት የሚከተሉትን ተግባራት በጋራ እና በተናጠል ብንተገብር ድላችንን እናፋጥናለን፡
1. የተባበረ የትግል ምዕራፍ እና የነፃነት ታጋዮች ጥምረት በመመስረት በስልጣን ላይ ያለውን ዘረኛና አምባ ገነን ቡድን መጋፈጥ እንጀምር፡፡ የተበታተነ ትግል ነፃነታችንን ሊያመጣልን ዋስትና የለውም፡፡
ለምሳሌ፡- በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉ የትግል እንቅስቃሴዎችን እውቅና በመስጠት ትግሉን በመቀላቀል፣በገንዘብ፣ በመረጃና ሌሎች ጠቃሚ ግባቶች ልንደግፍ ይገባናል፡፡
2. ጠላቶቻችንን አነማን እና ምን ላይ እንደሆኑ ማወቅና መለየት የመጀመሪያው ሲሆን ተባባሪዎቻቸው እነማን እንደሆኑ እና እነሱ የሚጠቀሙበት የአፈና (የጭቆና አገዛዝ) ስልት መረዳት ይኖርብናል፡፡ የሚቆጣጠሯቸውን ተቋማት እና አነዚህን ተቋማት የሚደግፏቸውን፣የሚመሯውንና የሚያስተዳድሯቸውን ግለሰቦች መለየት ያስፈልጋል፡፡
3. ማንኛውም በቅርብ ክትትል የማይደረግበት ዜጋ ከሆንክ ከማህበረሰቡ ጋር በምልክትና ሌሎች መንገዶች ሀሳብና መረጃ ተለዋወጥ፡፡ ሲነቁብህ እራስህን ከመረጃ ምንጭነት ተቀባይ ወደመሆን ተሸጋግረህ ለዘረኖቹ ደህንነቶች እንዳገኙት ተዋረዱን አጥፋባቸው፡፡ ከእነደዚህ አይነት ቁጥጥር ነፃ የሆነ በሙሉ በመረጃ ማሰተላለፍ/ማጋራት ሥራ ይሳተፍ፡፡ ስልታዊ እንቅስቃሴህ/ሽ ከተነቃበት አኗኗርና ቦታን ቀይሮ ትግሉ እንዳይደናቀፍ ቅርፅና ስልቱን በመቀየር የትግል ይዘቱን ማስቀጠል ይቻላል፡፡ የዘረኛ አምባገነኖቹ ንብረት ከሆኑ የመረጃ ምንጮች ውጭ የሆኑ የመረጃ ምንጮችን ተገልገይ/ል፡፡ ኢሳት ቴልቪዚዮንና ሬዲዮ፣ ትግል ደጋፊ ብሎጎችን፣ትዊተር፣ ፌስቡክ ወዘተ… ተጠቀሚ/ም፡፡
4. የዘረኛ ፣አናሳና አምገነኖችን ድክመቶች እንጠቀም፡፡አነርሱ ወደ በረሃ ከወጡ ጀምረው የኛን ክፍተቶች በደንብ ተጠቅመል፡ ጠቅሟቸውማል፤ በስልቱም ዘመናትን አስቆጠሩ፡፡ በአንድ አካባቢና ብሔር ጭቆናና ግፍ ላይ ብቻ ሳናተኩር በግፋቸው መገፋታችንን ለህዝብ በመተረክ እንቀስቅስበት፡፡ በሁሉም ማህበረሰብ የሚደርሱና የደረሱ ግፎች የሚወሱበትና የሚዘከሩበት ሰፊ ጊዜ ይኑረው፡፡ በአንድ አካባቢ ብቻ በሚካሄድ ጦርነት፣ አመፅና እምቢተኝነት ብቻ አናተኩር፡፡ ሀገር አቀፍ የትግል ሙቀት እንዲኖር ሁሉንም በተመጣጣኝ ተይዞ ድጋፍ ይሰጠው፡፡
5. የወንበዴዎቹን ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል እና የመከላከያ አባላት እነሱን ያሳደጉ እናት አባቶቻቸውን እና እህት ዎነድሞቻቸውን የግፍ ፅዋ እያስጎነጬ ያለውን ዘረኛና አምባገነን፤ ዘመን ያለፈበት አናሳና ዘረኛ ቡድን ወግኖ የራሱን ቤተሰቦች እያሰቃዬና እያሳረደ መሆኑን በተለያዩ ዘዴዎች በመንገር የህሌና ቁስሉን አመርቅዘው/ዥው፡፡ በዚህም መንገድ ውጥረት ውስጥ ከቶ ትኩረታቸውን በመበታተን ትግሉን እነዳይቋቋሙ ማድረግ ይገባል፡፡ይቻላልም፡፡
6. የቢሮቸራሲውን ቁርኝት እና የጭቆና አውታሩን በመበጣጠስ የነፃነት ቀንን መምጫ ማሳጠር፡፡ ይህን በማድረግም ህገመንግሰታዊ፣ተቋማዊ፣ ፖለቲካዊ ወዘተ ለውጦችን ውስጥ ለውስጥ በማስጀመር ነፃነትን የተላበሰ የአዲስ ስረዓት መሠረት መጣል፡፡ የምጣኔ ሀብታዊ ለውጥ ለማምጣት የእነዚ ተቋማዊ፣ህማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦች ወሳኝ በመሆናቸው ቅድሚያ መሠረታቸው ከተጣለ አዘረኛ አምባገነኑ ቡድን እንደ ተወገደ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምጣኔኃብትን ማዕከል ያደረገው ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡
ምስጋና፡- ለገሀናዊው ደራሲ እና የነፃ አፍሪካ ድርጅት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ጆርጅ አይተይ
አንድነታችን ለሁላችንም መተኪያ የሌለው የመኖር እና የነፃነታችን መሠረት ነው!
በኑርልኝ መኩሪያው ጋረድ (ኢትዮጵያዊ)
No comments:
Post a Comment