Tuesday, January 19, 2016

ኢህአዴግ/ህወሓት ለኢትዮጵያ ድንበር በሞቱት አባቶቻችን ደም ውስጥ እጁን ነከረ!

ኢህአዴግ/ህወሓት ለኢትዮጵያ ድንበር በሞቱት አባቶቻችን ደም ውስጥ እጁን ነከረ!
በገንዘብ፣በጎጥ እና በደም ጥማት የሚንቀለቀል ልቦና የተሸከሙት የአራት ኪሎ ባለስልጣናት አፄ ቴዎድሮስ ከነገሱበት እስከ አፄ ዮሐንስ የተሰዉበትን መሬት ለሱዳን ለመሸጥ ተስማምተዋል።የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ትርጉም ይዘናል።
ኢህአዴግ/ህወሓት ለኢትዮጵያ ድንበር በሞቱት አባቶቻችን ደም ውስጥ እጁን ነከረ! አፄ ቴዎድሮስ ከነገሱበት እስከ አፄ ዮሐንስ የተሰዉበትን መሬት ለሱዳን ለመሸጥ ተስማምቷል። ኢትዮጵያ የተዳከመች ሲመስላቸው ጠላቶቿ ስነሱባት መስማት አዲስ ነገር አይደለም።
አዲስ ነገር የሚሆነው በቤተ መንግስቷ በኢትዮጵያ ስም መንግስት ነኝ የሚሉ ስብስቦች የኢትዮጵያን ጥቅም ከባዕዳን ጋር ሲዶልቱ፣ሲሸጡ እና ሲያስማሙ መመልከት ነው።በገንዘብ፣ በጎጥ እና በደም ጥማት የሚንቀለቀል ልቦና የተሸከሙት የአራት ኪሎ ባለስልጣናት አፄ ቴዎድሮስ ከነገሱበት እስከ አፄ ዮሐንስ የተሰዉበትን መሬት ለሱዳን ለመሸጥ ተስማምተዋል።
ይህ ሕሊናን የሚያደማ ብቻ ሳይሆን የመኖር እና ያለመኖር ህልውና ጉዳይ ነው።''ዳሩ ሲነካ መሃሉ ዳር ይሆናል'' የሚለው አባባል እዚህ ላይ ማሰቡ ተገቢ ነው።ይህ ሥራ በመንግሥትነት እራሳቸውን የሾሙ ስብስቦች ኢትዮጵያን የማፈራረስ ልክ የት ድረስ እንደሚሄድ ብቻ ሳይሆን የከሃዲነት ደረጃቸው እና ህዝብን የመናቃቸው መጠን ምን ያክል እንደሆነ ማሳያ ነው።
አቶ ኃይለማርያም በድንበሩ አካባቢ የሚያርሱ ገበሬ ኢትዮጵያውያንን የህዝብ ተወካይ ነኝ ባሉ ምክር ቤት ስም ''ሽፍቶች'' እያሉ የተሳደቡትን ስድብ የሱዳኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እብራሂም ጋንዱር ለአልጀዝራ በሰጡት መግለጫ ላይም ደግመውታል።
ኢትዮጵያውያንን እርሳቸው ብቻ ሳይሆኑ በስልጣን ላይ የተቀመጠው የኢትዮጵያ መንግስትም እንደሚገልላቸው ሲገልጡ ''ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሱዳን ግዛት ላይ የሰፈሩትን ሽፍቶች (gangs) በመግታት የድንበር ማካለሉን ሥራ በአንድነት እየሰሩ ነው'' ነበር ያሉት። አሁን የንግግር እና የወሬ ጊዜ አይደለም። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል በሙሉ መለየት አለበት።ኢትዮጵያን ከሸጡ ጋር ነህ ወይንስ አይደለህም? ጥያቄው ይህ ነው።ኢትዮጵያን የከዳ በሙሉ ተገቢውን ቅጣት ማግኘት አለበት።

ኢህአዴግ/ህወሓት ለኢትዮጵያ ድንበር በሞቱት አባቶቻችን ደም ውስጥ እጁን ነክሯል።የኢትዮጵያ የቀደሙት መሪዎች ማናቸውም የኢትዮጵያን ድንበር ጉዳይ ላይ ሲደራደሩ አልታዩም። አፄ ዮሐንስ ከደርቡሽ ጋር ተዋግተው መተማ ላይ አንገታቸው የተቀላው ለአገራቸው ክብር ነው። አፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ እራሳቸውን የገደሉት ለኢትዮጵያ ክብር ነው።ዛሬ ሚልዮኖች ያፈሰሱትን ደም እረግጦ የኢትዮጵያን መሬት ለባዕዳን አሳልፎ ለመስጠት የተነሳው የህወሓት ቡድን የሕዝብ ፍርድ ያስፈልገዋል።
ወቅቱ እያንዳንዱ ሰው ለድንበሩ ዘብ የሚቆምበት ጊዜ ነው።ባዕዳን ዳር ድንበሩን ሲፈልጉ ከመሃል በጎሳ እንድንቧደን እና እንድንጋጭ በማድረግ ጭምር ነው።ለእዚህም የሚረዳቸው የአራት ኪሎ መንግስት አለ።ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት ስትወስድ ብቻዋን አትሆንም ኢትዮጵያን ለዘመናት ለማዳከም የሚማስኑ የአረብ ሊግ አባላት እና የሩቅ መሰሪዎችንም ይዘው ነው።
ጉዳዩ የተቀናበረ ነው።ለኢትዮጵያውያን ቀዳሚውን ሥራ ለመግለፅ የሚያጠቃልለው ሁነኛ አባባል ''ጠላትማ ምን ጊዜም ጠላት ነው።አስቀድሞ መምታት አሾክሿኪውን ነው'' የሚለው ነው።ቀዳሚው ጠላት እኛነታችንን የሸጠን ለ24 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተንሰራፋው ስርዓት ነው።ቅድምያ ስልጣኑን መልቀቅ ያለበት ህወሓት ነው።የሱዳኑ ጉዳይ 'እዳው ገብስ ነው'።
ምንጭ ፡- ጉዳያችን

No comments:

Post a Comment