የቀድሞው የህውአት አባል አዳዲሶቹ የህውአት አባሎች በዝግ ስብሰባ ተጠምደዋል፡ በስብሰባውም ብዙ የተከራከሩበትና ያልተስማሙበትን ውሳኔ በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል አሳልፈዋል፡
የአማራ ክልል እንቅስቃሴ በጣም ጠንካራ እና ከባድ እንቅስቃሴ ናቸው፡ የሚወስዱት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በአማራ ክልል በሚኖሩት አባሎች ላይ ከፍተኛ ፍራቻ እና ጉዳት እያስከተለ ነው፡ ይህ በእንድህ ከቀጠለ በአማራ ክልል የሚኖሩትን አባሎቻችን *ሰላዮች * ካጣን መረጃዎቻችን ማግኘት ስለማንችል ህውአት የሚባለው በአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ ስልጣኑን አጣ ማለት ነው፡ ያኔ ለኛ የሞት ሞት ነው፡ በማለት በአማራው ክልል የሚደረገው እንቅስቃሴ ባለ በሌለ ሃይላችን ከአማራ ክልል መንግስት ሙሉ በሙሉ ተቀብለን በሃይል ማንበርከክ እና የተቃጣብንን አደጋ መቀልበስ አለብን ብለዋል ፡
በሌላ ጎኑ ደግሞ ይሄ እርምጃ በጣም ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍለንና መቀልበሻው ሊያጥረን የሚችልበት እንዳይሆን ጦሩነቱን በግልጽ ካወጅነው ህዝብ በአንድነት ከተነሳብን እና ብዙ ደም ከተፋሰሰ በሃላ ከዛ በሃላ ይሄ ደግሞ በትግራይ ህዝብ ላይ ከባድ አደጋ መጋበዝ ነው፡ በሁሉም ክልል የሚኖሩት ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ ቀላል አይደለም የሚሊም በስብሰባው ተነስታል።
የሆነው ሆኖ ከ95% በላይ የህውአት አባሎች በሃይል የሚወስደው እርምጃ ተስማምቶ ከዛ በኋላ የሚመጣውን ነገር አብረን እናየዋለን የሚል አቃም በመያዝ ተስማምተው ወደ ተግባር እንዲለወጥ መወሰድ ያለባቸው ቅድሚያ ዝግጅት ይወሰድ ብለዋል።
በኦሮሚያ የኦሮሚያ ጉዳይ ብዙም አያሰጋም የሚፈልጉትን ነገር ከሰጠናቸው ዝም ሊሉ ይችላሉ በዚህ ሰዓት የኦሮሞን ጉዳይ እንዲቀጣጠል ማድረግ የለብንም የጠየቁትን በሙሉ መንግስታችን እንደሚፈጽምላቸው በመናገር ማዘግየት እና ማራጋጋት አለብን ነገሮች ክተረጋጉ በሃላ መልሰን እቅዳችንን ወደምናሳካበት እና በእንቅስቃሴ ውስጥ ንኪኪ ያላቸውን በሙሉ ለቅመን ዋጋቸውን እንሰጣችቸዋለን በማለት ዘግተዋል።
ሌላው በጣም የተከራከሩበትና ያጣላቸው ጉዳይ በንብረት ሃብት ጉዳይ ነው፡
አማራ እና ኦሮሚያ በተነሳው ህዝባዊ አመጽ የተደናገጡት የህውአት ቢሊዬነሮች አባላት በኦሮሚያና በአማራ ሲዘርፉት የነበሩት ሃብት ስለተቋረጠባቸው ይሄ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ወደ ፊት ሊኖረን የሚችለው ድረስ እንዴት ነው ምክንያቱም በከፍተኛ ሁኔታ ሃብት የምንሰበስብባቸው አካባቢዎችን ካጣን ወደ አንድ መንደር ልንገባ ነው በዚህ አግባብ ደግሞ የምንፈልገውን እና ሁላችንንም እንደፈለገ ሊያንቀሳቅሰን የሚችል ሃብት የለም ለተተከሉትም ማሽነሪዎችንም ጥሬ ዕቃ አቅርቦት የለም ሁሉም ህዝባችን ወደዚህ አካባቢ የመሰባሰቡ ግዳጅ ከመጣብን ከፍተኛ የሆነ የእህል አቅርቦትም ያጥረናል እና ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እንገባለን በዛ ሰዓት ምን አይነት እርምጃ ነው መውሰድ ያለብን የተሰበሰበው ሃብትስ እንዴት ነው የምንከፋፈለው በማለት ጠንካራ ክርክር የተነሳበት ነበር በዚህ ላይ ሁሉም የህውአት አባል የተለያየ ሃሳብና አቋም በመያዝ ተፈረካክሰዋል ጸብ ቀረሽ ንግግር ሲያደርጉም ተስተውለዋል በመላው ኢትዮጵያ የተሰገሰገው የህውአት ሃብት ምዝበራ ወደ ትግራይ ሲገቡ የሚመዘብሩት ስለሌለ ያለንን በምን መልኩ እንካፈል በሚል በመለያየታቸው አንዱ አንዱን በጠላትነት እንዲተያዩ አድርጓል ።
በስተመጨረሻ ግን አሁን መጀመሪያ እድል ስላለን እንደዚህ ሰጣ ገባ ውስጥ መግባት የለብንም ሙሉውን የትግራይ ወጣት በመቀስቀስ የተቃጣብንን አደጋ መወጣት የምንችልበትን ስራ መስራት አለብን በሚለው ያልተስማሙበትና የተለያዩበትን ስብሰባ ዘግቷል።
ኢትዮጵያኖች ከመቸውም ግዜ በላይ በህውአት ሞት ተደግሶልናል፡
በጣም የገረመኝና የደነቀኝ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚያደርጉት ንቀትና በአማራው ህዝብ ላይ ለመጨፍጨፍ የተነሱበት አላማ ነው፡ የኦሮሞም ሆነ የአማራ ህዝብ ብሎም ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ከናንተ አስተሳሰብ እና ከፋፍለህ ዝረፍ፦ ከፋፍለህ ግደል ፦ከፋፍለህ ግዛ፦ ዕቅዳችሁን ካወቀ በጣም ቆይቷል፡ የኦሮሞ ጥያቄ የአማራም ብሎም የኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው። የሁላችንም የኢትዮጵያ ጥያቄ ደግሞ ወያኔ በቃን ከእንግዲህ በሃላ ህዝብንና ህዝብን አጣልተህ እና አናክሰህ መኖር አትችልም ስልጣኑን ለህዝብ በቃን ወያኔ ከአሁን በኋላ አይገዛንም እያለ ነው፡ እንጅ የህዝብን ጥያቄ መመለስ መቻል አይደለም ሞራሉም እንደሌለህ ለመናገር እወዳለሁ፡ ከእንግድህ በኋላ በወያኔ ሃሳብ ተስማምቶ ወደ ሞት የሚነዳ ኢትዮጵያዊ የለም።
ስማ፦ ስማ፦ ስማ ፦የሰማ ላልሰማ ያሰማ !!