Wednesday, September 14, 2016

አጋዚ ከ100 በላይ ቤቶችን በኮንሶ አንድዶ በ’ጸረ ሰላም ኃይሎች’ ያሳብባል | ይናገራል ፎቶው

የኮንሶ ነዋሪዎች ከልዩ ወረዳነት ወደ ወረዳ ወርደው በሰገን ዞን ስር እንዲጠቃለሉ መደረጋቸውን ተቃውመው፣ እንዳውም ኮንሶ ራሱን ችሎ ዞን ሊሆን ይገባዋል በሚል ያነሱት ጥያቄ የአጋዚ ጥይት ሰለባ እያደረጋቸው መሆኑን በተደጋጋሚ መዘገባችን አይዘነጋም:: በኮንሶ ይህ ዜና እየተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የመንግስት ሥራዎች የቆሙ ሲሆን በከፍተኛ ውጥረት ውስጥም ይገኛል:: ይህን ሰላማዊውን የኮንሶ ሕዝብ ጥያቄ አጋዚ ጦር እየሰጠው ያለው ምላሽ የሚዘገን ነው:: በትናተናው ዕለት ብቻ አይሎታ ዶካቱ እና ሉሊቶ ከተሞች ከአንድ መቶ በላይ በአጋዚ ጦር ተቃጥሏል:: ቁጥራቸው አይታወቅ እንጂ የሞቱ ሰዎችም አሉ:: አጋዚዎች በኮንሶ የተነሳውን ሕዝባዊ ቁጣ ለማብረድ ሆን ብለው ቤቶችን ካቃጠሉ በኋላ በ’ጸረ ሰላም’ ኃይሎች ለማሳበብ ሞክረዋል::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ አክቲቭስት ዳን ኤል ፈይሳ እንደዘገበው የኮንሶ መንደሮች አይሎታ ዶካቱ እና ሉሊቶ በወታደሮችና ህወሀት በሾማቸው አመራሮች ያደራጇቸው ነብሰበላዎች ቤንዚን አርከፍክፈው በተለቀቀባቸው እሳት አመድ ሆነዋል። ከፍጅቱ ማምለጥ የቻሉ ሲያመልጥ አቅመ ደካሞች እንዲሁም ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ ብዙዎች ተገለዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብም በሽሽት ኮንሶ ካራት ከተማን አጥለቅልቋት በረሀብና በጥም እንየተንገላታ ነው።
የኮንሶ ህዝብ ማንኛውም ወገን ሰበዓዊ ድርጅቶች እርዳታ እንዲለግሱዋቸውም እየጠየቁ ነው።
ከ3000 በላይ ወታደር ከነሙሉ ትጥቁ ሰፍሮ ጥይት እያርከፈከፈ ህዝቡን እየፈጀው ነው።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/65848
ፎቶዎችን ይመልከቱ::
konso

konso2jpg
konso3

No comments:

Post a Comment