Thursday, September 8, 2016

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የአቋም መግለጫ ጳጉሜ 3, 2008 ኖርዌይ !! በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚፈጽመው ጭፍጨፋ ይቁም!!


ዘረኛው የወያኔ ቡድን በሁሉም የሀገሪችን ግዛቶች ውስጥ በታሪክ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ የማፈን የመግደልና እንዲሁም የጅምላ ጭፍጨፋዎችን በንጹሀን የአማራና የኦሮሞ ዜጎች እንዲሁም ሌሎች ብሄረሰቦች ላይ ያለምንም እርሕራሔ እየፈጸመ ይገኛል።
በተለይም ካለፈው ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በጎንደርና በጎጃም እንዲሁም በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የጅምላ የጥፋት ዘመቻ ታውጇል። በአማራ ክልል በአምባ ጊዮርጊስ ብቻ ከ 26 በላይ ዜጎች ከየት እንደመጡ በማይታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል።በባህር ዳር ፣ ከአንድ ኮንዶሚኒይም ሶስተኛ ፎቅ ላይ ሆኖ በአልሞ ተኳሽ መሳሪያ 48 ዜጎች በደቂቃዎች ዉስጥ ተረሽነዋል። ደም በአገራችን እንደ ጎርፍ እየፈሰሰ ነው።የአገዛዙ የኅልውና መሠረት የሆነው ነፍሰ በላው የአጋዚ ሠራዊት ዕድሜና ፆታ ሳይለይ፥ ሕፃናትን፣ ወጣቶችን፣ አዛውንትን፣ ጎልማሶችን፣ ወንዶችና ሴቶችን ቤት ለቤት እያደነ እጅግ መርዘኛ በሆነ ጥይት እየደበደበ የዘር ፍጅት እያደረሰ ነው። የትግሬ-ወያኔ በከፈተው በዚህ ዐማራን ከምድረ ገጽ የማጥፋት ዘመቻ፣ በሺህዎች የሚቆጠሩ እህት ወንድሞቻችን ተገድለዋል፤ አያሌዎች ቆስለዋል፤ በርካታዎች ታስረዋል፤ ተጫውተው ያልጠገቡ፣ ክፉ ደጉን ያልለዩ ሕፃናት በአረመኔዎቹ ወያኔዎች ተቀጥፈዋል። ልጆቻችን አድገው ከጎስቋላው ሕይዎታችን ይታደጉናል ብለው ተስፋ የሰነቁ ወለጆች፣ ተስፋቸውን አጥተዋል፤ ቤተሰብ ፈርሷል።

የወያኔ መንግስት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በማረሚያ ቤቶች ላይ እሳት በመለኮስ ንጽሁን ዜጎችን መጨፍጨፉ ጭቃኔውንና ማንአለብኝነቱን ያስመሰከረበት ነው።
በምርጭ 97 ማግስት በቃሊቲ መረሚያ ቤት በተነሳ ቃጠሎ ፤ በትግራይ ክልል በአዲግራት ከተማ መረሚያ ቤት ፤ በደብረ ማርቆስ የሚገኘው ማረሚያ ቤት፤ በአምቦ ከተማ የሚገኘው ማረሚያ ቤት በተነሳ ቃጠሎ ፤በጎንደር ከተማ በሚገኘው ማረሚያ ቤት በተነሳ ቃጠሎ እንዲሁም በቅርቡ በቂሊንጦ ማረሚይ ቤት በተንሳ ቃጠሎ በወያኔ ስናይፐር ቁጥራቸውበ ከ23 በላይ የሚሆኑ ንጽሁን ዜጎች በግፍ ተገለዋል።ይህ ደግሞ ወያኔ በየማረሚያ ቤቱ በገፍና በፍርደ ገምድል ስርአት ታስረው ካሉት ሰዎች መካከል ለስልጣኔ ያሰጉኛል፣ህዝብን ያስተባብራሉ፣በህዝቡ ዘንድ ታአማኒነት አላቸው ብሎ የሚያምንባቸውን በማረሚያ ቤት ያሉ ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎችን በዚህ አጋጣሚ ለመግደል ሆነ ብሎ የፈጸመው ሴራ ነው።

የወገኖቻቻን ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም በዚህ በግፈኛው ስርአት መንግስት ስር አካላቸው ለጎደለ እንዲሁም ህይወታቸውን ላጡ ዜጎቻችን ምን ግዜም ታሪካቸው ተፅፎ ይኖራል። እነርሱ ለእኛ ነፃነት ሲሉ ሞቱ፣ ተሰቃዩ። እኛስ እነርሱ የሞቱለትንና እየተሰቃዩ ላሉበት ክቡር ዓላማ፣ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? ብለን ራሳችን በመጠየቅ፣ ከትውልድና ከታሪክ ተጠያቂነት የሚያድን ተግባር ልንፈጽም ይገባል።
ስለሆነም ጀግኖቹ ሰማዕታት እህት ወንድሞቻችን የሞቱለትን ዓላማ ዳር ለማድረስ፣ ዓርማቸውን አንግበን፣ በአንድነት የድሉን ቀን ለማቃረብ በጽናት ወያኔን ልንዋጋው ይገባናል።
ይህ አንባገነን ሥርዓት ኢትዮጵያ እንደሃገር ሕዝቧም እንደ ሕዝብ ቀድሞ በነበረዉ ሃገራዊ ትስስር እንዳይቀጥል ለእኩይ ዓላማዉ ሲል ብቻ የሃገሪቷን ሕዝቦች በዘርና በቋንቋ በመከፋፈል የሃገሪቷን ሕዝቦችን ሲያጣላና እርስ በርሳቸዉ እንዳይተማመኑ በከፍተኛ ጥንቃቄ የሰራና በሃገሪቷ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰቦች ወይም ብሄረሰቦች ከራሳቸው ዘር ውጭ ሌላውን ማመን የማይችሉበት ሁኔታ ሲፈጥር የቆየ ቢሆንም ይህንን ሴራ በመበጣጠስ የአማራና የኦሮሞ ህ/ሰብ ያሳየው አንድነት በወያኔ ሰፈር ከፍተኛ ሽብር የፈጠረ በመሆኑ የወያኔ መንግስት ይሄንን ሕዝባዊ መነቃቃት ለማጥፈት በሌሎችም ላይ እንደሚያደርገው ሁሉ የተለያዮ ዘዴዎችን በመጠቀም ያላሰለሰ የሞት ሽረት ጥረት ሲያደርግ ይታያል።

የወያኔ መንግስት በህዝብ ያልተወከለ አገሪቱን የግዛት አንድነት ያላስጠበቀ፤ የሃገሪቷን አኩሪ የነፃነትና የአንድነትን ታሪክ ገድል የካደና የናደ እኩይ ቡድን ስለሆነ ይህ ቡድን ከህዝብ ጫንቃ ላይ ማስወገዱ አማራጭ የሌለዉ ወቅታዊና ሃገራዊ ግዴታ መሆኑን ዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት በጽኑ ያምናል። 
እኛ የዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አባላት አምባገነኑ ህውሃት በሰላማዊና በንፁሃን ዜጐች ላይ የወሰደውን ኃላፊነት የጐደለው እርምጃ አጥብቀን እያወገዝን የኢትዮጵያ ሕዝብ ልዩነቱን ወደ ጐን በመተው ይህንን ዘረኛ ና አምባገነን ስርዓት ለማስወገድ ከመቸውም ጊዜ በላይ ተባብሮ እንዲነሳ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ትግል ለዘላለም ኮርታ ትኖራለች!
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ !!

No comments:

Post a Comment