ህውሓት/ኢህአዲግ/መራሹ አገዛዝ ላለፉት ሃያ አምስት (25) አመታት እና ከዚያም በፊት በበረሃ ቆይታቸው ወቅት ጭምር የተዘራውና የተኮተኮተው ዘረኝነት፣ አገራችንን ከፋፍሎ ለመግዛት የጭፍን ብሔረተኝነት የሥልጣን ጥማት ማሣያ እንደሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ይረዳል፡፡ ይህንን ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴ፣ በንቃትና በትጋት ሲከታተለው የነበረው፣ የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የደቡብ፣ የሐረሪ፣ የሱማሌ፣ የአፋር፣ የጋንቤላና የቤንሻንጉል ክፍለ አገር ኢትዮጵያውያን፣ በአንድ ድምጽ “ዘረኝነት በቃን! ከፋፋዮችም ዞር በሉልን !” እያሉ ነው፡፡ እጅግ የሚያመረቃና ከፍተኛ ኃይልና ግርማ ያለው ሕዝባዊ ድምጽ ነው፡፡ የኢያሪኮን ግንብና ቅጥሮች ያናወጸው ሕዝባዊ ድምጽ፣ ዛሬ በአገራችን ኢትዮጵያ፣ ኢህአዲግ-መራሹንም ሥርዓት አንኮታኩቶ እንደሚገረስሰው አንጠራጠርም፡፡ ይህም ወቅትና አይቀሬው የአገዛዙ የጽልመት ሰዓት በመድረሱ፣ እኛ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ የተሰባሰብን አባላትና ደጋፊዎች፣ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የድል ብስራት ለመምጣቱ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የለንም !!! ለህዝባዊ ትግሉም የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ሙሉ ድጋፍ ይሰጣል ፡፡
No comments:
Post a Comment