ዓመታዊ መምህራንን በህወሓት ርዕዮተዓለም የማጥመቅ ሥራ ዛሬ ተጀምሯል። ከእነሱ በኋላ የተማሪዎች ይከተላል። ህወሓት ርዕዮቴ ነው የሚለው “አብዮታዊ ዲሞክራሲ” “ለነባሮቹ ታጋዮች” ሳይቀር ግልጽ ያልሆነ የቅዠቶች ድሪቶ ነው።
እንዲህ ዓይነቱን “ፀረ - ትምህርት” ብቻ ሳይሆን “ፀረ - ሰው” “ስልጠናን” እንዴት ዋጋ ማሳጣት ይቻላል?
ከስልጠናው መቅረት ከሁሉ የተሻለ አማራጭ ቢሆንም እንኳን የጋራ ውሳኔ ይጠይቃል። The Logic of Collective Actions ይኸኛውን አማራጭ ከባድ ያደርገዋል የሚል ስጋት አለኝ፤ ይህንን አማራጭ ተግባራዊ ለማድረግ በመምህራን ውስጥ ያለው የሕዝባዊ እምቢተኝነት ስሜት አሁን ካለው ሞቅ ማለት አለበት። [ከጥቂት ወራት በኋላ እዚህ ደረጃ ላይ ይደርሳል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አሁን ግን ትንሽ ይቀረዋል]
መቅረትን ከአማራጭነት ካወጣን ሁለት ሌሎች አማራጮች አሉ።
1. ፍሬ ከርስኪ ጉዳዮችን እያነሱ በታላቅ ወኔ በመከራከር ሴሚናሩን ውል ማሳጣት፤ ትናንሽ ነገሮችን እጅግ ዋጋ ያላቸው አስመስሎ ቀኑን በክርክር መጨረስ።
2. ዝምታ፤ በምንም ጉዳይ ላይ አስተያየት አለመስጠት። በግድ ተናገር ከተባለው ረብ የለሽ ነገር መናገር።
ሁለቱም አዋጭ ታክቲኮች ናቸው፤ ሁለቱን የመምህራኑን ደህንነት ይጠብቃሉ፤ ሁለቱን የሴሚናሩን ድብቅ ተልዕኮ ያከሽፋሉ። እኔ ሁለተኛውን እመርጥ ነበር ይሆናል። ጊዜዬን በተሻለ መንገድ ለመጠቀም ጭንቅላቴን የሚያዝናኑ ነገሮችን እያሰብኩ ዝም ብዬ እቀመጥ ነበር። ወዳጆቼ ይህንን መንገድ እንድትሞክሩት እመክራሉ።
ተቃውሞዓችሁን በዝምታ ግለጹ፤ ዝምታችሁ በጩኸት በላይ እንዲሰማ ማድረግ ትችላላችሁ።
(ዶ/ር ታደሰ ብሩ)
No comments:
Post a Comment