Monday, August 1, 2016

‪ሰበርዜና….‬ ዛሬ በአባይ ወልዱ የሚመራው የትግራይ ክልል ካቢኔ በመቀሌ ከተማ ባአባይ ወልዱ መስራ ቤት አስቸኳይ ስብሰባ

Abay weldu
http://www.satenaw.com/amharic/archives/18341
ዛሬ በአባይ ወልዱ የሚመራው የትግራይ ክልል ካቢኔ በመቀሌ ከተማ ባአባይ ወልዱ መስራ ቤት አስቸኳይ ስብሰባ መደረጉ ከቦታው የነበሩ ታማኝ ምንጮቻችን ገልጸውልናል።በዋናነት የሥብሠባው አላማና በአጀንዳነት የተያዙት ጉዳዮች
1ኛ)አማሮች በተለይ ጎንደር ላይ ያሉት ጥቂት ጸረ ሰላም ሀይሎች እና የሻብያ ተላላኪ ትምክህተኞች በትግራይ ህዝብ ላይ ያወጁት ጸረ ትግራይ ህዝብ ፕሮፓጋንዳ ከፌዴራል መንግስት ጋር ተነጋግረን እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ አሳስበዋል።

2ኛ)በወልቃይት የአማራ ማንነት ጉዳይ ኮምቴዎች በትግራይ ውስጥ በእስር ስለሚገኙ ለቀረበባቸው የአሸባሪነት ክሥና ህገ መንግሥታዊን ሥርአት በሁከት ለመጣል ብሎም ህዝብን ከህዝብ ማጋጨት እና ውንብድና የሚል ክስ የተከሠሡት በሚገባ ክሳቸው ተጠናክሮ ባሥቸካይ ውሣኔ እንዲያገኝ ለፍትህ ቢሮ ሀላፊው አቶ ተሥፋ አለም ይህደጎን አዝዘዋል።በተጨማሪም በሥብሠባው ለነበሩት ይክልሉ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሂርትን ለነዚህ ወንጅለኞች የማያዳግም ቅጣት እንዲሠጣቸው እንዲያደርጉ አሳሥበዋል።እዛው አከል አድርገው በክልሉ የጸጥታ ጉዳይ ሥለ ኮለኔል ደመቀ ለቀረበላቸው ጥያቄም “ኮለኔል ደመቀ በገር ክህደት እና በሽብር ወንጀል ክሥ ቀርቦ አሥፈላጊው ቅጣት በትግራይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዲሥ አበባ ጉዳዩ እንዲታይ እናደርጋለን ብለዋል።
3ኛ)የክልሉ ፖሊሥ ኮምሽነር ወዲ ሻምበል በጸጥታው በኩል የሠሩትን ሲያቀርቡ በወልቃይት፣ጠገዴ፣ጠለምት፣ዳንሻና አከከባቢ ሊነሳ የሚችል ችግር ካለ በቂ አዲሥ ሥልጡን የፖሊሥ ሠራዊት መመደባቸውንና በአከባቢው ያሉት የትግራይ ተወላጆች ማህበራዊ ተጽእኖ እንዳይደርሥባቸው አሥፈላጊውን ጥብቃ እየተደረግላቸው መሆኑንና ካከባቢው ጸጥታ በመነጋገርም እንዲታጠቁ እየተደረገ መሆነን ገልጸዋል።
4ኛ)በሀገሪቱ ህግ ያልተፈቀደ ባንዲራ ይዘው የወጡት የደረግ ትርፍራፊዎች በትግራይ ብሄር ላይ ያነጣጠረ ዛቻና የሥም ማጥፋት ሥራ የትግራይ ህዝብ ይህንን አውቆ እንዲታገላቸው ለወረዳ መሥተዳድሮች መመሪያ ተላላፎ ህዝቡን አሥፈላጊ መረጃ አግኝቶ በተደራጀ ሁኔታ ሠላማዊ ሠልፍ ወጥቶ ግልጽ የሆነ ጸረ ትምክህቶኞች ተቃውሞ እንዲያሠማ ህዝቡን በየአከባቢው እንዲያሣምኑት አሳሥበዋል።
Nigiste Saba-Ethiopia

No comments:

Post a Comment