ብዙ የትግራይ ተወላጆች የወልቃይትን ጉዳይ ~ በአንድ ክልልየመካለል ፣ ካርታ ላይ መስመር እንደ ማስመር ቀላል ነገርአድርገውት ያቀርባሉ :: ነገሩ እንደሱ አይደልም እነሱም ልያቀሉት የፈለጉበት ምክንያት ኢትዮጵያ አንድ ነች ወዴትም ቢካለል ችግር የለውም ከሚል ህሳቤ አይደለም ነገሩ ቅኔ ነው
እኛ ግን ወልቃይት አማራ ነው ~ የአማራም ድንበር ተከዜ ነው የምንለው የወያኔን የብሔር ፖለቲካ ለማራገብ ፈልገን አይደለም ነገር ግን ወልቃይት ወደ ትግራይ እንዲካለል ለምን እንደተፈለገ ጠንቅቀን ሰልምናውቅ ፣ ላለፉት 40 አመታት በዚያ እንግዳ ተቀባይ ሕዝብ ላይ ምን ደባ ሲካሄድ እንደነበር ጠንቅቀን ስለምናውቅ ፣ በአንድ ክልል ከመካለል በላይ በወልቃይት ተውላጆች ላይ በስነ- ልባናም ፣ በኢኮኖሚም ፣ በማንነትም ላይ ምን እየተደረግ እንዳለ ጠንቅቀን ስለምናውቅ ፣ለዘመናት
በአከባቢው ላይ የሚኖሩ የወልቃይት ተወላጆችን በማፈናቅል ፣ በመግድል ፣ በማሰር ከትግራ ብዙ ሺ ስዎችን በማምጣት በማስፈር የአከባቢውን ድሞግራፍ ለመቀርይ ጥረት እየተደረ መሆኑን ጠንቅቀን ስለምናው ፣ በማንኛውም ሰብአው ፍጥሩ ላይ ልደረግ የማይገባው ዜጎች ያለፍላጎታቸው ባልፈለጉት ቋንቋ ፣ ባህል እንዲጠቀሙ እየተገደዱ መሆኑን ጠንቅቀን ስለምናውቅ ፣ የወልቃይት ሕዝብ በታሪክ የትግራ ክልል (አመራር ስር) ሆኖ እንደማያቅ ጠንቅቀን ስለምናውቅ ነው ::
.
እኛም እንጠይቅ (ይህ ጥያቄ የህወሓት ካድሬዎችን ሳይሆን በኢትዮጵያ አንድነት አምናለው ለምትሉ ለትግራይ ተወላጆች ብቻ ነው) እናንተስ በኢትዮጵያ አንድነት የምታምኑ ከሆነ አንድ ሕዝብ በፈለገው ክልል የመካለል ፣ የፈለገውን ባህል ፕራክትስ የማድረግ ፣ ከፈለገውን ቋንቋ መጠቀም ድሞክራሳዊ መብቱ ከሆነ የወልቃይት ሕዝብ የአማራነት ጥያቄ ሲያነሳ ስለምን ይከፋችሁል ፣ ስለምን የህዝቦችን ጥያቄ ለማድበስበስ ትሞክራላችሁ ፣ ስለምን በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠር ጥያቄ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ ፣ ስለምን በወልቃይት ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ አታወግዙም ስለምን …..
No comments:
Post a Comment