አለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት (Global Alliance for the Rights of Ethiopians) ከህወሃት አልሞ ተኳሾችና መስዋዕት ለሆኑ፣ ጉዳት ለደረሰባቸውና ቤተሰቦቻቸው ድጋፍ እንዲደረግ አለም አቀፍ ጥሪ አቀረበ።
መቀመጫውን ሰሜን አሜሪካ በማድረግ ለኢትዮጵያውያን መብት በአገራችን በተነሳው ህዝባዊ እምቢተኝነት ምክንያት በአገዛዙ ታጣቂ ሃይሎች ጉዳት ለደረሰባቸው የኦሮሚያና የአማራ ክልል ለሚገኙ ወገኖች የተቻለንን ድጋፍ የማድረጊያ ጊዜው አሁን መሆንኑን በመግለጽ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።
“አስቸኳይ የመደጋገፍ ጥሪ” በሚል ርዕስ መግለጫ ያወጣው የግሎባል አሊያንስ የቦርድ አስተዳደር ኢትዮጵውያን በቀላሉ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉበትን ሁኔታ ማመቻቸቱንና የሚሰጠው ድጋፍ ጉዳቱ ለደረሰባቸው ወገኖች የሚደርስበትን መንገድ መረጋገጡን አስታውቋል። “ለወገኖቻችን እንድረስላቸው” በማለት ጥሪውን ያቀረበው ግሎባል አልያንስ ከእለት ተዕለት እየተባባሰ በሄደው የጥይት ናዳ የሚሞቱትና የሚቆስሉት ወገኖቻችን እየጨመረ በመሄዱ አስቸኳይ ድጋፍ ለማድረግ ድረገፅን እንዲገበኙ አሊያም በቀጥታ ስልክ ቁጥር እንዲጠቀሙ ጥሪውን አስተላልፏል።
No comments:
Post a Comment