በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ሳያቋርጥ ወራትን ባስቆጠረበት በአሁኑ ወቅት፣ ከ450 በላይ የሆኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ህዝቡ ያነሳውን ጥያቄ ተቀብለው ትግሉን እንደተቀላቀሉ ተገለጸ።
ህዝቡን የተቀላቀሉት የሰራዊት ተወካይ ከስፍራው ለኢሳት እንደተናገሩት፣ የሰራዊቱ አባላት የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች በመሆናቸው ለህዝብ ድጋፍ ለማሳየት በዚህ በወሳኝ ሰዓት ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል። የመከላከያ ሰራዊቱ ከህዝቡ ላይ የተጣበቀውን የህወሃት ዘረኛ አገዛዝ ነቅሎ መጣል አለበት ሲሉ ለኢሳት ተናግረዋል።
ሰራዊቱ እንደሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ በህወሃት የበላይ አዛዥ ጄኔራሎች ፍዳውን ሲያይ ኖሯል ያሉት እኝይ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት የሰራዊቱ ቃል አቀባይ፣ ላለፉት 25 አመታት በህወሃት የጦር አመራር ለመግለጽ የሚከብድ ወንጀል ሲሰራባቸው እንደነበር ተናግረዋል።
ህዝቡ ትግሉን አጠናቅሮ በቀጠለ ቁጥር የመከላከያ ሰራዊቱም እንዲሁ ከህዝቡ ጎን በመሆን ትግል እንደሚያደርጉ ከሰሜን ኢትዮጵያ በቃለ-መጠይቁ ተመልክቷል። ከጥቂት የህወሃት አዛዦችና የስርዓቱ አቀንቃኞች ውጪ አብዛኛው የሰራዊት አባላት የህዝብ ልጆች ናቸው ያሉት ህዝባዊ ተቃውሞን የተቀላቀሉ ቃል አቀባይ፣ መንግስትን በመቃውሞ ወደህዝቡ የሚቀላቀለው ለሚደረገው ትግል ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚያደርጉ ተነግሯል።
No comments:
Post a Comment