Tuesday, September 6, 2016

አሁን ከአንዲት ወዳጄ ጋር በፌስ ቡክ ስናወራ ኢሳት ውስጥ ነው የምትሰራው እንዴ ብላ ጠየቀችኝ.. እኔ ደግሞ ''ፌመስ'' ነኝ ብዬ ሳቅራራ ለካስ ማንም አያውቀኝ ብዬ አይምሮዬ እየተነካ... ሃሃ አዎ ኢሳት ውስጥ እሰራለሁ አልኳት። ምን ብትለኝ ጥሩ ነው... ኢሳትም ሆነ አጠቃላይ ፖለቲካ ሲያስጠላኝ አለችኝ.. እንደልጅት አነጋገር ኢሳት በሚያደርገው ቅስቀሳ ሰው እያስፈጀ ነው። ለውጥ ላይመጣ ነገር ለምን ሰው ታሰፈጃላችሁ? ብላ ሁሉ ሞገተችኝ... እንደኔ እምነት ኢሳትም ሆነ ሌሎች መሰል ሚዲያዎች የለውጥ አቀንቃኝ ቢሆኑም ቅሉ ቀስቃሽ እና ቆስቋሽ ናቸው በሚለው ግን አልስማማም። የሃገሬ ህዝብ አደባባይ እየወጣ ተቃውሞውን የሚያሰማው በደሉ በዝቶ ስለገነፈለ እንጂ እኛ ስለቀሰቀስነው አይደለም። (በነገራችን ላይ እንደዝች ልጅ የሚያስቡ ሰዎች አብዛኛዎቹ እነ እንትና / የኢህአዴግዬ የእህል ውሃ ዘመዶች እና የስጋ ዘመዶች ቢሆኑም ሁሉም ግን እንደዛ ናቸው ማለት አይቻልም እና በትህትና ነገሩን ከስሩ ማስረዳት ተገቢ ነው።) በዚህ ጉዳይ ላይ ባሳለፍነው እሁድ በ ዋዛ እና ቁምነገር/ Abe Tokichaw ገጻችን ቀጥታ ስርጭት ሙከራ ያደረግን ግዜ በቅጡ አውገተናል። ይሄውም ወግ የዛሬው ዋዛ እና ቁምነገር ላይ ተካቷል። እና ምን ለማለት ነው፤ እነሆ ዋዛ እና ቁምነገር ዝግጅት ስለ ቂሊንጦው የእሳት አደጋ ከናንተ ጋር በቀጥታ የተወያየነውን አካቶ ተከስቷል። የኢሳት ድረገጽ የሚከፈትላችሁ ወዳጆች እነሆ... http://video.ethsat.com/?p=27962 አይ እርሱማ በጄ አይለንም ኮ የምትሉ ደግሞ እነሆ የኢሳት ዩቲዩብ፤ https://www.youtube.com/watch?v=xHn6je0ff28 ሳልነግራችሁ... የቀጥታ ስርጭት ነገር ሙድ አላት... አንዳንድ የቴክኒክ ማዳበሪያዎችን አድርገን እንደጋግማታለን... በተረፈ ሰላም ናችሁ አይደል!?

No comments:

Post a Comment