Muluken Tesfaw..
ከ40 በላይ የጠፉ ወታደሮችን ፍለጋ ወደ ደንቢያ በሁለት ኦራል ጦር ተልኳል
የጎንደር ቅዳሜ ገበያው ቃጠሎ የዐማራ የንግድ ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ነው
ትናንት መስከረም 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ትጥቅ ለማስፈታት ወደ በለሳና ወገራ ወረዳዎች ድንበር አካባቢ የሔደው የወያኔ ጦር ውስጥ ከ30 በላይ እንደተገደሉ ተገልጾ ነበር፡፡ ዛሬ ማምሻውን ለማረጋገጥ እንደሞከርነው የወያኔ ጦር የሸሹ ገበሬዎችን በመከተል እስከ ማጫ በለሳ እና ደንቀዝ ድረስ ተጉዞ ነበር፡፡ ሆኖም አብዛኛው የወያኔ ጦር አባላት በዚያ መቅረታቸውን ነው ያነጋገርናቸው ሰዎች የገለጹት፡፡ ሆኖም በቁጥር ስንት ወታደሮች እንደሞቱ የታወቀ ነገር የለም፡፡ አስተያየት ሰጪዎቻችን እንደሚሉት የመሣሪያ ነጠቃው ሁሉንም የወገራና የበለሳ አርሶ አደር ከቤት እንዲሸፍት ምክንያት ሆኖታል ተብሏል፡፡ ከምዕራብና ምስራቅ በለሳ ወረዳዎች ገበሬዎች በመደራጀት መሣሪያ ላለመነጠቅ እየተጋደሉ ነው ተብሏል፡፡ በበለሳ ድንበር ባሉ የወገራ ወረዳ፣ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ቀበሌዎችና የምዕራብ በለሳ ውስጥ ቤት ውስጥ የሚገኙት ሕጻናትና ሴቶች ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል ዛሬ መስከረም 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ምሽት 2፡00 ሰአት ላይ ከመከላከያ ሠራዊት ከነትጥቃቸው የሸፈቱ ከ40 በላይ የሚሆኑ ወታደሮችን ለመያዝ በሚል ወደ ደንቢያ ወረዳ ጉራንባ ወደተባለ ቦታ ከጎንደር የወያኔ ጦር ተንቀሳቅሷል ተብሏል፡፡ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች የደንቢያን ሕዝብ ትጥቅ የማስፈታት ዓላማን ሁሉ አንግቦ ወደ አካባቢው አምርቷል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ የደንቢያ ገበሬዎች መልእክቱ አስቀድሞ እንዲደርሳቸው ለማድረግ ተሞክሯል፡፡
No comments:
Post a Comment