Friday, September 16, 2016

ታላቅ የሥራ ማቆም እድማ ጥሪ!


ታላቅ የሥራ ማቆም እድማ ጥሪ!!
ከባህርዳርና ጎንደር ህዝባዊ ተቃውሞ አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
የባህር ዳር እና የጎንደር አስተባባሪ ኮሚቴዎች ከፊታችን ሰኞ ማለትም ከመስከረም 9 ጀምሮ እስከ መስከረም 14 ድረስ የሚቆይ(ቅዳሜን ይጨምራል) የስድስት ቀናት የሥራ ማቆም አድማ የጠራን ሲሆን ፤ሁሉም የአማራ ከተሞች የስራ ማቆም አድማውን እንድትቀላቀሉ ጥሪ አቅርበናል። 
በመሆኑም ማንኛውም የንግድ ድርጅት እና ተሽከርካሪ ጥሪውን ተቀብሎ አድማውን ተግባራዊ እንዲያድርግ እየጠየቅን፤ ይህን የማይቀበል ድርጅትና ተሽከርካሪ ለሚደርስበት ጉዳት ኃላፊነቱን እራሱ እንደሚወስድ እናስገነዝባለን!
የሥራ ማቆም አድማው ዋና ምክንያት በሽዎች የሚቆጠሩ ወንድሞቻችን በገፍ ታስረው ከፍተኛ ድብደባ እና ግድያ እየተፈፀመባቸው ስለሆነ ሳምንቱን ሥራ ሳንሠራ እነሱን ለመዘከር ነው። ስለሆነም በመስቀል በአል በየሰፈሩ ባለ ደመራ እርድ የማይፈፀምበት ይሆናል ።
እርድ የማይፈፀምበት ዋና አላማ፤ እህት ወንድሞቻችንን በግፍ ካስገደሉ፣ከገደሉ፣ ካሣሰሩና ካሰሩ ባለስልጣናት፣ ፓሊስ፣ ሚሊሻ ካድሬና ተላላኪዎች በተከፈላቸው የደም ዋጋ በሆነ ደመወዝ በሚደረግ ግብይት ከነሱ ጋር የማንለዋወጥ፣ የማንበላና የማንጠጣ መሆኑን እንዲያውቁት ነው። ይህን ጥሪ የማያከብር ወይም የሚተላለፍ፤ የእህትና የወንድሙን ስጋና ደም እንደበላና እንደጠጣ ነው የምንቆጥረው።
ስለሆነም ሁሉም የአማራ ህዝብ ጥሪውን እንዲቀበል በሞቱት ወገኖቻችን ስም እንጠይቃለን።
(ማስታወሻ፦ የቀይ መስቀል ተሽከርካሪዎች፣ ፉርማሲዎች፣ ክሊንኮችና ዳቦ ቤቶች አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ እናሳውቃለን።)

No comments:

Post a Comment