Tuesday, September 6, 2016

ESAT 1 hr · ሰበር ዜና የአጋዚ ወታደሮች ተገደሉ፣ 1 ቆስሏል።ሕዝብ በወሰደው የቦምብ ጥቃት በነቀምት ከተማ ወታደሮቹ ተገድለዋል። በዚህ ድንጋጤ ሠራዊቱ ግበታዊ የበቀል እርምጃ በመውሰድ ከጉዳዩ ጋር ግኑኝነት የሌላቸው 3 የክረምት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ገድሏል። በኦሮሚያ ላለፉት ለ9 ወራት በሰላማዊ መንገድ መብቱን፣ፍትሕ፣እኩልነት፣ ዴሞክራሲ ሲጠይቅ የቆየው ሕዝብ ፌደራል መንግስት በሚልስ ስም በህወሓት ወታደራዊ አገዛዝ ስር ወድቋል። የአጋዚ ጦር በሁሉም የኦሮሚያ አካባዊዎች ሰፍሮ ያዋክባል፣ያስራል፣ይገድላል።ከኅዳር ወር ጀምሮ በ10ሺዎች ታስረው ከ800 በላይ ተገድለዋል። ይህ ያስመረረው ሕዝብ ወደ ኃይል እርምጃ እየገባ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።

No comments:

Post a Comment