Mesay Mekonnen.
በነገራችን ላይ የህወሀት መንግስት ስደት የሰለቸውንና የፖለቲካ ክስረት ገጥሞት የሚንከራተትን እያሰሰ፡ በገንዘብ ደልሎ ሀገር ቤት በማስገባት ለካድሬዎቹ የሞራል ጥገና የሚሆን ፕሮፖጋንዳ ላይ ተጠምዷል። የበፊተኞቹን ትተን ሰሞኑን የሆኑትን ማንሳት ይቻላል። የአፋር የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ነው ተብሎ አሎ ካይዲስ የሚባል ሰው ህገመንግስቱን ተቀብሎ ለመታገል ሀገር ቤት ገባ የሚል ዜና የህወሀት ሚዲያዎች ሲደልቁ ነበር። ሳምንት ሳይሞላው ተጣልቷቸው ካናዳ ገባ። ለጊዜው ለፕሮፖጋንዳ ተጠቀሙበት። ፍርሃት የሚንጣቸውን ካድሬዎቻቸውን አረጋጉበት። ዛሬ ደግሞ በሰበር ዜና ቱዋት ፖል የሚባል የአርበኞች ግንባር መሪ ከመንግስት ጋር ተስማማ። ሰራዊቱ በቅርቡ ትጥቁን ፈትቶ ሀገር ቤት ይገባል እያሉ በፈንጠዝያ ላይ ናቸው። መቼም እንደዚህ የከሰረ፡ በውሸትና ተራ ፕሮፖጋንዳ ካድሬዎቹን እያጠገበ፡ አንድም ቀን ብትሆን ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚንደፋደፍ ስርዓት ታይቶም አይታወቅም።
ቱዋት ፖል የሚባል የአርበኞች ግንባር መሪም አባልም የለም። የዛሬ 20 ዓመት አከባቢ ጥቁር አንበሳ የሚባል ድርጅት ሲመሰረት የነበረ በኋላም የአርበኞችን አንድነት ግንባር ወደሚል ስም ቀይረው ሲንቀሳቀስ ቆይቶ ሚናው ሲደክም ከፊት መስመር ወጥቶ ወደ ኋላ በማፈግፈግ የስደት ህይወት ላይ የቆየ ሰው ነው። የእሱ አርበኞች አንድነት ግንባር የነበረውና የአሁኑ አርበኞች ግንቦት ሰባት ፈጽሞ የሚገናኙ አይደሉም። ህወሀት የሰሞኑን ወሬ ቀለብ አድርጎ ከቱዋት ፖል ጋር ሰፍቶ እያምታታበት ነው። ዱርዬ፡ ወንበዴ መንግስት።
እኔ በግሌ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በቅርበት መከታተል ከጀመርኩ ካለፉት 10 ዓመታት ወዲህ ቱዋት ፖል የሚባል ሰው ዘሩ እንደጠፋው ዳይኖሰር ''የሚባል ነበረ'' በሚል ከመስማት ውጪ በአንድም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ያልነበረ ሰው ነው።
ህወሀት ከስሯል። ከገደል አፈፍ ላይ ነው። ውድቀቱ የማይቀር ነው። አሎ ካይዲስ፡ አያድነውም። ቱዋት ፖል አይታደገውም። ብርሃኑ ነጋ ነገ ቢቀላቀለው አያተርፈውም። የተጀመረው ህዛባዊ ትግል ነው። የተነሳው ህዝብ ነው። የመጨረሻው ዙር ላይ ያለን ስርዓት የትኛውም ምድራዊ ሃይል ሊያድነው አይችልም። በቃ!!
No comments:
Post a Comment