Wednesday, September 7, 2016

በአበባ እርሻ የተሰማራ የኔዘርላንድ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ጠቅልሎ መውጣቱን አስታወቀ ኢሳት (ጳጉሜ 2 ፥ 2008)



Bilderesultat for የኢትዮጵያ አበባ ልማትበኢትዮጵያ በግዙፍ የአበባ እርሻ ምርት ላይ ተሰማርቶ የነበረ አንድ አለም አቀፍ የኔዘርላንድ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ጠቅልሎ መውጣቱን ይፋ አደረገ። 
ኢስመራልዳ ፋርም የተሰኘው ኩባንያ በአማራ ክልል በመንግስት ላይ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ በአበባ ማምረቻ የእርሻ ድርጅቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጿል። ከሳምንት በፊት በተፈጸመበት በዚሁ ጥቃት ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እንደወደመበት የኔዘርላንዱ ኩባንያ አውስቷል። 
በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ባለመሆኑ ምክንያት መቀመጫውን በዚህ በአሜሪካ ያደረገ የኢስሜራልዳ እህት ኩባንያ በኢትዮጵያ ያለው የአበባ ማምረቻ ተቋም ሁሉ ለሙሉ እንዲዘጋ መወሰኑን የኔዘርላንድ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 
በኢትዮጵያ የሚገኙ የኩባንያው 14 የውጭ ሃገር ሰራተኞች፣ ድርጅቱ በወሰደው እርምጃ ስራ ማቆማቸውን የአበባ አምራች ኩባንያው በድረገፁ ላይ ባሰፈረው መግለጫ አመልክቷል። 
ከኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ ለቆ መውጣቱን ይፋ ያደረገው የኔዘርላንዱ የአበባ አምራች ኩባንያ ላለፉት በርካታ አመታት ከመንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪን ሊያስገኝ የቆየ ሲሆን፣ 40 በመቶ የሚሆነውን ምርቱን ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ያገኝ እንደነበር ለመረዳት ተችሏል። 
በኦሮሚያ እና በጋምቤላ ክልሎች እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉምዝ የሚገኙ በርካታ አርሶ አደሮች መሬታችን ያለ-አግባብ ለውጭ ባለሃብት ተሰጥቶብናል በማለት ተቃውሞን ሲያካሄዱ መቆየታቸው ይታወሳል። 
ይህንኑ አቤቱታ ተከትሎ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች ለሃገሪቱ በሚሰጡት ድጋፍ ላይ የማስተካከያ እርምጃን እንዲወስዱ ዘመቻ ሲያካሄዱ ቆይተዋል። 
የብሪታኒያና የአለም ባንክ አቤቱታው በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ካደረጉ በኋላ ለኢትዮጵያ በሚሰጡት የልማት ድጋፍ ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ ዘመቻ ሲያካሄዱ ቆይተዋል። 
የብሪታኒያና የአለም ባንክ አቤቱታው በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ካደረጉ በኋላ ለኢትዮጵያ በሚሰጡት የልማት ድጋፍ ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ውሳኔ ማስተላለፋቸው ይታወቃል። 
የልማት አጋሮቹ ለኢትዮጵያ ሲሰጡ የቆየው ድጋፍ ገበሬዎችን ከቀያቸው ለማፈናቀል እንደዋለ በአለም ባንክ ስር የተቋቋመ አንድ ቡድን ማረጋገጥ እንደቻለ ባለፈው አመት ይፋ ማድረጉን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሲዘግቡ ቆይቷል። 
የቡድኑን የምርመራ ውጤት ተከትሎ የብሪታኒያ መንግስት በየአመቱ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ዘርፈ ብዙ የልማት ድጋፍ እንዲቀር መወሰኑ የሚታወስ ነው። 
የአለም ባንክ በበኩሉ ለኢትዮጵያ በሚሰጠው የልማት ድጋፍ ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ውሳኔን ያስተላለፉ ሲሆን፣ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በ10ሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች መሬታቸውን ለልማት በሚል ሰበብ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ይገልጻሉ። 
ከጸጥታ ችግር ጋር በተገናኘ ከኢትዮጵያ ጠቅልሎ መውጣቱን ያስታወቀ የኔዘላንዱ ኩባንያ በአመት ወደ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የአበባ ምርት ለተለያዩ ሃገራት ያቀረብ እንደነበር ለመረዳት ተችሏል።

No comments:

Post a Comment