Friday, September 16, 2016

የዐማራ ሕዝብ ወደ ጫካ ወይም ማሰቃያ ካምፕ መሔድ ምርጫ ቀርቦለታል፤  መፈናቀል በአውሮፕላንና በእግር፤ በወታደር የሚፈናቀሉና በወታደር የሚጠበቁ ዜጎች

Muluken Tesfaw.
ከትግራይ የበቀለው ጥቁር ፋሽስት ለዐማራ ሕዝብ ሁለት ምርጫዎችን አቅርቦለታል፤ ሁለቱም መጥፎ ናቸው፤ ሁለቱም የሕልውና ፈተናዎች ናቸው፡፡ ዛሬ ዐማሮች ዜጎች ሳይሆኑ የወያኔው የጭቃኔ ማሳያና መለማመጃዎች ሆነዋል፡፡
በጎጃምና በጎንደር ያሉ በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ዐማሮች ብር ሸለቆ የወታደር ማሰልጠኛ ማእከል ገብተው በትግሬ ጄኔራሎች ቶርቸር እየተደረጉ ነው፡፡ ጫማቸውን አውልቀው በግርደፉ በተከሰከሰ አሸዋና በብርጭቆ ስባሪ ላይ በእንብርክክ እንዲሔዱ እየተደረጉ ነው፤ በጠርሙስ ስባሪ ጸጉራቸው ሲላጭ የሚደርስላቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋች አካል እንኳን የለም፡፡ በቶርቸር አካላቸው ሲጎድል ‹‹ለምክር ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ ተወስደዋል›› ነው የሚባለው፡፡ በሌላ በኩል ከመታሠር የፈሩ ቤታቸውን ከአራዊት ጋር አድርገዋል፡፡ ዛሬ በከተማዎች አካባቢ ወንድ የሚባል ፍጡር እንኳ የለም፡፡ 
ዐማሮች አንድ የቀረ ሀብታቸው መሣሪያቸው ነው፤ እሱን ለመቀማት የትግሬው ፋሽስታዊ ሥርዓት ግብረ ኃይል አቋቁሞ በዐማሮች ላይ ዘምቷል፡፡ ወቅቱ ገብስ የሚታጨድበት፤ ጤፍ የሚታረምበት፣ ማሽላ የሚሸለቀቅበት፣ የተለያዩ አዝርእቶች እንክብካቤንና መስብሰብን የሚፈልጉበት ወቅት ቢሆንም ይህ ፋሽስታዊ ሥርዓት የዐማራውን ሕዝብ ከሀብትና ከጥሪት ውጭ ለማድረግ በዚህ ወቅት በአዋጅ ዘምቶበታል፡፡ መሣሪያቸውን አናስነጥቅም ያሉ ዐማሮች ከጠላታቸው ጋር እየተዋደቁ ነው፡፡ 
ደግሞ በሌላ በኩል ይህ ጨካኝ ሥርዓት በእቅድ ዐማሮችን ከደቡብ ክልል እያፈናቀለ ነው፡፡ በኮንሶ የዐማሮች መንደር ዶጋ አመድ ሆኗል፡፡ ሕይወታቸውን ለማትረፍ የቀናቸው በጭነት መኪና እድለኛ ያልሆኑት ደግሞ በእግራቸው አርባ ምንጭ ድረስ እየተጓዙ ነው፡፡ ዛሬ አርባ ምንጭ ወደ ሴቻ ሰፈር ሂዶ የአባያና የጫሞን ሀይቆች ወይም የእግዜር ድልድይን ውበት ለማየት የሚሻ ሰው ዐይኑ የሚያርፈው ደራሽ ከሌላቸው ብኩን የዐማራ ተፈናቃዮች የጥቁር ፋሽስቱ ሰለባ እናቶችና ሕጻናት ፊት ላይ ነው፡፡ የአብያተ ክርስቲያናት ደጀ ሰላም እንኳ ለማረፊያ የሚሆን ቦታ አልሰጧቸውም፤ በአርባ ምንጭ ጎዳናዎች ላይ ተልከስክሰዋል፡፡ አዎ ይህ የዛሬው የዐማራ ሕዝብ ዕጣ ፈንታ ነው፡፡ 
የሥርዓቱ ዜጎችስ? አገር ለእነርሱማ ይህች ናት፡፡ ዐማራውን በጅምላ የመጨፍጨፉ ዐዋጅ ከመጽደቁ በፊት ከባሕር ዳርና ጎንደር አውሮፕላኖች ቀርበው መብራት እየጠፋ ወደ መቀሌ ተሸኙ፡፡ ጥሪታቸውን ይዘው በሱዳን መከላከያ ሽፋን ወደ ገዳሪፍ ገቡ፤ የወዳጅነት አሸኛኘት ተደረገላቸው፡፡ ከዐማራ ሕዝብ ጋር በቆዩበት ጊዜም ዲሽቃና ክላሽ እየተሰጣቸው በየቦታው በግፍ ዐማሮችን ሲጨፈጭፉ ቆዩ፡፡ የኮንዶሚኒየም ሕንጻ ላይ ወጥተው ከንጹሐን ላይ ተኮሱ፡፡ በቡሬ በሆቴላቸው በጅምላ እየገደሉ አስከሬኖችን አከማቹ፡፡ ከዚያስ? ከዚያማ አንድ አንድ ጋንታ ጦር ለአንድ የሥርዓቱ አገልጋይ ለጥበቃ ይመደባል፡፡ ልዩነቱ ግልጽ ነው፡፡ ‹በወርቃማው›ና በዐማሮች መካከል ያለው ልዩነት ከሰማይና ከምድር የሰፋ ነው፡፡ መገናኛ ብዙሃኑ የእነርሱ ነው፤ የአንድ ብሔር ዜጎች ተፈናቀሉ፤ ተጎዱ፤ ተባለ፡፡ 
አሁን በእኛ እና በእነርሱ መካከል ያለው የጠብ ግድግዳ መፈረስ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ የተሃድሶ ስብሰባ የሚፈታው አይሆንም፤ የበርሊን ግንብን እንደማርፈስ የቀለለ አይደለም፡፡ የዐማራ ሕዝብ ምርጫውን ያስተካክላል፡፡ ለጊዜው ሁለቱም የከፉ ቢሆንም ከከፋው የተሻለ የከፋውን ይመርጣል፡፡ 
ኧረ ጥራኝ ጫካው ኧረ ጥራኝ ዱሩ
ላንተም ይሻልሃል ብቻን ከማደሩ

የዐማራ ሕዝብ ተጋድሎ ይጥላል፤ ያሸንፋልም!!

No comments:

Post a Comment