Friday, September 16, 2016
*ከ60 ዓመታት በላይ በኮንሶ የኖሩ፣ ቋንቋቸው ኮንሶ የሆኑ ከ200 በላይ የአማራ ብሔር ተወላጆች ማሳቸው በእሳት ነዶ፣ ቤታቸው ተቃጥሎ ተፈናቅለዋል። በ4 አይሱዙ ጭነት መኪና ሼሌ ላይ የተበተኑት አማሮችን ኮንሶዎች ምግብ እና መጠለያ እየሰጡ ረድተዋቸዋል። የኮንሶን የአስተዳደር ጥያቄን ወደ ብሔር ግጭት ለመውሰድ በገዢው ስርዓት ህወሓት_ደኢህዴን የተፈጸመ ሴራ እንደሆነ ነዋሪዎች ይናገራሉ። የአማራ ብሔር ተወላጆች ዛሬ አርባምንጭ እንደገቡ ታውቋል። ከሰሞኑ ከ50 በላይ ሰዎች በኮንሶ መገደላቸው ይታወቃል። *መምህራን ለሁለት ሳምንት በካድሬዎች የሚሰጣቸውን ስልጠና እየተቃወሙ በመሆኑ ዝምታን መርጠው በስልጠናው የማይሳተፉ የማስተማር ፍቃዳቸው እንደሚነጠቅና እንደሚታገዱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። ከኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት የተጠሩ ካድሬዎች መምህራኑን በማባበል፣ በማስፈራራት...የተለያዩ ዘዴዎች ቢጠቀሙም ስብሰባው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከተያዘለት ሰዐት በፊት ያለምንም ውጤት መበተኑን ለመረዳት ተችሏል።ESAT Radio 15 Thu Sep 2016
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment