Neamin Zeleke a member of Patriotic Ginbot 7 council and Head of Foreign Affairs of the External Leadership ECADF interview: On TPLF aggression against Eritrea, on current affairs, and struggle of the Ethiopian people against the minority dictatorship.
Thursday, June 30, 2016
ጀግኖቹ የውስጥ አርበኞች በወያኔ ባለስልጣናት ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ቀጥሏል።
ወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ ከተማ አቶ ተድላ ካሳሁን የተባለ የትግራይ ባለሐብት በታጣቂ ወጣቶች እርምጃ ተወሰዶበት በ4 ጥይት ተደብድቦ እንደሞተና ትላንት June 28 ቀን በትግራይ በአድዋ ከተማ እንደተቀበረ ተገልጿል። ይህ ግለሰብ በወልቃይት የማንነት ጥያቄ ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የሰሜን ጎንደር ተወላጆች ላይ ከፍተኛ ክትትል እያደረገ የሚጠቁም የሚያሳስር፣ የሚያስደበድብና የሚያሰቃይ የወያኔ ስርዓት ታማኝ አገልጋይ ሲሆን ወልቃይቶች እንዲጠፉ በማስተባበር ፊርማ አሰባስቦ ለወራሪው የትግራይ አስተዳደር ያስገባ፥ የማፍለስ ዘመቻውን በዋናነት ከሚመሩት የትግራይ ባለሃብቶች አንዱና የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ በማፈንና በማፈናቀል ለተያዘው የጥፋት ዘመቻ ማስተባበሪያ 60,000 ብር ለአሸባሪው የትግራይ ሚሊሻ ጦር የሰጠ በዳንሻ የፋና ሆቴል ባለቤት መሆኑ ታውቋል።
ሰበር ዜና... ህወሃት በሰሜኑ ግንባር ተጨናንቋል የም/መቶ አለቃ ደጀኔ እና ወታደር በኩር ይናገራሉ!
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በምእራብ ትግራይ ሂሞራ በታች የማይካድራ ነዳጅ ማጠራቀሚያ አካባቢና እስከ ሰቲት ሁመራ እንዲሁም ጉናና ኡማህጂር ምስራቅ ትግራይና ዓዲ ግራት ድረስ የተሰማራዉ ከተለያዩ ክፍለ ጦሮችና ልዩ ሐይል እንዲሁም አካባቢ ሚሊሻዎች ተወጣቶ በስምሪት ላይ የሚገኘዉ የጸረ ሽብር ቡድን ወደ ግንባር እንዲሰማራ ባለመ መልኩ እየተበተነና እየተሰባጠረ እንደሚገኝ ታማኝ የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል።
ህብር ስኳር ከመንግስት ጋር ቅርበት ያላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ባደረሱት ጫና ፈተና ውስጥ መሆኑ ተነገረ ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2008)
ስኳር በማምረት በሃገሪቱ ያለውን የስኳር ዕጥረት ለመቅረፍ ብሎም የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት የተቋቋመው ህብር ስኳር አክሲዮን ማህበር በመንግስት በኩል በተደረገበት ጫና እንዲሁም ግለሰቦች ባሳደሩበት ተፅዕኖ ሁለቱ ስራ አስኪያጆች ሲሰደዱ ድርጅቱ በህወሃት የጦር ጄኔራሎች በሚመራው ሜቴክ እስረኛ መሆኑ ተገለጸ።
Wednesday, June 29, 2016
እንግዲህ የሕዝብ ምሬት እዚህ ደርሷል!
እንግዲህ የሕዝብ ምሬት እዚህ ደርሷል!
ከዚህ በሗላ ለአጋዚም ሆነ ለፌደራል ፖሊስ ያለው ብቸኛ አማራጭ አንድ ነው! አዎ! ከሕዝብ ጎን መሰለፍ፤ የሕዝብ ትግል አጋር መሆን ብቻ!!! ዛሬ በሀና ማርያም የሆነው የሕዝቡ ምሬት ጫፍ እንደደረሰ ትልቅ ማሳያ ነው። ለአጋዚም ሆነ ለፌደሬል ፖሊስ የማቂያ ደውልም ጭምር። ሕወሓት አብቅቶለታል! ሕዝቡ ከሕወሓት ለሚሰነዘርበት ጥቃት የአፀፋ ምላሽ መስጠት ጀምሯል! ከዚህ በሗላ ገሎ የሚሞት እንጂ ቆሞ ሞቱን የሚጠብቅ ዜጋ የለም! ጆሮ ያለው ይስማ፤ ልብ ያለው ልብ ይበል! አዎ! በጊዜ መንቃት ይሻላል! አለያ ለሞተ ስርአት ከለላ ለመሆን መሞከር ፍፃሜው ያው ሞት ነው! ዛሬ በሀና ማርያም አካባቢ የሆነውም ይህ ነው!
በፋሽስቱ ወያኔ ታዝዘው የነዋሪውን ቤት ለማፍረስ ተልከው ከሄዱት የወያኔ ፓሊስ አባላት ውስጥ ከ17 በላይ የሚሆኑ ፓሊሶች መገደላቸው እየተነገረ ነው!
#ETHIOPIAአዲስ አበባ በፋሽስቱ ወያኔ ታዝዘው የነዋሪውን ቤት ለማፍረስ ተልከው ከሄዱት የወያኔ ፓሊስ አባላት ውስጥ ከ17 በላይ የሚሆኑ ፓሊሶች መገደላቸው እየተነገረ ነው!
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከዚህ ፋሺስት መንግስት ጋር በመሞዳሞድ ህዝብን የምታስጨርስ ሁላ ይሄ ለእናንተ የማንቂያ ደወል ነው! እጃቺሁን በግዜ ሰብስቡና ከህዝብ ጋር ተሰለፉ! አለበለዚያ አይቀርልህም!
“አርበኞች ግንቦት 7ትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ የደረግነው ጉዞ የሃገር ወዳድነት መለኪያ እንጂ ወንጀል አይደለም” ብርሃኑ ተክለያሬድና እየሩሳሌም ተስፋው ኢሳት (ሰኔ 21 ፥ 2008)
ወደ ኤርትራ ያደረግነው ጉዞ የሃገር ወዳድነት መለኪያ እንጂ ወንጀል አይደለም ሲሉ እነብርሃኑ ተክለያሬድ ለፍርድ ቤት የተከሳሽነት ቃላቸውን ሰጡ። አርበኞች ግንቦት 7ትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሊሻገሩ ሲሉ ተይዘው በወህኔ ቤት የሚገኙት የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባላት የነበሩ ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድና ወጣት እየሩሳሌም ተስፋው ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ይህንን ያቀረቡት በጽሁፍ ሲሆን፣ እንዳያነቡ መከልከላቸውም ተመልክቷል።
Tuesday, June 28, 2016
የህወሃት አባላት ያልሆኑ የደህንነት አባላት በጥርጣሬ እየታሰሩ ነው ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :
የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት አባል የነበሩና በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ በተለይም በሶማሊያ በሚካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ላይ ቁልፍ ሚና ነበራቸው የተባሉ 3ቱ ነባር የደህንነት አባላትና አስተባባሪዎች ከተገደሉ በሁዋላ፣ ከግድያው ጀርባ እጃቸው ሊኖርበት ይችላል ተብለው የተጠረጠሩ የህወሃት አባላት ያልሆኑ የሌሎች ብሄረሰቦች የደህንነት አባላት እየተያዙ ነው። እስካሁን ከተያዙት መካከል አብዛኞቹ የኦሮሞ ተወላጅ የደህንነት አባላት ሲሆኑ፣ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጠበቂዎችም ይገኙበታል።
በአልሸባብ ተይዘው የነበሩትን የኢትዮጵያን ወታደሮች እና አንድ የፈረንሳይ የስለላ አባል ለማስለቀቅ ተልእኮ ተሰጥቷቸው የነበሩና ተልእኮዋቸውን በስኬ
ቤታቸው በህገወጥ መንገድ ይፈርስባችሁዋላ በመባላቸው ሰዎች ተቃውሞአቸውን ገለጹ
ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ወረዳ 11 በአካባቢው መጠሪያ ቀርሳና ኮንቱማ በሚባሉ አካባቢዎች ቤቶችን በህገወጥ መንገድ ሰርታችሁዋል የተባሉ ነዋሪዎች፣ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ካላፈረሱ ግን መንግስት እንደሚያፈርስባቸው ከተነገራቸው በሁዋላ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።
አርበኛ ታጋይ ሱራፌል ዘውዱ *አርበኞች ግንቦት 7*ን ተቀላቀለ፡፡ ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ የሰጠውን ቃለ-ምልልስ ተከታተሉ፡፡
በሰላማዊ ትግል ረጅም ጊዜ ሲታገል የነበረው የሰማያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ አርበኛ ታጋይ ሱራፌል ዘውዱ *አርበኞች ግንቦት 7*ን ተቀላቀለ፡፡ ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ የሰጠውን ቃለ-ምልልስ ተከታተሉ፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ.....
በሶማሊያ ሕይወቱን እየገበረ የሚገኘው ሰራዊት ላለፉት 6 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈለው ታወቀ
አልሸባብን ለመወጋት በሱማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ሕብረት ከ20 የማያንስ ሰራዊት ላለፉት 6 ወራት ምንም ዓይነት ደመወዝ እንዳልተከፈለው ቢቢሲ አጋለጠ::
አልሸባብን ለመዋጋት በሶማሊያ የሚገኘው ይኸው የኢትዮጵያን ጨምሮ የሌሎች አፍሪካ ሃገራትን ሰራዊት የያዘው እዚያው የሚገኘው የአፍሪካ ሕብረት ጦር በገንዘብ የሚደጎመው በአውሮፓ ህብረት የነበረ ቢሆንም የአውሮፓ ሕብረት ላለፉት 6 ወራት ገንዘብ እንዳልላከ ቢቢሲ ዘግቧል::
እንደ ቢቢሲ ዘገባ የአውሮፓ ሕብረት ለ እያንዳንዱ ሰራዊት በወር $1,028 ለመክፈል የተሰማማ ቢሆንም ወታደሮቹን ወደዚያው የሚልኩት ሃገራት $200 እንደሚቆርጡና ከሌሎች ክፍያዎች ተቆራርጦ ለወታደሮቹ $800 ዶላር ይደርሳቸዋል::
የአውሮፓ ሕበርት ገንዘቡን ላለፉት 6 ወራት ያልላከው በበሒሳብ ምክንያት ነው የሚል ድፍን ያለ ምላሽ ይሰጥ እንጂ በምን ዓይነት ሒሳብ ችግሩ እንደተፈጠረ የተባለ ነገር የለም::
ላለፉት 12 ወራት በአሚሶም ስር ያሉት የብሩንዲ; የዩጋንዳ; የኬንያና የኢቱኦጵያ ወታደሮች በአልሸባብ ጥቃት ሲደርስባቸው ቆይቷል::
ጁን 9 አልሸባብ 60 የኢትዮጵያ ወታደሮችን በሃልጋን መገደሉን; እንዲሁም ኤፕሪል 21 6 ወታደሮችን በቤይ አካባቢ መግደሉን መግለጹ ይታወቃል::
በተጨማሪም ፌብሩዋሪ 15 በሸበሌ አካባቢ 15 የኢትዮጵያ ወታደሮች በአልሸባብ መገደላቸው ተዘግቧል::
ይህንን ሁሉ የሕይወት መሰዋዕትነት የሚከፍልን ሃይል በሂሳብ ስህተት ደመወዝ ለ6 ወር መከልከልን ምን ይሉታል?
Monday, June 27, 2016
ሰላም ሰላም፤ ይሰማል…. ይህ ድምጽ የሚተላለፍላችሁ ከ ‘’ጊንቢን ገረመው’’ አዲሱ አየር ማረፊያ ነው፤ የዛሬው ዋዛ እና ቁምነገራችን እነሆ ሰኞ በማለዳ ተከስቷል። ብትችሉ ብትችሉ እነሆ የኢሳት ደረ ገጽ፣http://video.ethsat.com/?p=25253 ድረ ገጹ ካልሆነላችሁ ደግሞ በዝች ተስፈንጥራችሁ https://www.youtube.com/watch?v=5YntmbkfWJ0 ኢሳት ዩቲዩብ ጎራ ብላችሁ ቃኙን፤ ሁለቱንም ለማድረግ እምቢኝ ላላችሁ ወዳጆች ከቆይታ በኋላ የኢሃዴግ ባለስልጣናት ለጠላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን የጻፉትን ደብዳቤ በጽሁፍ ለማጋራት ጥረት እናደርጋለን። (ያው እኛ ብንልም ቅሉ እኔው ነኝ… ሃሃ) እና በተረፈ እንዴት ናችሁ!.... ጎሽ ደህና እንድትሆኑልኝ ነው እኔም ምኞት ፍላጎቴ… ጥቆማ አስተያየት መለገሳችሁን ቀጥሉ እሺ… ጎበዞች!!! WAZA ENA KUMENEGER 27 Jun 2016
በነበቀለ ጉርሜሳ መዝገብ እነ በቀለ ገርባ ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ አቃቤ ህግ መልስ ሰጠ *ፍ/ቤቱ ሁለት ተለዋጭ ቀጠሮዎችን ሰጥቷል
በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የኦፌኮ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 ተከሳሾች ግንቦት 26/2008 ዓ.ም ላቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ መልስ ሰጥቷል፡፡
ዛሬ ሰኔ 20/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የአቃቤ ህግ የመቃወሚያ መልስን በጽሁፍ ተቀብሏል፡፡ አቃቤ ህግ መልሱን በሁለት ከፍሎ ያቀረበ ሲሆን፣ አንደኛው ከ1-4ኛ ተከሳሾች እንዲሁም ሁለተኛው ከ5-22ኛ ተከሳሾች ያዘጋጀው መሆኑ ተመልክቷል፡፡ የአቃቤ ህግ መልስ በሁለት የተከፈለ ይሁን እንጂ በይዘት ተመሳሳይ መሆኑን ካቀረበው የጽሁፍ መልስ ለመገንዘብ ይቻላል፡፡
አንዳርጋቸው ጽጌ የታገተበትን ሁለተኛ አመት ስናስታውስ ለነጻነት ትግሉ ያለንን ቁርጠኝነት በማደስ ነው!! –የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ
አንዳርጋቸው ጽጌ የታገተበትን ሁለተኛ አመት ስናስታውስ ለነጻነት ትግሉ ያለንን ቁርጠኝነት በማደስ ነው!! –የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ....ለማዳመጥ ሊኩን ይጫኑ....
ሰበር መረጃ.. በመፍረስ እና በመሸሽ ላይ የሚገኘዉ ህወሃት !
እራሱን የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን እያለ የሚጠራዉ የወያኔ ስርአት ዋነኛ የጀርባ አጥነት የብሔራዊ መረጃ በዘረፋና በሽሽት ተጠምዷል።
በሰሞኑ የህዉ የብሔራዊ መረጃ 9 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ በአለም ዙሪያ የሚገኙ የህወሃት የመረጃ ክንፍ ቀድሞ የሰየማቸዉንና በስለላ ስራ ላይ ተሰማርተዉ የነበሩ የሌላ ብሔር አባላቶችን በሙሉ መልሶ ወደ ሐገር ቤት በማስገባት በምትካቸዉ ከ 242 የሚጠጉ የአንድ ብሔር ብቻ ተወላጅ የሆኑ የመረጃ ሰራተኞችን እየተካ ይገኛል።
ጉዳዩን በትኩረት የተመለከቱት መረጃዎቻችን የመፍረስ ወይም የሽሽት መንፈስ እንዳለዉ የሚናገሩለት ይህ ዝዉዉር ድንገተኛና ያልተገመተ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ወጪ እየተደረገበት መሆኑ እጅግ እንዳሳሰባቸዉ ጠቅሰዉ እነዚህ ወደ ተለያየ ሐገር የሚላኩት የአንድ ብሔር የስለላ አባላቶች በትምህርት ፍቃድ ( Study Permit ) በንግድ ፍቃድ ( Business Permit ) በበቤተሰብ ጉብኝት ወይም ትስስር ፍቃድ ( Relation Permit ) በስራ ፍቃድ ( Work Permit ) በመንግስታዊ የስራ ወይም በዲፕሎማቲክ አገልግሎት ፍቃድ ( Diplomatic Travel documents ) ሲሆን በዋነኛነት የአሜሪካን ዋሺንግተን ዲሲ የአዉሮፓዎቹ ኖርዌይና ብሪታኒያ እንዲሁም የመሳሰሉት እና ደቡብ አፍሪካ አዉስትራሊያ የዝዉዉሩ ትኩረቶችእንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
የብሔራዊ መረጃ ከፍተኛ አመራሮች የህወሃት ባለስልጣን ቤተሰቦችና የትዳር ጓዶች ባጠቃላይ የተካተቱበት ይህ ሽሽት ወይም ዘረፋ ከዚህ ቀደም በሐገሪቷ ላይ ከታዩ አይን ያወጡ የዘረኝነት መንፈሶች ለየት ያለ እና እጅግ የተቻኮለ ሲሆን በተለያየ አለም ከሚገኙ የመረጃ ሰራተኞች ዉስጥ እስከ 23/06/2016 ወደ ሐገር ቤት እንዲመለሱ ከተጠሩት ዉስጥ በአብዛኛዉ እየተሰወሩ መሆኑና የመመለሻ ጊዜያቸዉም ማለፉን ታማኝ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )
Sunday, June 26, 2016
አርበኞች ግንቦት 7ን ስለተቀላቀለችው ወጣት አርበኛ ሜሮን ዓለማየሁ: ስለርሷ የማውቀውን ልናገር
ይህን ጽሁፍ ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ በፌስቡክ ገጹ ያሰፈረው ነው:: የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ቢያነቡት መረጃ ያገኙበታል ብለን ስላሰብን ሼር አድርገነዋል::
ስለሜሪ የማውቀውን ያህል እንዲህ ልናገር
……..
ሜሮን ዓለማየሁ (ሜሪ)ን ለመጀመሪያ ጊዜ ያወኳት እኔ በዕንቁ መጽሔት ላይ ዋና አዘጋጅ ሆኜ ስሰራ ነበር፡፡ በ2006 ዓ.ም በነበረው ታላቁ ሩጫ ላይ ‹‹የተቃውሞ ድምጽ አሰምተዋል›› ተብለው ‹‹የጣይቱ ልጆች›› የሚል ስያሜ የነበራቸው የሰማያዊ ፓርቲ ዘጠኝ ሴት አባላት በፖለስ ቁጥጥር ስር ውለው ለቀናቶች ታስረው ነበር፡፡ በወቅቱም ይህ ጉዳይ ትልቅ መነጋገሪ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ የ‹‹ጣይቱ ልጆች›› ከእስር ከተፈቱ በኋላም፤ ለሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኃላፊ ይድነቃቸው ከበደ ደወልኩለትና ከልጆቹ መካከል ቢያንስ አንዳቸውን ቃለ-ምልልስ ልናደርግላቸው እንዳሰብን ነገርኩት፡፡ ይድነቅም፣ ከሜሮን ጋር ከተነጋገረ በኋላ ስልኳን ልኮልኝ ለቃለ-ምልልሱ ፈቃደኛ ሆና ፒያሳ ተቀጣጠርን፡፡ ሜሪም ከአንድ የሴት ጓደኛዋ ጋር አብራ መጥታ ተገናኘንና አንድ ጸጥ ያለ ባርና ሬስቶራንት ውስጥ ቁጭ አልን – ለቃለ-ምልልስ፡፡
Friday, June 24, 2016
አንዳርጋቸው ጽጌ የታገተበትን 2ኛ ዓመት በማስመልከት በኖርዌይ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ
የግንቦት 7 ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን የፀጥታ ሃይሎች ታግተው ለዘረኛውና አፋኙ የወያኔ ቡድን ተላልፈው የተሰጡበትን ሁለተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ደረጃ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አስተባባሪነት በጁን 23/ 2016 በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት እልህና ቁጭት የተሞላበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄዳል።ዝግጅቱ ያስጀመሩት የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር አቶ ለገስ ታፈስ እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ ቡሀላ በንግግራቸውም የግንቦት 7 ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ይዞለት የተነሳውን አላማ ከግብ ላማድረስ በቆራጥነት አበክራን መስራት እንዳለብን እና ለተቀጣጠለው ለጻነት አና ዲሞክራሲ እንዲሁም ሰባዊ መብት ለማስመለ እና አገር ለማዳን ለሚደረገው ትግል ለአንድ ጌዚ እና ለመጨረሻ ወያኔን በማስወገድ ለመላ የአራችን ህዝቦች በእኩልነት ላይ የተመስረተች ሀገር ለመፍጠር አንዳርጋቸው የጀመረውን የቆመለትን አላማ ከዳር ለማድረስ በምንችለው እራሳችንን የትግሉ አካል በማደረግ የዚግነት ግዴታችን መወጣት እንዳለብን አስገዝበዋል ስላማዊ ስልፍ ከ14.00 በኖሮይጃን ሰአት አቆጣጠር የተጀመረ ሲሆን ።
የእንግሊዝ መንግስት ዜጋዋን ለወያኔ መንግስት ተላልፎ ከተሰጠበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት ሁለት አመታት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለማስፈታት ተፅዕኖ መፍጠርhttp://www.zehabesha.com/amharic/archives/62373 አለመቻልዋን ያደረገችውን ጥረት አናሳና ውስን በመሆኑ ኢትዮጵያዊያኖቹን አስቆጥቶዋል። ኢትዮጵያዊኖቹም በእንግሊዝ ኢምባሲ ደጃፍ በመገኘት የወያኔን ህገወጥ አፈና እና እስር የሚቃወሙ የተለያዩ መፈክሮች በመያዝ የተቃውሞ ድምፃቸውን አሰምተዋል። በስፍራው የነበሩ ሠልፈኞች ሲያሰሟቸው ከነበሩ መፈክሮች መካከል free Andargachew Tsige, Where is your Actions, we are all Andrgachew Tsige እና ሌሎችም የተቃውሞ ድምፆች አሰምተዋል። ሰልፈኞችም የያዙትን ደብዳቤ በሰልፉ አዘጋጅ ኮሚቴ በአቶዳንኤል አበበ የድርጅቱ ሊቀመንበር በኩል ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ አስረክበዋል። የእንግሊዝ ኢምባሲው ተወካይ ጉዳዩን በትኩረትና በቅርበት እየሰሩ መሆኑን እስከመጨረሻው ክትትላቸውን እንደሚቀጥሉ ለሰልፈኞቹ አሳውቀዋል። በመጨረሻም ሰልፈኞቹ በአንድ ላይ በመሆን የግንቦት ፯ ህዝባዊ ኃይል መዝሙር ላንቺ ነው ሐገሬ ላንቺ ነው ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው የሚለውን ህዝባዊ መዝሙር በደማቅና በሀገራዊ ስሜት ዘምረው ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ ከቀኑ 15.00 ተጠናቋል። ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን !!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
በዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ
Thursday, June 23, 2016
አንዳርጋቸው ጽጌ የታገተበትን ሁለተኛ አመት ስናስታውስ ለነጻነት ትግሉ ያለንን ቁርጠኝነት በማደስ ነው!! – June 23, 2016 የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ
የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ
የወያኔ አገዛዝ በአቡደራቡህ መንሱር ሃዲ ይመራ ከነበረው የየመን መንግሥት ጸጥታ ሃይል ጋር በመመሳጠር አንጋፋውን መሪያችንንና የትግል ጓዳችንን አንዳርጋቸው ጽጌን ከሰነዓ አውሮፕላን ማረፊያ አግቶ በቁጥጥሩ ስር ካስገባ እነሆ ዛሬ ሁለት አመት ሞላው።
የአለም አቀፉን ህግ በመተላለፍ ህወሃት ድንበር ተሻግሮና ባህር አቁርጦ አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን ሲያግት ቢያንስ ሁለት ውጤቶችን ለማግኘት አሰፍስፎ እንደነበር መገመት አያስቸግርም። አንደኛው ሥልጣን ላይ ተደላድሎ ለብዙ አመታት የመቆየት ምኞቱን አደጋ ላይ የጣለበትን የአርበኞች ግንቦት 7 እንቅስቃሴ አከርካሪ በመምታት ትግሉን አሽመደምደዋለሁ የሚል የተሳሳተ ስሌት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ህወሃትን የሚግደራደር ሃይል የትም ቢሆን ሊያመልጥ እንደማይችል በማሳየት የኢትዮጵያን ህዝብ አንገት ለማስደፋትና በፍርሃት አንቀጥቅጦ ለመግዛት የታለመ የእብሪት ውሳኔ ነው።
《 የሰላም ደጆች ሲዘጉ የአመጽ በሮች ይከፈታለሁ! 》ወጣት ሜሮን አለማየሁ
ሰማያዊ ፓርቲን በመቀላቀል ለዓመታት የገዥውን ፓርቲ በሰላማዊ መንገድ ስትታገል የቆየችው ወጣት ሜሮን አለማየሁ ፤ መንግስት በየጊዜው ሰላማዊ ታጋዮችን ወደ እስር ቤት እየወረወረና እየገደለ በሰላማዊ ትግል ሊቀየር እንደማይችል በተደጋጋሚ አሳይቶናል በሚል መንፈስ የትግል ስልቷን መቀየሯን እና ነፍጥ አንስታ ስርዓቱን ለመፋለም እንደተዘጋጀች ለአርበኞች ግንቦት 7 ራዲዮ ከሰጠችው ቃለ መጠይቅ ላይ ለመረዳት ተችሏል።
Wednesday, June 22, 2016
Tuesday, June 21, 2016
አየር ሃይል የበረራ ስልጠናውን ሙሉ በሙሉ ወደ ድሬዳዋ አዛወረ
ሰኔ ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት አየር ሃይል በዚህ ሳምንት አዳዲስ በገዛቸው የጦር አውሮፕላኖቹ ድሬዳዋ ላይ ወታደራዊ ልምምድ የሚጀምር ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፓይለት ስልጠና ( pilot Training base) መቀመጫውን እስከሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ከድሬዳዋ ወደ መቀሌ እንዲያዛውር ትእዛዝ ተላልፎለታል። አየር ሃይል “ለአገራዊ ጉዳይ ቅድሚያ መስጠት አለባችሁ” በሚል ትእዛዝ አየር መንገዱ የድሬዳዋ የበረራ ማሰልጠኛውን እንዲለቅ ያስገደደ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድም በድሬዳዋ የቀሩትን 5 የመለማመጃ አውሮፕላኖች በሳምንቱ መጨረሻ ወደ መቀሌ ያዛውራል።
የወያኔ ሰልፍ በፍራንክፈርት እና ግንቦት 7 ! (በልጅግ ዓሊ)
በልጅግ ዓሊ
ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም በፍራንክፈርት የዶክተር ብርሃኑ ነጋን መምጣት አስመልክቶ በተጠራ ስብሰባ ላይ ለመካፈል ወደ ቦታው አምርቼ ነበር። የስብሰባው ቦታ ከወትሮ በተለየ በፖሊስ ተከቦ ከሩቅ ተመለከትኩና ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ወደ ቦታው ጠጋ አልኩ። ጥቂት ግለሰቦችም ከወዲህ ወዲያ ይራወጣሉ፣ ግርግር ይስተዋላል። ይበልጥ እየተጠጋሁ ሲሄድ አንዳንድ የማውቃቸውን የወያኔ ደጋፊዎችን ለመለየት ቻልኩ። እውነቱን ለመናገር በመጀመሪያ የወያኔ አባላት የዶክተር ብርሃኑ ስብሰባ ለመቃወም ያዘጋጁት ስልፍ ነው ብዬ ለማመን አልቻልኩም ነበር። እንዲያውም ስብሰባውን አትካፈሉም ተብለው የተከለከሉ ሰዎች ተቃውሞ መስሎኝ ነበር።
ከቤንሻጉል ጉምዝ … ክልል በደቡብ ሱዳን ወታደሮች ታግተው የሚወሰዱት ዜጎቻችን ቁጥቸው እየጨመረ በመሄድ ላይ እንዳለ ታወቀ።
ባገኘነው መረጃ መሰረት ፣በቤንሻጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን ጉባ አሜድላ በተባለ ወረዳ ደቡብ ሱዳንን ከሚያዋስን ቀበሌ በሱዳን ወታደሮች እየታገቱ የሚወሰዱት ወገኖቻችን ቁጥር እየጨመረ እየሄደ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።
በአካባቢው በእርሻ ስራ ላይ የተሰማሩ በርከት ያሉ ወገኖቻችን ።ሲናር በተባለ ግዛት ከደቡብ ሱዳን በመጡ ወታደሮች በባለፈው ሳምንት 9 ሰዎች ታግተው እንደተወሰዱ ከገለጹ በኋላ፥የክልሉ መንግስት ይሁን የፌዴራል መንግስት ለማስመለሰ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት የተደረገ ጥረት እንደሌለ ተገልጿል ።
ባለፈው ሚያዚያ ወር ውስጥ 24 ወገኖቻችን ከቤንሻጉል ጉምዝ ክልል ታግተው እንደተወሰዱ የገለጸው መረጃው ፥እነዚህን ለማስመለሰ ከንግግር ያለፈ ሌላ የተሰራ ስራ እንደሌለና እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በሁለቱ አገሮች መካከል የድንበር ውዝግብ እየከረረ በመሄድ ላይ በመሆኑ ታግተው ለተወሰዱት ወገኖቻችን ለህይወታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ እንዳሉ የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስታውቋል።
Monday, June 20, 2016
ሱዳን መከላከያዋን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ማስጠጋቷ ተሰማ ሰኔ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-
የኢትዮጵያ ታጣቂ አርሶደአሮች የሱዳንን አርሶደአሮች በማባረር መሬታቸውን እየቀሙ ነው በሚል የአገሪቱ መከላከያ ሃይል የተወሰነ ጦሩን ወደ ድንበር አካባቢ አንቀሳቅሷል። ምንም እንኳ ሱዳን ወታደሮቿን ብታንቀሳቅስም፣ እስካሁን ደረስ ወታደሮቿ በኢትዮጵያ አርሶአደሮች ላይ እርምጃ ለመውሰድ አልደፈሩም።
ኤርትራ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ለተሰነዘረባት ጥቃት የአሜሪካ እጅ እንዳለበት ገለጸች ሰኔ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :
- የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር እንደገለጸው ኢትዮጵያ በቅርቡ በኤርትራ ላይ ለሰነዘረችው ጥቃትም ሆነ በአካባቢው ላሰማራችው ሳራዊት የአሜሪካ እጅ አለበት። የአሜሪካ መንግስት ሁለቱም ሃይሎች ጦርነት ውስጥ እንዳይገቡ ያስጠነቀቀ ቢሆንም፣ የኤርትራ መንግስት የአሜሪካ መግለጫ ጎጂውንና ተጎጂውን እኩል የሚፈርጅ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብሎአል።
Sunday, June 19, 2016
በምርምርና በዳበረ ሃሳብ ሽፋን የሕወሓት ስልጣን እድሜ ማስረዘሚያ እና የትኩሳት መለኪያው 'ጀኔራል?' ጆቤ #Ethiopia #EPRDF #TPLF #Jobe #MinilikSalsawi #Change
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ጆቤ በአሁኑ ወቅት ይዘውት እየተራመዱት የሚገኘው አስተሳሰብ ሕወሓትም በማዘናጊያ አጀንዳነት እያራገባቸው ነው::ወደ ሚዲያው እንዲወጡ የተደረገው የቀድሞ የወያኔ አየር ሃይል አዛዥ ከተንበርካኪው ቡድን ወገን እንደሆኑ የሚነገርላቸው ታጋይ አበበ ተክለሃይማኖት በሽምቅ ተዋጊነት የጄኔራልነት ማእረግ አግኝተው አየር ሃይል እንደ ፋንታ በላይ ባይመሩትም ገለውት ነበር::ሰሞኑን በወያኔ መንግስት እየተደጎሙ በሚኖሩት አዲስ አድማስ እና ሪፖርተር ጋዜጣ እዩኝ እዩኝ ያበዙት አበበ ተክለሃይማኖት አንድም ትኩሳት መለኪያ ሌላም ሕወሓት እድሜዋ እንዲረዝም እንደ መሽረፈት ሲሆኑ ጎን ለጎን ወደ ስልጣ እየተጠጋጉ መሆኑን ጽሁፎቻቸው ያሳብቃሉ::ሕወሓት በስልጣን እንዲቆይ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ የተሻለ አምባገነንነት እንዲፈጠር እየሰሩ ሲሆን የትግል አጋሮቻቸውን የተቹ መምሰሉ የሕወሓት የማዘናጊያ እና የማደናበሪያ አንዱ ስትራተጂ መሆኑን ልንነቃ ይገባል::
Ethiopia Dismisses Human Rights Watch Report on Oromia Region
Dan Joseph / VOA
Ethiopian authorities have dismissed a 61-pagereport by Human Rights
Watchthat details the killings of more than 400 people over the past seven months in a crackdown on protests in the country’s Oromia region.
Government spokesman Getachew Reda told VOA Thursda
ራስህን ጠይቅ ( ሄኖክ የሺጥላ )
ፖለቲከኛ ማለት ከአብዛንኛው ህዝብ በተለየ የመዋሸት ስጦታ የተሰጠው ሰው ማለት ነው ። ፖለቲከኞች መጀመሪያ ታጋይ በመሆን ይጀምሩና ፥ የሚታገላቸውን በማፍራት ይጨርሳሉ!
ፖለቲከኞችን ሁሉ አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ፥ ሁሉም የሚያወሩት ስለ አንድ ጭቁን ገበሬ ሲሆን ፥ በሚገርም ሁኔታ ሁሉም ገበሬውን አያውቁትም !
ፖለቲከኞች ሁሉም ስለተጨቆነ ህዝብ በተሰናሰነ መንገድ ማውራት ይችላሉ ። በዚህም ዲስኩራቸ
Ethiopia: Rally to protest blood money extravaganza
Ethiopia, a country where millions are starving and the world is scrambling to raise aid to save lives, few cronies and their corrupt allies are embezzling billions of dollars. This blood money is now being used to throw lavish party from July 3rd through 9th in the name of soccer festival. Every morally correct human being should stand against such immoral and unjust act. We call up on all Ethiopian / Ethiopian Americans to stand with the millions of impoverished and starving children of Ethiopia by boycotting AESAONE festivity and please join us at the protest on:
Sunday July 3, 2016 at 2:00 PM
Place – Mount Vernon High School
8515 Old Mt Vernon RD
Alxandria, VA. 22309
Organizer – DC Joint Task Force
For more info. Email “dcjointtaskforce@gmail.com”
http://ecadforum.com/2016/06/18/ethiopia-rally-to-protest-blood-money-extravaganza/
Friday, June 17, 2016
Seminar med Berhanu Nega fra Ginbot 7 Publisert: 17 juni 2016 -
Berhanu Nega, leder for den etiopiske opposisjonsorganisasjonen Patriotic Ginbot 7, deltok nylig på seminar i regi av NOAS. Både UDI, UNE og Landinfo var til stede på seminaret, som ga nyttig informasjon om forholdene i Etiopia.
የአዕምሮ ሚዛን የመጠበቅ ስትራቴጂ ፡ ዶ/ር ታደሰ ብሩ
በተፋፋመ ቅራኔ ውስጥ የገባ ሰው የአዕምሮ ሚዛኑን ሊያጣ ይችላል። ቀድመው ያልታዩ እንቅፋቶች፣ ጥርጣሬዎች፣ ከወዳጆች የሚቀርቡ ትችቶች እና መሰል ነገሮች ተደራርበው ፍልሚያ ው1ስጥ ያለን ሰው እዕምሮ ሊረብሹ ይችላሉ። በዚህም ምክንያት ተፋላሚ ሰው በጥርጣሬና ንዴት ውስጥ ሆኖ ውሳኔዎችን የሚሰጥበት አደጋ አለ። ሆኖም ግን ይህ ሰው በአሸናፊነት እንዲወጣ የአዕምሮውን ጉልበት በሚገባ መጠቀም ይኖርበታል።
ዳግመኛ የመንግሥት ዋይታ በተቃዋሚዎች ላይ (ጣሰው አሰፋ)
ጁን 11 2016 በፍራንክፈርት ከተማ ላርበኞች ግነቦት7 የድጋፍ ማሰባሰቢያ (Fundraising) ፕሮግራም ላይ ተገኝቼ ስለነበር አንዳንድ ገጠመኞቼን በቦታው ላልነበሩ ለማሰማት የሚለው የዚህ ማስታወሻ መነሻዬ ነው። ዳሩ ግን፤ በሱ ላይ ትረካዬን ከመቀጠሌ በፊት፤ ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ፤ አንድ ከ 11 ዓመት በፊት የሆነና በ11.06. 2016 ከሆነው ሁኔታ ጋር ተመሳሳይነት የነበረው ድርጊትን ስላስታወስኩ እሱን ላስቀድም፤
Thursday, June 16, 2016
Ethiopia's security forces accused of killing more than 400 protesters
Rodney Muhumuza and Elias Meseret, The Associated Press
Published Thursday, June 16, 2016 7:05AM EDT
Last Updated Thursday, June 16, 2016 9:06AM EDThttp://www.ctvnews.ca/world/ethiopia-s-security-forces-accused-of-killing-more-than-400-protesters-1.2948081#_gus&_gucid=&_gup=Facebook&_gsc=ixs0Q3c
KAMPALA, Uganda -- Ethiopian security forces have killed more than 400 people in a crackdown on protests in the Oromia region since November, Human Rights Watch said Thursday.
Tens of thousands of others have been arrested, the rights group said in a new report , citing the accounts of 125 protesters, witnesses and others.
The student-led protests were sparked by a government plan to expand the municipal boundaries of the capital, Addis Ababa, into Oromia, where farmers fear they will lose their land. The development proposal has since been retracted.
The security forces used live ammunition for crowd control repeatedly, killing one or more prote
Eritrea files formal complaints to the Security Council on TPLF’s military aggression ESAT News (June 15, 2016)
Eritrea’s Ambassador to the UN, Girma Asmerom said on Wednesday that the world should condemn the military aggression by the TPLF regime in Ethiopia.
Speaking to ESAT, the Ambassador said Eritrea has filed its formal complaints to the UN Security Council and is waiting to hear from the world’s governing body.
Wednesday, June 15, 2016
አልሸባብ 89 የኢትዮጰያ ወታደሮችን እንዴት ሊገድል ቻለ? አልሸባብ የኢትዮጵያን የስለላ መረብ ኔት ወርክ አገኘው ወይስ በአልሸባብ ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያ የመረጃ ሰዎች ተያዙ?
ካለፉት 6 ወራት ጀምሮ በርካታ የኢትዮጵያ ወታደሮች በአልሸባብ ወታደሮች ቢገደሉም የሚዲያ ሽፋን አላገኙም፤ ለወደፊቱም ጥቃቱ ይጨምራል የሚል ከፍተኛ ስጋት በገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት በኩል ተፈጥሯል። ለምን? በሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር አደጋ ውስጥ እየገባ ይሆን? ድብረጺዮን ወደ ሶማሊያ መመላለስ ለምን አበዛ?
የአፍሪካ ህብረት የማይቆጣጠረው በድብቅ የገባ የኢትዮጵያ ጦር ሶማሊያ ውስጥ መኖሩስ ይታወቃል? ለምን በድብቅ ማስገባት ተፈለገ?
የኢትዮጵያ የደህንነት ሰራተኞች ሁኔታስ እንዴት ነው? የእርስ በርስ መተማመን አለ? የደህንነት ሰራተኞች ለምን ታሰሩ? የተገደሉስ ይኖሩ ይሆን?
በሌሎች የአሚሶም አባል አገሮች በተለይም በጅቡቲና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነትስ እንዴት ነው?
በእነዚህና በሌሎችም ጉዳዮች ኢሳት ከአዲስ አበባ የደህንነት ጽ/ቤት ያገኘውን ሚስጢራዊ መረጃ በመንተራስ የቀረበ ዘገባ
ጥብቅ ስሳሰቢያ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ስደተኞችን ከሰሰ!
በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ ላይ የሚገኘዉ የወያኔ ኢንባሲ ከፍተኛ የሆነ ስህተት በመስራት ላይ ይገኛል! ይህዉም በዚያ በደቡብ አፍሪካ በስደት የሚገኙ በተለይም የወያኔን ስርአት በመቃወም የሚኖሩ ወገኖች በህጋዊ መንገድ በሐገሪቷ የስደተኞች ቢሮ ( DAPARTMENT OF HOME AFFAIR ) የመታወቂያ ወረቀት ወይም የመኖሪያ ፍቃድ የተሰጣቸዉ ግለሰቦች ለንግድና ለተለያየ የአገልግሎት ጥቅም ወደ ሌሎች ሐገር ሊያሸጋግር የሚችል የጉዞ ሰነድ ( PASPORT ) እንዳያገኙ ፈጽሞም ኢንዳይሰጣቸዉ የወያኔዉ ተላላኪ የሆነዉ የኢትዮጵያ እንባሲ ክስ አቅርቧል!
በመሆኑም አንድ ስደተኛ ወረቀት ሊያሰጠዉ ከሚችለዉ መስፈርት አንዱ የወያኔን ስርአት በመቃወሙ ምክንያት መሰደዱን ማረጋገጥ ከመፋሉ የተነሳ በመሆኑ ማንኛዉም ስደተኛ በስደተኝነት እያለ የጉዞ ሰነድ ( Pasport ) የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
የህጉ አንክዋር እንዲህ ይላል "አንድ ስደተኛ ግለሰብ ለደህንነቱ ሲባል ከኢትዮጵያ ዉጭ በጉዞ ሰነዱ የትም ሐገር የመጓዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ"
ነገር ግን የኢትዮጵያ ኢንባሲ በክሱ ላይ እንዳስቀመጠዉ መረጃ አለኝ እያለ ሙግት ጀምሯል! ይህዉም በተባበሩት መንግስታት ዉል መሰረት የደቡብ አፍሪካ የስደተኞች ቢሮ የጉዞ ሰነድ ( passport ) የሚሰጣቸዉ ኢትዮጵያዊያኖች ፓስፖርቱን የሚፈልጉት ወደ ኤርትራ በመጓዝ አርበኞች ግንቦት 7 የተባለ የሽብር ቡድንn ለመቀላቀል ነዉ! ። የሚል ተልካሻ መነሻ ሐሳብ ሲሆን ክሱ በጥንቃቄ እንዲታይለት አቤቱታዉን አቅርቧል።
ይህን መሰል ክህደት በገዛ ሕዝቡ ላይ የሚፈጽመዉ ተላላኪዉ የወያኔ ኢንባሲ በሰሞኑ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የደቡብ ተወላጆች በተለይም የከንባታና ሐዲያ ልጆችን ሰብስቦ አስገራሚ የሆነ የዉንብድና የሐሰት ስራ በገዛ ወገኖቹ ላይ ሊፈጽም ተዘጋጅቷል!
አምባሳደር ሙሉጌታ የተገኙበት የደቡብ ህዝቦች ስብሰባ ላይ የተገለጸዉ ተንኮል... በስደተኝነት ህጋዊ ወረቀት አግኝታችሁ ከኢትዮጵያ ዉጭ የትም መሄድ የሚያስችል የጉዞ ሰነድ ( Pasport ) ያላችሁ የደቡብ ተወላጆች ሐገራችሁ ገብታችሁ ገንዘባችሁን ተጠቀሙ ወረቀታችሁ እንዳይበላሽ ከዚህ ወደ ሱዳን ወይም ኬንያ ወይም ደግሞ ጅቡቲ ትሄዱና ከዚያ ደግሞ በኢትዮጵያ ፓስፖርት ወደ ሐገራችሁ መግባት ትችላላችሁ በማለት ስደተኞችን ለከሰሱት የኤርትራ ጉዞ መረጃ መሰብሰቢያ በማድረግ ለመጠቀም እያመቻችሁ ይገኛሉ።
በመሆኑም በዚህ እኩይ ተግባር የተበሳጩ ኢትዮጵያዊያን የወያኔ ኢንባሲ ያደረጋቸዉን ገለጻዎች በሙሉ በድምጽና በምስል በመያዝ ለሚመለከተዉ አካል አስተላልፈዉ ጉዳዩ በተለየ መልኩ እየታየ እንደሚገኝ መረጃ የደረሰዉ የወያኔ ኢንባሲ ወደ ሐገር ቤት የላከዉን ሪፖርት የዉስጥ ምንጮች አሳልፈዉ ሰጥተዋል።
ማሳሰቢያ..... በደቡብ አፍሪካ የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በሙሉ ይህን የወያኔ ተንኮል ግምት ዉስጥ በማስገባት ከተጠነሰሰባችሁ ሴራ እንድትጠነቀቁ እና እራሳችሁን እንድትጠብቁ እናሳስባለን ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ሰሞኑን በፍራንክፈርት፣ ጀርመን ለድርጅታቸው በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ላይ ለደጋፊዎቻቸው ያሰሙት ንግግር። "ፕሮፌሰሩ በዚህ ስብሰባ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግረናል፣" ብለዋል
የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ሰሞኑን በፍራንክፈርት፣ ጀርመን ለድርጅታቸው በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ላይ ለደጋፊዎቻቸው ያሰሙት ንግግር። "ፕሮፌሰሩ በዚህ ስብሰባ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግረናል፣" ብለዋል።| Speech by Arbegnoch Ginbot 7 Chairman Professor Berhanu Nega at fundraising event in Germany - June 2016
Click Here To Watch | ለማየት እዚህ ይጫኑ፦
Tuesday, June 14, 2016
ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ሕወሃት) ሰኔ 7 ቀን 2008 በጾረና ግምባር ወደ ኤርትራ ግዛት ተንቀሳቅሶ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ባወጣው አጭር መግለጫ “የሕወሃት አገዛዝ በፆረና ማዕከላዊ ግንባር ጦርነት ከፍቶብናል” ነበር ያለው።
የኤርትራ መንግስት “ኢትዮጵያ ጥቃት ፈጸመችብኝ” አለማለቱ ኤርትራውያን የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘረኛና አምባገነን አፋኝ ሥርዓት ስር ደፍጥጦ እየገዛ ያለው በሕዝብ ያልተመረጠና ከአንድ አነስተኛ የህዝብ ብዛት ካለው ብሄር የወጣ እራሱን የብሄረሰቡ ነጻ አውጪ እያለ የሚጠራ አናሳ ቡድን ሕወሃት እንደሆነ በሚገባ ስለሚያውቅ ነው።
ለወትሮው ኢትዮጵያን በመግዛት ልይ ያለውን ዘረኛና ጨቋኝ ቡድን “ሕወሃት” በሚለው ትክክለኛ መጠሪያው አዘውትረው የሚጠሩት ከሕወሃት የአፈና አገዛዝ ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን፣ የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች፣ የመብት ተሟጋቾች እና አንዳንድ በሃገር ቤት የሚገኙ ኮፍጣና የተቃዋሚ አባላት ብቻ ነበሩ። ይሁንና አለማቀፍ የዜና አውታሮች በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበሮች ጦርነት ተቀሰቀሰ መባሉን ሰምተው ጆሮዋቸውን አቅንተው በሚጠብቁበት ወቅት የኤርትራው ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር “የሕወሃት አገዛዝ በፆረና ማዕከላዊ ግንባር ጦርነት ከፍቶብናል” የሚል ቋንቋ በመጠቀሙ ምዕራባውያኑ የዜና አውታሮች ምናልባትም ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያውን አገዛዝ በትክክለኛ ስሙ “ሕወሃት” ሊጠሩት ተገደዋል።
ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ሕወሃት) እራሱን “ኢሕአዴግ” በሚባለው ጭንብል ስር ቀብሮ ለዓመታት ኖርዋል። እርግጥ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ “ኢሕአዴግ” በሚባለው ድርጅት ስር አለን የሚሉትን ድርጅቶች “ጥርስ የሌላቸው አንበሶች” እንደሆኑ ጠንቅቆ ያውቃል። የድርጅቶቹ ዋነኛ ተግባርም እንወክለዋለን የሚሉትን ብሄረሰብ/ሕዝብ እጅና እግር አስረው ለሕወሃት እንዲገዛ ማድረግ ነው።
አልሸባብ 89 የኢትዮጰያ ወታደሮችን እንዴት ሊገድል ቻለ?
አልሸባብ የኢትዮጵያን የስለላ መረብ ኔት ወርክ አገኘው ወይስ በአልሸባብ ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያ የመረጃ ሰዎች ተያዙ?
ካለፉት 6 ወራት ጀምሮ በርካታ የኢትዮጵያ ወታደሮች በአልሸባብ ወታደሮች ቢገደሉም የሚዲያ ሽፋን አላገኙም፤ ለወደፊቱም ጥቃቱ ይጨምራል የሚል ከፍተኛ ስጋት በገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት በኩል ተፈጥሯል። ለምን? በሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር አደጋ ውስጥ እየገባ ይሆን? ድብረጺዮን ወደ ሶማሊያ መመላለስ ለምን አበዛ?
ኢትዮጵያ፡ የዘ-ህወሀት ወንጀለኞች ያልተመዘገበ ቦንድ ባሜሪካ ሲሸጡ ማጅራቸዉን ተያዙ!- ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ባለፈው ሳምንት የዩኤስ አሜሪካ የቦንድ እና አክስዮን ልውውጥ ኮሚሽን/U.S Securities and Exchange Commission (SEC) በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ለአራት ዓመታት ያልተመዘገበ ህገ ወጥ የቦንድ ሽያጭ በማካሄድ ያገኘውን 6.5 ሚሊዮን ዶላር እንዲመልስ (ዲስጎርጅመንት ወይም በትክክል ስተርጎም “ማስተፋት”) ቅ ጣት በይኖበታል ።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61996(ዲስጎርጅመንት ወይም “ማስተፋት” በአሜሪካን ሕግ ማለት አንድን ዋጋ ያለውን ነገር በህገወጥ መልክ ወይም ደግሞ የሞራል ስብዕናን በጣሰ መልኩ የተገኘን ትርፍ ለባለመብቱ አካል መልሶ እንዲያስረክብ የሚያስገድድ ሕግ ማለት ነው።) የዘ-ህወሓት ገዥ ቡድን ተገዶ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በሕገ ወጥ ዘዴ የበላዉን አጠፋለሁ ብሎ ለአሜሪካ የቦንድ እና አክስዮን ልውውጥ ኮሚሽን በፊርማ አረጋገጧል ።
ይህ ትችት በእርግጥ ትንሽ ቴክኒካዊነት አጠቃቀምን የያዘ በመሆኑ ከሕግ አንጻር ሲታይ ለአንዳንድ ሕግን አጥብቀው ለማይከታተሉ አንባቢዎች ትንሽ ለመረዳት አስቸጋሪ ፅሁፍ ሊሆን ይችላል።
በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ግጭት ሁለቱም አገራት እርስ በእርስ ተወነጃጀሉ ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2008)
በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ግጭት መከሰቱን ሁለቱም መንግስታት አስታወቁ። እሁድ ሰኔ 5 ቀን 20008 ዓም በፆረና ግንባር ተከሰተ በተባለ ግጭት ሁለቱም መንግስታት ዕርስ በዕርስ የተወነጃጀሉ ሲሆን፣ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን በሁለቱም ወገን ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ግጭት መከሰቱን የዘገቡት ለገዢው ፓርቲ ቅርበት ያላቸው ድረገጾች ሲሆን፣ ኤርትራ መጠነ ሰፊ ጥቃት ተሰንዝሮባታል ብለዋል፣ ውጊያው በፆረና እና ዛላምበሳ ግንባር እንደሆነም አመልክተዋል። ለገዢው ፓርቲ ቅርበት ያላቸው ሚዲያዎች የጦርነቱን ዜና በሚዘገቡበት ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ዝምታን መርጦ ቆይቷል።
የኤርትራ መንግስት በይፋ ዕሁድ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ በፆረና ግንባር ጥቃት እንደተሰነዘረበት ገልጿል። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር “ወያኔ የመንግስት ጥቃት ሰነዘረ” በሚል ርዕስ ባወጣው አጭር መግለጫ በፆረና ማዕከላዊ ግንባር ጥቃት እንደተሰነዘረበት ገልጿል።
“የኤርትራ መንግስት በፆረና ግንባት ጥቃት ለመሰንዘር በመሞከሩ የአጸፋ ርምጃ ተወስዷል።” በምል ርዕስ ባወጣው መገለጫ፣ ከኤርትራ መንግስት ጋር ውጊያ መድረጉን አረጋግግጧል። በመግለጫው ስለጉዳቱ መጠን የተገለጸ ነገር ባይኖርም አቶ ጌታቸው ረዳ በሁለቱ ወገን ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጎዳዮች ፅቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸው ረዳ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት መግለጫ ግጭት እንደነበር አረጋግጠው፣ በሁለቱም ውገን ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን በኤርትራ ወገን ደግሞ የበረታ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ሰኞ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ግጭት መብረዱን አረጋግጧል።
Monday, June 13, 2016
ኤርትራ በጾረና ግንባር ጥቃት እንደተሰነዘረባት አስታወቀች
ሰኔ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ በጾረና ግንባር የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ትናንት እሁድ ጥቃት መፈጸማቸውን አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ስለ ጥቃቱ ዝርዝር መግለጫ እንደሚያወጣ ገልጿል። በኢትዮጵያ በኩል እስካሁን በይፋ የተሰጠ መግለጫ የለም። በሁለቱም ድንበሮች ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየታዬ ሲሆን፣ ጥቃቱ ወደ ሙሉ ጦርነት ይሸጋገር አይሸጋገር ገና የታወቀ ነገር የለም። አርበኞች ግንቦት7 ባወጣው መግለጫ ጦርነቱ ህወሃት ከገባበት የውስጥ አጣብቂኝ ለመውጣት የጀመረው ነው ብሎአል።
ወያኔ ከገባበት ውጥረት ለመውጣት በከፈተው ጦርነት ትኩረታችን አይቀለበስም !!! – መግለጫ June 13, 2016
በጥጋብና እብሪት የተወጠረው የህወሃት አገዛዝ በትናንትናው ዕለት ዕሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008 በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በኩል ከኤርትራ ጋር በሚያዋስኑ የድንበር ቦታዎች ላይ ጦርነት ጀምራል፤ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ይህን ዜና አረጋግጠው ዘግበዋል። ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በወያኔ በኩል ስለጦርነቱ ምንም የተሰጠ መግለጫ ባይኖርም የኤርትራ መንግሥት በጾረና ግንባር በኩል ጥቃት እንደተፈጸመበት ትናንት ማምሻውን ይፋ ባደረገ መግለጫ አረጋግጦአል።
መራሹ ጦር በኤርትራ ድንበር ላይ ትንኮሳ መጀመሩ ሀቅ ነው። ዶ/ር ታደሰ ብሩ
ህወሓት ለስልጣን ወንበሩ እንጂ ለመሬት፣ ለድንበር፣ ለመንደር፣ ለወደብ፣ ለሕዝብ ደንታ እንደሌለው የሃያ አምስት ዓመታት ታሪኩ ያረጋግጣል። ፍላጎቱ ከላይ ከተዘረዘሩት አንዱ እንኳን ቢሆን ኖሮ ጦርነቱ ድሮ በተደረገ ነበር።
የህወሓት ዓላማ በኤርትራ ምድር የሚገኙ የኢትዮጵያ የነፃነትና የዲሞራሲ ኃይሎችን ማጥፋት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት እየተደራጁ የሚገኙትን የዲሞክራሲ ኃይሎችንም ማፈግፈጊያ ማሳጣት ነው። ህወሓት ጦርነት ያወጀው በኢትዮጵያዊያን ላይ ነው። የወያኔ ወረራን ማክሸፍ የህወሓት እድሜ ማሳጠር ነው።
ጠላት ጎምዛዛ ሎሚ ሲወረውርልን ጨምቀን ጫፋጭ የሎሚ ጭማቂ (ሊሞናይድ) መጠጣት የኛ ስራ ነው !!!
ዶ/ር ታደሰ ብሩ
Sunday, June 12, 2016
Saturday, June 11, 2016
ESAT Special program Ethiopian Soliders in Somalia
http://ecadforum.com/2016/06/11/esat-special-program-ethiopian-soliders-in-somalia/
ESAT Special program Ethiopian Soliders in Somalia. ESAT TV and Radio is the first independent Ethiopian Satellite Television service and Radio Station who broadcast to Ethiopia and the rest of the world.
በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ኣስተናጋጅነት ኣርበኞች ግንቦት ሰባት በኖርዲክ ኣገሮች ጆን 4-2016 ያካሄደው የገንዘብ ማሰባሰብ ሰነስርዓትና ህዝባዊ ውይይት የፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሸው ያደረጉት ንግግር
በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ኣስተናጋጅነት ኣርበኞች ግንቦት ሰባት በኖርዲክ ኣገሮች ጆን 4-2016 ያካሄደው የገንዘብ ማሰባሰብ ሰነስርዓትና ህዝባዊ ውይይት
የፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሸው ያደረጉት ንግግር
According to Professor Getachews speech social scientists have proved that an ethinic based dominant party which represents less than 20% of the population canot be democrat. Therefore, Weyane which can represent max 7% of the Ethiopian population, will never ever be democrat.
ሰበር ዜና: አክሱም ስታዲየም ፌደራል ፖሊሶች ተፈነከቱ – ሕዝቡ በድንጋይ ተከታከተ (ፎቶዎች ይዘናል)
በትግራይ አክሱም ስታዲየም ውስጥ በተደረገ የ እግር ኳስ ጨዋታ ደጋፊዎች ባነሱት ሁከት ፖሊሶችና በርካታ የስፖርት ደጋፊዎች ተፈነከቱ::
በአክሱም ስታዲየም የአክሱም ከተማ እና የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ እየደረገ ባለበት ወቅት ደጋፊዎች ባነሱት ሁከት የተነሳ በርካታ ሰዎች ሲቆስሉ ስታዲየሙ ሄልሜት ባጠለቁ ልዩ ኃይሎች መከበቡ ታውቋል::
በኢትዮጵያ ከፍተኛው ሊግ የሚጫወቱት ሁለቱ የትግራይ ክልል ክለቦች ደጋፊዎች ያነሱት ሁከት ላይ ተጫዋቾች ሳይቀሩ መፈንከታቸውና ደጋፊዎች በድንጋይ ሲከታከቱ እንደቆዩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::
ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም የቡና ደጋፊዎች ባነሱት ብጥብጥ ስታዲየሙ ላይ እና በሰዎች ላይ ጉዳት ከመድረሱም በላይ አንድ ሰው መሞቱን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::
Subscribe to:
Posts (Atom)