የግንቦት 7 ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን የፀጥታ ሃይሎች ታግተው ለዘረኛውና አፋኙ የወያኔ ቡድን ተላልፈው የተሰጡበትን ሁለተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ደረጃ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አስተባባሪነት በጁን 23/ 2016 በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት እልህና ቁጭት የተሞላበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄዳል።ዝግጅቱ ያስጀመሩት የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር አቶ ለገስ ታፈስ እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ ቡሀላ በንግግራቸውም የግንቦት 7 ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ይዞለት የተነሳውን አላማ ከግብ ላማድረስ በቆራጥነት አበክራን መስራት እንዳለብን እና ለተቀጣጠለው ለጻነት አና ዲሞክራሲ እንዲሁም ሰባዊ መብት ለማስመለ እና አገር ለማዳን ለሚደረገው ትግል ለአንድ ጌዚ እና ለመጨረሻ ወያኔን በማስወገድ ለመላ የአራችን ህዝቦች በእኩልነት ላይ የተመስረተች ሀገር ለመፍጠር አንዳርጋቸው የጀመረውን የቆመለትን አላማ ከዳር ለማድረስ በምንችለው እራሳችንን የትግሉ አካል በማደረግ የዚግነት ግዴታችን መወጣት እንዳለብን አስገዝበዋል ስላማዊ ስልፍ ከ14.00 በኖሮይጃን ሰአት አቆጣጠር የተጀመረ ሲሆን ።
የእንግሊዝ መንግስት ዜጋዋን ለወያኔ መንግስት ተላልፎ ከተሰጠበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት ሁለት አመታት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለማስፈታት ተፅዕኖ መፍጠርhttp://www.zehabesha.com/amharic/archives/62373 አለመቻልዋን ያደረገችውን ጥረት አናሳና ውስን በመሆኑ ኢትዮጵያዊያኖቹን አስቆጥቶዋል። ኢትዮጵያዊኖቹም በእንግሊዝ ኢምባሲ ደጃፍ በመገኘት የወያኔን ህገወጥ አፈና እና እስር የሚቃወሙ የተለያዩ መፈክሮች በመያዝ የተቃውሞ ድምፃቸውን አሰምተዋል። በስፍራው የነበሩ ሠልፈኞች ሲያሰሟቸው ከነበሩ መፈክሮች መካከል free Andargachew Tsige, Where is your Actions, we are all Andrgachew Tsige እና ሌሎችም የተቃውሞ ድምፆች አሰምተዋል። ሰልፈኞችም የያዙትን ደብዳቤ በሰልፉ አዘጋጅ ኮሚቴ በአቶዳንኤል አበበ የድርጅቱ ሊቀመንበር በኩል ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ አስረክበዋል። የእንግሊዝ ኢምባሲው ተወካይ ጉዳዩን በትኩረትና በቅርበት እየሰሩ መሆኑን እስከመጨረሻው ክትትላቸውን እንደሚቀጥሉ ለሰልፈኞቹ አሳውቀዋል። በመጨረሻም ሰልፈኞቹ በአንድ ላይ በመሆን የግንቦት ፯ ህዝባዊ ኃይል መዝሙር ላንቺ ነው ሐገሬ ላንቺ ነው ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው የሚለውን ህዝባዊ መዝሙር በደማቅና በሀገራዊ ስሜት ዘምረው ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ ከቀኑ 15.00 ተጠናቋል። ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን !!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
No comments:
Post a Comment