በኖርዲክ አባል ሃገራት የአርበኞች ግንቦት 7 የውይይት እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በኦስሎ ከተማ በደማቅ ሁኔታ መከበሩ ከተለያዮ አባል ሃገራት
በመጡ አባላት መካከል የነበረው አና መተሳሰብ ከምንም በላይ የሚያሳይ አኩሪ ተግባር ሲሆን የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆኑት የኖርዌይ የአርበኞች ግንቦት7 አባላት በሙሉ ለትግሉ ያላቸውን ቆራጥነት ያሳየ ሲሆን ለድርጅታቸው መሪ ያላቸው ክብርና መሪያቸው ደ/ር ሙሉዓለም እንዲሁ ለአባላት ያሳዩት የነበረው ክብርና ቀረቤታ ለሌላውም ቢሆን ሊዘነጋ የማይችል ለቆሙለት ድርጅት ሲባል ምን ያህል ለሰው ልጅ ክብር እንደሚገባውና የመተሳሰብ ስርዓት ከምንም በላይ ወሳኝ መሆኑን ለማስተማር ችለዋል።በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ታሳታፊ የነበሩ የስዊድን አርበኞች ግንቦት 7 አባላት በቦታው በመገኘት ለድርጅቱ ሊቀመንበር አርበኛ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ያደረጉት አቀባበል ከምንም በላይ ለአባላት ኩራት መሆኑ ሊዘነጋ የማይችል ሃቅ ነው ።
ከዚያም ባለፈ መድረኩን በፍፁም ጨዋነት ይመሩት ስለነበሩት ዶ / ር ሙሉዓለም ብዙ ማለት የሚቻል ነበር ይህም ከራሳቸው ልጆች / አባላት / ብዙ አድናቆት ያተረጉና እሳቸውም ለልጆቹ ያላቸውን ክብር ማየት ብቻ በቂ ነው ። በእንግድነት ቀርበው የነበሩትን ፕ/ ር ጌታቸው በጋሻው በጣም ትምህርት አዘል ንግግር ከመቼውም በላይ በሚመስጥ በለሰለሰ አንደበታቸው ታዳሚውን ግንዛቤ አስጨብጠውት ሲያልፉ እንዲሁም የጀግናው አንዳርጋቸው እህት ወ/ሮ ብዙነሽ ፅጌ ባልታሰበ ሁኔታ በቦታው መገኘት ታዳሚውን ሁሉ በደስታ እንዲፈነድቅ ያደረገ ሲሆን እሳቸው በአንዲ ስም አቅርበውት የነበረ ግጥም የአብዛኛውን ተሳታፊ ልብ የነካና ለቀጣዩ ትግል በበለጠ የሚያበረታታ ነበር። ሌላው በድርጅቱ ሊቀመንበር አርበኛ ፕ /ር ብርሃኑ ነጋ የቀረበውን ንግግር እና ከአባላት የሚጠየቁ ጥያቄዎች እና መልስ አባላትን ያስደሰተና ለቀጣዩ የትግል አቅጣጫችን ከምንግዜውም በላይ ስንቅ መሆኑና ትግሉ የደረሰበትን ሁኔታ በግልፅ ያሳየ ነበረ። ባጠቃላይ የዝግጅቱ መርሃ ግብር ለጨረታ በቀረበው ምስል በከፍተኛ ዋጋ 800,162 በወ/ሮ ብዙነሽ ፅጌ አሸናፊነት ተጠናቆ እሳቸው ግን ምስሉን ወንድማቸው አንዳርጋቸው ለሚወዱት ለኖርዌይ የአርበኞች ግንቦት 7 በስጦታ ሲያስረክቡ የኖርዌይ የአግ 7 ታጋዮች ደግሞ ረጅም ርቀት ተጉዘው ለዝግጅቱ ድምቀት ለሰጡት የስዊድን አርበኞች ወዳጅነትንና ፍቅርን በሚገልፅ አኳኃን አበርክተዋል ።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61777
ድል ከአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች!!!
Ethiofri@gnäll.com
ጁን 2016
No comments:
Post a Comment