Thursday, June 30, 2016

ሰበር ዜና... ህወሃት በሰሜኑ ግንባር ተጨናንቋል የም/መቶ አለቃ ደጀኔ እና ወታደር በኩር ይናገራሉ!



በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በምእራብ ትግራይ ሂሞራ በታች የማይካድራ ነዳጅ ማጠራቀሚያ አካባቢና እስከ ሰቲት ሁመራ እንዲሁም ጉናና ኡማህጂር ምስራቅ ትግራይና ዓዲ ግራት ድረስ የተሰማራዉ ከተለያዩ ክፍለ ጦሮችና ልዩ ሐይል እንዲሁም አካባቢ ሚሊሻዎች ተወጣቶ በስምሪት ላይ የሚገኘዉ የጸረ ሽብር ቡድን ወደ ግንባር እንዲሰማራ ባለመ መልኩ እየተበተነና እየተሰባጠረ እንደሚገኝ ታማኝ የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል። 
ይህዉ የጸረ ሽብር ቡድን በተለይም ከደረሰበትና እየደረሰበት ከሚገነዉ ድንገተኛ ጥቃት ምክንያት እጅግ በመመናመኑና በመዳከሙ ለስምሪት የአካባቢዉ ክፍለ/ጦሮች እንዲተኩ የተወሰኑ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በአካባቢዉ ላይ ከሚደረገዉ ወታደራዊ መሯሯጥ የተነሳ ስጋት ስላደረባቸዉ አካባቢያቸዉን ወደ መልቀቁ ደረጃ ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ እማኞች እየተናገሩ ይገኛሉ።
የህወሃት አዲስ ምልምልና ቅጥር ወታደሮች በመክዳት ምክንያት ከፍተኛ አደጋ እያስከተሉ በመምጣታቸዉ ወደ ደጀን ጦር የሚደረገዉ ዝዉዉር ከሰቲት ሁመራ ጀርባ ሲካተቱ ነባሮች በስምሪት እና ጸረ ሽብር ስምሪቱን እንደቆጣተሩ ሆኗል። 
በሰሜን ጎንደርና በምእራብ ይትግራይ አካባቢዉ ተሰማርተዉ የሚገኙት 24ተኛና ክ/ጦሮች ከ 25ተኛ ክ/ጦር ጋር ቅይጥ ብረት ለበስ ሜካናይዝድ በማደራጀት ይጥምር ዉህድ የሚመስል ስልታዊ ክንዉን እያደረጉ ሲሆን ለዚህ ያለመረጋጋትና የመበታተን ጦስ ዋነኛዉ ምክንያት በየእለቱ በሰራዊቱ ላይ የሚደርሱ አነስተኛ ጥቃቶች እና የዉስጥ አርበኞች የፈጠሩት ጫና በአንኳርነት ተጠቃሽ ከመሆኑ በተጨማሪ የኢትዮ ኤርትራ የጦርነት ስጋት የፈጠረዉ ትርምስ በራሱ የተያያዘ መጨናነቅ መፍጠሩን ባሳለፍነዉ ሳምንት ከሰሜኑ ግንባር ተነጥለዉ በጎረቤት ሐገር በተጠለሉ የም/መቶ አለቃ ደጀኔ ጥላሁን እና የወታደር በኩር ገ/ስላሴ ለታማኝ ምንጮቻችን ተናገረዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

No comments:

Post a Comment