Thursday, June 23, 2016

《 የሰላም ደጆች ሲዘጉ የአመጽ በሮች ይከፈታለሁ! 》ወጣት ሜሮን አለማየሁ

ሰማያዊ ፓርቲን በመቀላቀል ለዓመታት የገዥውን ፓርቲ በሰላማዊ መንገድ ስትታገል የቆየችው ወጣት ሜሮን አለማየሁ ፤ መንግስት በየጊዜው ሰላማዊ ታጋዮችን ወደ እስር ቤት እየወረወረና እየገደለ በሰላማዊ ትግል ሊቀየር እንደማይችል በተደጋጋሚ አሳይቶናል በሚል መንፈስ የትግል ስልቷን መቀየሯን እና ነፍጥ አንስታ ስርዓቱን ለመፋለም እንደተዘጋጀች ለአርበኞች ግንቦት 7 ራዲዮ ከሰጠችው ቃለ መጠይቅ ላይ ለመረዳት ተችሏል።

ወጣት ሜሮን ያለ አንዳች ጥፋት በተደጋጋሚ በበሬ ወለድ ክሶች ለእስር እንደተዳረገች እና በእስር በነበረችበት ዘጠኝ ወራቶች ውስጥ የህወሃት መርማሪዎች በሷና በሌሎች የህሊና ታሳሪዎች ላይ የፈፀሙትን አሰቃዊ ግፎች በቃለ መጠይቋ አስታውሳለች።
ወጣት ሜሮን በአሁኑ ሰዓት ኤርትራ የሚገኙትን የነጻነት ኃይሎች ተቀላቅላ ትገኛለች። አርበኛ ታጋይ ሜሮን በአገሬ ላይ የተጫነውን አምባገነናዊ ስርዓት ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ነፍሴን ልሰጥ በረሃ ገብቻለሁ ስትል ተደምጣለች።
በመጨረሻም ወጣቷ ባስተላለፈችው መልእክት “ሁላችንም እራሳችንን ነፃ ማውጣት አለብን። በብዛት ሲታይ የተወሰነ ሰው መስእዋት ከፍሎ ሌላው ተደስቶ መኖር ነው የሚፈልገው ፤ ነገር ግን ሁላችንም መታገል ብንችል ከዚህ አንባገነን ስርአት ነፃ መውጣት እንደምንችል እንዲረዱልኝ እፈልጋለሁ።” ብላለች።
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ

No comments:

Post a Comment