Monday, June 6, 2016

ሰበር ዜና... በደቡብ ሱዳን የወያኔ ሻለቃ እርምጃ ተወሰደበት.



ከወያኔ የግፍ አገዛዝ እራሳቸዉን በማግለል በምእራብ ደቡብ ሱዳን እና በጁባ አካባቢ መሽገዉ የነበሩ ብዛት ያላቸዉ የትግራይ ነጻ አዉጪ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን በማፈላለግ ላይ የተሰማራዉ በተለይም ከጋምቤላ ተጠልፈዉ የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን ህጻናትን ለማፈላለግ በሚል ሽፋን ለበቀል ሲንቀዠቀዥ የነበረ አነስተኛ መጠን ያለዉ የወያኔ ቡድን መሪና አዝዥ በሻለቅነት ማእረግ ላይ የሚገኝ ከፍተኛ መኮንን በዚያዉ በደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያ አዋሳኝ ጠረፍ አኮቦ ( Akobo ) አካባቢ ማንነታቸዉ ባልታወቀ ታጣቂዎች እርምጃ እንደተወሰደበት ምንጮች አሳዉቀዋል።
በደቡብ ሱዳን ብዛት ያላቸዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የወያኔን ስርአት በመክዳት በዚያ እንደሚኖሩ የገለጸዉ ምንጫችን አያይዞ አብዛኞቹ ለደህንነታቸዉ በመስጋት ምክንያት ሐገር ለመቀየር ተገደዋል።
እነዚህ የከዱ አባላቶች በዋነኛነት ካልቸዉ የዉትድርና ብቃት እና እረጅም ልምድ እንዲሁም ከተሸከሙት መረጃዎች አንጻር የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን ወያኔ ላይ የፈጠሩት ጭንቀት እንዳለ ሆኖ አባላቱ በኤርትራ የሚገኙ ተቃዋሚዎችን የመቀላቀላቸዉ ስጋት በአጠቃላይ የወያኔን የመከላከያ አዝዦች ሰላም የነሳቸዉ መሆኑን ምንጫችን ሲገልጹ አያይዘዉ የከዱ አባልቶችም ያንን ከማድረግ ወደኍላ እንደማይሉ አሳዉቀዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!
( ጉድሽ ወያኔ )

No comments:

Post a Comment