Tuesday, June 28, 2016

በሶማሊያ ሕይወቱን እየገበረ የሚገኘው ሰራዊት ላለፉት 6 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈለው ታወቀ

27210718553_d292423c53_zአልሸባብን ለመወጋት በሱማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ሕብረት ከ20 የማያንስ ሰራዊት ላለፉት 6 ወራት ምንም ዓይነት ደመወዝ እንዳልተከፈለው ቢቢሲ አጋለጠ::
አልሸባብን ለመዋጋት በሶማሊያ የሚገኘው ይኸው የኢትዮጵያን ጨምሮ የሌሎች አፍሪካ ሃገራትን ሰራዊት የያዘው እዚያው የሚገኘው የአፍሪካ ሕብረት ጦር በገንዘብ የሚደጎመው በአውሮፓ ህብረት የነበረ ቢሆንም የአውሮፓ ሕብረት ላለፉት 6 ወራት ገንዘብ እንዳልላከ ቢቢሲ ዘግቧል::
እንደ ቢቢሲ ዘገባ የአውሮፓ ሕብረት ለ እያንዳንዱ ሰራዊት በወር $1,028 ለመክፈል የተሰማማ ቢሆንም ወታደሮቹን ወደዚያው የሚልኩት ሃገራት $200 እንደሚቆርጡና ከሌሎች ክፍያዎች ተቆራርጦ ለወታደሮቹ $800 ዶላር ይደርሳቸዋል::
የአውሮፓ ሕበርት ገንዘቡን ላለፉት 6 ወራት ያልላከው በበሒሳብ ምክንያት ነው የሚል ድፍን ያለ ምላሽ ይሰጥ እንጂ በምን ዓይነት ሒሳብ ችግሩ እንደተፈጠረ የተባለ ነገር የለም::
ላለፉት 12 ወራት በአሚሶም ስር ያሉት የብሩንዲ; የዩጋንዳ; የኬንያና የኢቱኦጵያ ወታደሮች በአልሸባብ ጥቃት ሲደርስባቸው ቆይቷል::
ጁን 9 አልሸባብ 60 የኢትዮጵያ ወታደሮችን በሃልጋን መገደሉን; እንዲሁም ኤፕሪል 21 6 ወታደሮችን በቤይ አካባቢ መግደሉን መግለጹ ይታወቃል::

በተጨማሪም ፌብሩዋሪ 15 በሸበሌ አካባቢ 15 የኢትዮጵያ ወታደሮች በአልሸባብ መገደላቸው ተዘግቧል::
ይህንን ሁሉ የሕይወት መሰዋዕትነት የሚከፍልን ሃይል በሂሳብ ስህተት ደመወዝ ለ6 ወር መከልከልን ምን ይሉታል?27210718553_d292423c53_z

No comments:

Post a Comment