Tuesday, June 14, 2016

ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ሕወሃት) ሰኔ 7 ቀን 2008 በጾረና ግምባር ወደ ኤርትራ ግዛት ተንቀሳቅሶ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ባወጣው አጭር መግለጫ “የሕወሃት አገዛዝ በፆረና ማዕከላዊ ግንባር ጦርነት ከፍቶብናል” ነበር ያለው።


የኤርትራ መንግስት “ኢትዮጵያ ጥቃት ፈጸመችብኝ” አለማለቱ ኤርትራውያን የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘረኛና አምባገነን አፋኝ ሥርዓት ስር ደፍጥጦ እየገዛ ያለው በሕዝብ ያልተመረጠና ከአንድ አነስተኛ የህዝብ ብዛት ካለው ብሄር የወጣ እራሱን የብሄረሰቡ ነጻ አውጪ እያለ የሚጠራ አናሳ ቡድን ሕወሃት እንደሆነ በሚገባ ስለሚያውቅ ነው።
ለወትሮው ኢትዮጵያን በመግዛት ልይ ያለውን ዘረኛና ጨቋኝ ቡድን “ሕወሃት” በሚለው ትክክለኛ መጠሪያው አዘውትረው የሚጠሩት ከሕወሃት የአፈና አገዛዝ ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን፣ የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች፣ የመብት ተሟጋቾች እና አንዳንድ በሃገር ቤት የሚገኙ ኮፍጣና የተቃዋሚ አባላት ብቻ ነበሩ። ይሁንና አለማቀፍ የዜና አውታሮች በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበሮች ጦርነት ተቀሰቀሰ መባሉን ሰምተው ጆሮዋቸውን አቅንተው በሚጠብቁበት ወቅት የኤርትራው ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር “የሕወሃት አገዛዝ በፆረና ማዕከላዊ ግንባር ጦርነት ከፍቶብናል” የሚል ቋንቋ በመጠቀሙ ምዕራባውያኑ የዜና አውታሮች ምናልባትም ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያውን አገዛዝ በትክክለኛ ስሙ “ሕወሃት” ሊጠሩት ተገደዋል።
ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ሕወሃት) እራሱን “ኢሕአዴግ” በሚባለው ጭንብል ስር ቀብሮ ለዓመታት ኖርዋል። እርግጥ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ “ኢሕአዴግ” በሚባለው ድርጅት ስር አለን የሚሉትን ድርጅቶች “ጥርስ የሌላቸው አንበሶች” እንደሆኑ ጠንቅቆ ያውቃል። የድርጅቶቹ ዋነኛ ተግባርም እንወክለዋለን የሚሉትን ብሄረሰብ/ሕዝብ እጅና እግር አስረው ለሕወሃት እንዲገዛ ማድረግ ነው።

ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበሮች ጦርነት የመቀስቀሱን ዜና ከሰሙ በኋላ በማህበራዊ ድረገጾች እያንጸባረቁ ያሉት መልእክትም ይህንኑ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ከተጫነበት ዘረኛና አምባገነን የጭቆና አገዛዝ እራሱን አላቆ ነጻ ለመውጣት የሚያደርገውን የነጻነት ትግል አቅጣጫ ለማሳትና የሕወሃትን አገዛዝ ለማስቀጠል ታስቦ ከኤርትራ ጋር የሚደረግ ጦርነት የኢትዮጵያን ሕዝብ አይመለከትም!

No comments:

Post a Comment