Saturday, June 11, 2016

ሰበር ዜና: አክሱም ስታዲየም ፌደራል ፖሊሶች ተፈነከቱ – ሕዝቡ በድንጋይ ተከታከተ (ፎቶዎች ይዘናል)

 axum tigraiበትግራይ አክሱም ስታዲየም ውስጥ በተደረገ የ እግር ኳስ ጨዋታ ደጋፊዎች ባነሱት ሁከት ፖሊሶችና በርካታ የስፖርት ደጋፊዎች ተፈነከቱ::
በአክሱም ስታዲየም የአክሱም ከተማ እና የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ እየደረገ ባለበት ወቅት ደጋፊዎች ባነሱት ሁከት የተነሳ በርካታ ሰዎች ሲቆስሉ ስታዲየሙ ሄልሜት ባጠለቁ ልዩ ኃይሎች መከበቡ ታውቋል::
በኢትዮጵያ ከፍተኛው ሊግ የሚጫወቱት ሁለቱ የትግራይ ክልል ክለቦች ደጋፊዎች ያነሱት ሁከት ላይ ተጫዋቾች ሳይቀሩ መፈንከታቸውና ደጋፊዎች በድንጋይ ሲከታከቱ እንደቆዩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::
ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም የቡና ደጋፊዎች ባነሱት ብጥብጥ ስታዲየሙ ላይ እና በሰዎች ላይ ጉዳት ከመድረሱም በላይ አንድ ሰው መሞቱን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋምaksum Tig::aksum Tigrai 1

No comments:

Post a Comment