Tuesday, June 14, 2016

በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ግጭት ሁለቱም አገራት እርስ በእርስ ተወነጃጀሉ ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2008)



በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ግጭት መከሰቱን ሁለቱም መንግስታት አስታወቁ። እሁድ ሰኔ 5 ቀን 20008 ዓም በፆረና ግንባር ተከሰተ በተባለ ግጭት ሁለቱም መንግስታት ዕርስ በዕርስ የተወነጃጀሉ ሲሆን፣ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን በሁለቱም ወገን ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ግጭት መከሰቱን የዘገቡት ለገዢው ፓርቲ ቅርበት ያላቸው ድረገጾች ሲሆን፣ ኤርትራ መጠነ ሰፊ ጥቃት ተሰንዝሮባታል ብለዋል፣ ውጊያው በፆረና እና ዛላምበሳ ግንባር እንደሆነም አመልክተዋል። ለገዢው ፓርቲ ቅርበት ያላቸው ሚዲያዎች የጦርነቱን ዜና በሚዘገቡበት ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ዝምታን መርጦ ቆይቷል።
የኤርትራ መንግስት በይፋ ዕሁድ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ በፆረና ግንባር ጥቃት እንደተሰነዘረበት ገልጿል። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር “ወያኔ የመንግስት ጥቃት ሰነዘረ” በሚል ርዕስ ባወጣው አጭር መግለጫ በፆረና ማዕከላዊ ግንባር ጥቃት እንደተሰነዘረበት ገልጿል።
“የኤርትራ መንግስት በፆረና ግንባት ጥቃት ለመሰንዘር በመሞከሩ የአጸፋ ርምጃ ተወስዷል።” በምል ርዕስ ባወጣው መገለጫ፣ ከኤርትራ መንግስት ጋር ውጊያ መድረጉን አረጋግግጧል። በመግለጫው ስለጉዳቱ መጠን የተገለጸ ነገር ባይኖርም አቶ ጌታቸው ረዳ በሁለቱ ወገን ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጎዳዮች ፅቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸው ረዳ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት መግለጫ ግጭት እንደነበር አረጋግጠው፣ በሁለቱም ውገን ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን በኤርትራ ወገን ደግሞ የበረታ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ሰኞ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ግጭት መብረዱን አረጋግጧል።

No comments:

Post a Comment