Tuesday, June 21, 2016

ከቤንሻጉል ጉምዝ … ክልል በደቡብ ሱዳን ወታደሮች ታግተው የሚወሰዱት ዜጎቻችን ቁጥቸው እየጨመረ በመሄድ ላይ እንዳለ ታወቀ።


ባገኘነው መረጃ መሰረት ፣በቤንሻጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን ጉባ አሜድላ በተባለ ወረዳ ደቡብ ሱዳንን ከሚያዋስን ቀበሌ በሱዳን ወታደሮች እየታገቱ የሚወሰዱት ወገኖቻችን ቁጥር እየጨመረ እየሄደ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።
በአካባቢው በእርሻ ስራ ላይ የተሰማሩ በርከት ያሉ ወገኖቻችን ።ሲናር በተባለ ግዛት ከደቡብ ሱዳን በመጡ ወታደሮች በባለፈው ሳምንት 9 ሰዎች ታግተው እንደተወሰዱ ከገለጹ በኋላ፥የክልሉ መንግስት ይሁን የፌዴራል መንግስት ለማስመለሰ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት የተደረገ ጥረት እንደሌለ ተገልጿል ።
ባለፈው ሚያዚያ ወር ውስጥ 24 ወገኖቻችን ከቤንሻጉል ጉምዝ ክልል ታግተው እንደተወሰዱ የገለጸው መረጃው ፥እነዚህን ለማስመለሰ ከንግግር ያለፈ ሌላ የተሰራ ስራ እንደሌለና እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በሁለቱ አገሮች መካከል የድንበር ውዝግብ እየከረረ በመሄድ ላይ በመሆኑ ታግተው ለተወሰዱት ወገኖቻችን ለህይወታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ እንዳሉ የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስታውቋል።

No comments:

Post a Comment