Monday, June 6, 2016

ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባና የገቢ ማሰባሰቢ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ተካሄደ!!


ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ከኖርዲክ አገራት የገቢ ማሰባብሰቢያ ህዝባዊ ስብሰባና የውይይት ፕሮግራም በጋራ አዘጋጅነት እ ኤ አ ጁን 4, 2016 በኦስሎ ኖርዌይ የተዘጋጀው ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በተጨማሪ የገንዘብ ማሰባሰብያ ዝግጅት በአርበኞች ግንቦት 7 በፕሮፈሰር ብርሀኑ ነጋ በአይነቱ ለየት ያለ ከፍተኛ የሆነውን የገንዘብ ማሰባሰብና የ አንድነት መንፈስ የተላበሰበት ታሪካዊ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ።
በዝግጅቱ መክፈቻ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ ዳንኤል አበበ የመክፈቻ ንግግር ፕሮግራሙን እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኃላ መድረኩን ለዶ/ር ሙሉ አለም አዳም ፕሮግራሙን አስጀምረውታል።
በዝግጅቱም ላይ በእንግድነት ከተጋበዙት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሀኑ ነጋ ከኤርትራ በረሃ፣ ፕሮፈሰር ጌታቸው በጋሻው በተጨማሪም የኢሳት ጋዜጠኞች ገሊላ መኮንን አምስተርዳም እና መታሰቢያ ቀፀላ ለንደን እንግድነት ተገኝተዋል። በዚህም ዝግጅት ፕሮፈሰር ጌታቸው ስለ ኢትዮጵያ ያለውን የኢኮኖሚ ትንተና በሰፊው ገልፀዋል።
ፕሮግራሙን በሰፊው ሲጠበቅ የነበረው የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሀኑ ንግግር በመቀጠል በአገሩቱ ውስጥ እየተደረገ ያለውን ትግል ሰፊ እና ጥልቅ ማብራሪያ አቅርበው በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በተለያዮ አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኞች አስከፊው ስደትና መከራ በወያኔ መንግስት በመሸሽ እያደረሰባቸው ባለው ስቃይ ለዚ አስከፊ ስደት የዳረጉን የወያኔን የግፍ አገዛዝ ጫፍ መድረሱንም ጭምር ያሳየ ምልክት ነው በድርጊታቸውም በቃ ልንላቸው ይገባል ትግሉን መደገፍ ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል።

በቀጣዮም ፕሮግራም ታዳሚው ያልተጠበቀው ለተሳታፊውም በዓነቱ እንግዳ የሆነ ነገር በመከሰቱ ህዝቡን ያስደሰተ ክስተት ተከሰተ። በዝግጅቱም ላይ ከተሳታፊዎች ፊታቸውን በከፊል በመሸፈን ዝግጅቱን ሲከታትርሉ የነበሩት ግለሰብ ማንነታቸው በመድረክ ላይ በመወጣት ተሳታፊ ያስደመመ ያስደተና የአንድነት መንፈስን የበለጠ ያጠናከረ ክስተት በአንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙነሽ ፅጌ ያልተጠበቁ እንግዳ ሆነው ተገኝተዋል ። ወ/ሮ ብዙነሽ ።።።።። የሚባል ግጥም በማቅረብ ተሳታፊው በእንባ ፥ በቁጭት ስሜት ያንገበበ መልዕክት ያለው ግጥም አስተልፈዋል። የተወሰን ደቂቃ የምሳና ሻይ እረፍት በማድረግ በቀጥታ ወደ ልዩ ታሪካዊ የጨረታ ዝግጅት ነበር የታለፈው በጨረታውና የገቢ ማሰባሰቢያ የቀረበው ፎቶ የታጋይ አርበኛ ፕሮፈሰር ብርሀኑ ነጋ ፣ አርበኛ ታጋይ መዓዛ ፅጌ እና አንዳርጋቸው ፅጌ በ አንድ ላይ ያጠቃለለ ነበር። ለጨረታው ቀርቦ የነበረው ከፍተኛ ዋጋ በ ወ/ሮ ብዙ አየሁ ፅጌ አሸንፈዋል። በጨረታውም ያሸነፉትን የሶስቱ ታጋይ አርበኞች ፎቶ መልሰው ለአዘጋጁ አስረክበዋል አዘጋጁም ከረጅም ርቀት ተጉዘው ከስዊድን አገር ለመጡ አገር ወዳድ አርበኞች አስረክበዋል። በፕሮግራሙ ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢትዮጵያዊነት ነግሶ የታየበት ነበር ። በቀሪ ልዩ ዕጣ የወጣላቸው በልዮ ስሙ ኦታ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የትግሉ አጋር በዕጣው የወጣላቸውን የኮምፒተር ዕጣ ለ አርበኞች ግንቦት 7 አባልት እና ደጋፊ ለትግሉ ይጠቅማል በማለት በስጦታ መልክ ለግሰዋል። ሌላም ሌላም ስጦታዎች የተካተቱበት እና ለትግል ሜዳ ለተሰማሩት አጋር ጋዶች የሚሆን በ አንድ ግለሰብ 1000 ቲሸርት በስጦታ ተለግሰዋል። በማጠቃለያውም በ ኖርዌዳን ክሮነር 800,162 /ስምንት መቶ ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ሁለት ሳንትም/ ተሰብስቦዋል ። የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በተካሄደው የአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰቢያ በደመቀ ሁኔታ እንዲሳካ ላደረጋችሁ የነጻነት ታጋዮች ሁሉ ድርጅቱ የተሰማውን ትልቅ አድናቆት በምስጋና ሲገልጽ በተለይ ከስዊድን እንዲሁም ከሰሜንና ከተለያየ የአውሮፓ ክፍል የመጣችሁ፣ ከበርገን፣ ከትሮንድሃየም፣ ከክርስትያንሳንድ፣ ስታቫንገር እንዲሁም ከተለያየ የኖርዌይ ቦታ የመጣችሁ፣ በማያያዝም የከረንት አፌር ፓል ቶክ ሩም እንዲሁም ኢካዴፍ ከፍተኛ አድናቆት እና ምስጋና ስናቀርብ በማያያዝ የፍጻሜ የትግሉ ለሚጠይቀው መስዋእትነት ከአፍ ባለፈ በተግባር ስላሳያችሁት አጋርነት የነጻነት ታጋዮች ሁሉ ድርጅቱ የአክብሮት ምስጋናውን ያቀርባል፣ በተለይ የዘረኛው የጥጵልፍ አቃጣሪ ቡችሎች ፕሮጋራማችንን ለማስተጓጎን ያደረጉትን ያልተሳካ ሙከራ ከነሱ ውስጥ በመሆን እንቅስቃሴያቸውም ስታቀብሉን ለነበር የውስጥ አርበኞች ከፍተኛ አድናቆት እና ምስጋና እናቀርባለን፣ 
በስተመጨረሻ ከአገር ቤት በመደወል የገንዘብ ድጋፍ ላደረጋችሁንም ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን!!
ኢትዮጵያችን በክብር ለዘላለም ትኖራለች

ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

No comments:

Post a Comment