Monday, October 3, 2016

Abebe Gellaw


ብሄራዊ ሃዘን ወደ ብሄራዊ ትግል መቀየር ይገባዋል። በአገር ቤትም ይሁን በውጭ የምንገኝ አክቲቪስቶች እና የለውጥ አራማጆች በሙሉ ልዩነቶቻችንን አቻችለን ህዝባችንን ከዳር እስከዳር ለትግል ለማነሳሳትና ለማስተባበር ታጥቀን እንነሳ። ከዚህ በሁዋላ በጋራ ማዘን እና ማልቀስ ትተን በጋራ እንታገል። 
ይህ አንድ ሃሙስ የቀረው የነቀዘ ወንጀለኛ፣ ዘረኛና ፋሺስታዊ የወያኔ ስርአት በማያዳግም ሁኔታ የሚወድቀው ሁሉም ለጋራ የነጻነት ራእይ በጋራ ሲታገል ብቻ እንደሆነ አጠያያቂ አይደለም። ህዝብ አጎንብሶ ካልተገዛ ማንም አይፈናጠጠውም፣ ማንም አይገድለውም፣ ማንም አይዘርፈውም። 
በቃ! ዛቻ ሳይሆን ተግባር መሆን ይገባዋል.....የውጭ ሃይሎችን መማጸን ትተን እኛው ለየብቻ የጀመርነውን እኛው በጋራ እንጨርስው! ስርነቀል ለውጥ የጋራ ተግባር ውጤት ነው.... እንወያይ፣ እንመካከር፣ የጋራ መፍትሄና የትግል ስትራቴጂ እንንደፍ ። 
ገፍተን ገፍተን ገደል አፋፍ ላይ አድርሰናቸዋል። ሳንከፋፈል በጋራ ከተነሳን፣ በጋራ እንጥላቸዋለን...አትጠራጠሩ!

No comments:

Post a Comment