Ethio freedom Voice
Thursday, June 2, 2016
ሰበር መረጃ'''
የፈተናዎች ኤጀንሲና ትምህርት ሚኒስቴሩ ሽፈራዉ ሽጉጤ ሌላዉ ስህተት!
በሽፈራዉ ሽጉጤ የሚመራዉ የትምህርት ሚኒስቴር ሌላኛዉን ታሪካዊ ስህተት ለመስራት ተዘጋጅቷል ይህ ሀገሪቷን የማትወጣበት አዘቅት ዉስጥ ሊከት የሚችል ስህተት በነሽፈራዉ ሽጉጤ መጽደቁን የሚያረጋግጡ መረጃዎች እየደረሱን ሲሆን ይህዉም ባጠቃላይ የ12ተኝ ክፍልን ማጠናቀቂያ ፈተናዎች መሰወራቸዉን የሚያረጋጥ ነዉ።
የፈተናዎች ኤጀንሲና ትምህርት ሚኒስተር በበኩሉ የፈተናዎቹ ጥያቄዎች እንደማይቀየሩና ነገር ግን እንደሚዘበራረቁ ማለትም ከቡክሌት እና ምርጫ ኮድ ብሎም ከበፊቱ የጥያቄ ቁጥር መለያየት ሂደት ብቻ እንደሚደረግ ምንጮች ጠቁመዋል።
ከታማኝ መረጃዎች ለመረዳት እንደተቻለዉ ሁሉም ኮድ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናወች ተሰርቀዋል!!
በተያያዘ ዜናም ከፈተናወች ኤጀንሲና ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኙ መረጃወች እንደሚጠቁሙት በሽፈራዉ ሽጉጤ የሚመራዉ ሚኒስቴር ፈተናዉን ከቡክሌት እና ምርጫ ኮድ ብሎም ከበፊቱ የጥያቄ ቁጥር መለያየት ካልሆነ በስተቀር ከዚህ በፊት የወጣዉ ጥያቄ እንደማይቀየር ለማረጋገጥ ተችሏል::
ይህም ማለት በምንም አይነት መንገድ የፈተናዉ መልስ የደረሰዉ ተማሪ ዉጤቱን ከፍ የሚያደርገዉ ወይም ማትሪክን በቀላሉ ለማለፍ እድሉ ሲኖረዉ! በአንጻሩ ፈተናዉ ያልደረሰዉ ጎበዝም ሆነ ሰነፍ ተማሪ በተለይም የፈተናዉን መልስ አግኝተዋል ተብሎ የተገመቱትን ከኦሮሚያ ክልል ወጭ የሚገኙ ተማሪወች ባጠቃላይ ዉጤት አምጥተዉ ወደ ዩኒቨርሲቲ አይገቡም! ወይም ማትሪክን ተፈትነዉ ዉጤት የማምጣታቸዉ ኡደት ዝቅተኛ ነዉ ማለት ነዉ።
የትግራዩ ነጻ አዉጭ ቡድን ትምህርት ሚኒስቴር እንደሚለዉ ከሆነ የዩኒቨርሲቲ መግቢያዉን ዉጤት ዝቅ አደርጋለዉ ቢልም፡ በዚህ የፈተና ዉጤትና ፈተናዉ እራሱ በተሰረቀበት ሁኔታ ላይ በተደራቢ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ዉጤትን ዝቅ ከማድረግ ጋር በተያያዘ የሚያልፉትን ተማሪዎች ግምት ዉስጥ ስናስገባቸዉ በሐገሪቷ ላይ ያሉት ዩኒቨርሲቲወች ዉጤት አምጥቶ ብቁ የሚሆኑትን የተማሪዎች ብዛት ለማስተናገድ አይችሉም::
በመሆኑም ፈተናዉ ወይም መልሱ ያልደረሰዉ አካባቢ የሚገኙ ሐገር ተረካቢ ወጣት ተማሪዎች ሁሉ ተቃዉሞዋቸዉን በማሰማት ኢፍትሐዊ የሆነዉን ይህን አሰራር እንዲቃወሙ ግድ ይላል!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
( ጉድሽ ወያኔ )
No comments:
Post a Comment
Newer Post
Older Post
Home
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment