Monday, October 3, 2016

ኢሳት አምስተርዳም የዕለቱ ዜና ከሟቾቹ መካከል በቪዲዮው ከእናቷ ጋር ቆማ የምትታዬው ወጣት ሰላም አንዷ ናት። ወጣት ሰላም ለቤተሰቦቿ አንድ ልጅ ስትሆን በትምህርቷ በጣም ጎበዝና ለወደፊት ተስፋ የተጣለባት ተማሪ እንደነበረች ጓደኞቿ ተናግረዋል። የሰላም እህት ዲና አለማዬሁ ፦“ምን ልበል? ምን ላድርግ እህቴ!? ተቃጠልኩልሽ! ተንገበገብኩልሽ እህቴ!! ገና ነበር እኮ ጊዤሽ! እንዴት ልሁን?! ምን ልሁን ሰላምዬ?!! ኢሀዲግ እህቴን ቀማኝ !!!”በማለት ሀዘኗን በለቅሱ ገልጣለች። ሌላዋ ሟች ደግሞ ገና ካገባች መንፈቅ ያልሞላት አዲሷ ሙሽራ ሲፈን ለገሰ ናት። የሲፈን ወንድም ሲናገር፦“ካገባች እንኳን ስድስት ወር ያልሞላት እህቴ ሲፈን ለገሰ ዛሬ ከጎኔ ተለየች። በቢሾፍቱ ሌሎች የቀመሱትን የሞት ፅዋ እሷም ተጋራች:: ሃዘኔ መራር ነው፤ ሲፎ ፈጣሪ ነፍስሽን በገነት ያኑረው ከማለት ውጪ ምንም የምናገርበትም አንደበት የለኝም”ብሏል። ብዙዎችን እጅግ ያሳዘነው ነገር በቪዲዮው ከጎኗ ቆሞ የሚታየው የሟቿ ሙሽራ የሲፈን ወንድም በአጋዚዎች ጥይት የተገደለው ገና የዛሬ ሁለት ወር መሆኑ ነው። ሌላው በኢሬቻ በዓል ህይወታቸውን ካጡት መካከል የጅማ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ የሆነውና በሥራ ላይ የተሰማራው ኢንጂኒዬር ደረጀ ቡልቶ ይገኝበታል...... ሌሎችም በርካታ ወጣቶች በአል ለማክበር ከቤታቸው እንደወጡ ጥይት መቷቸውና አፈር ተጭኗቸው ሳይመለሱ ቀርተዋል።ቤተሰብ ከዛሬ ነገ ደረሱልኝ እያለ በሙሉ አይን የማያያቸው አያሌ እንቡጥ አበባዎች ረግፈዋል። ጥቂት የማይባሉ የወደፊት የሀገር ተስፋዎች እንደ ዘበት ተቀጭተዋል። -28:32ESAT Daily News Amsterdam October 03, 2016

No comments:

Post a Comment