በቅርቡ 29/9/2016 ከደብረ ዘይት የተነሱ 3 የጦር ጀቶች በአዳማ በኩል በማድረግ ለ33 ደቂቃዎች መሰወራቸዉንና ጉዳዩ በከፍተኛ ሚስጥር እንዲያዝ መረጃ አቀብዬህ እንደነበረ ታስታዉሳለህ።
በመሆኑም ትናንት በሰጠሁህ ፍንጭ መሰረት ሁለት የበረራ ክፍል ሰራተኞች መረጃ ያወጣሉ ተብለው ተወስደዋል፤ እኔም ይህንን የማቀብልህ በፍጹም ድፍረት ነዉ፤
አብራሪዎቹ ከደብረ ዘይት የአየር ሐይል ጣቢያ በመነሳት የእሬቻ በአል በሚከበርበት የቢሾፍቱ አካባቢ ዝቅ ብለዉ በመብረርር የሙከራ ግዜ እንዲወስዱ መመሪያ እንደተላለፈላቸዉ ለማወቅ ችያለዉ፡ አብራሪዎቹ በመመሪያዉ መሰርት ዝግጅት ላይ እንዳሉ የመርዝ ጭስ ( የአድማ መበተኛ በሚል ) ሽፋን ለአስፈላጊ ጥንቃቄ መጠቀም ሊቻል ስለሚችል አዲስ የሆኑ ማስወንጨፊያዎችን እንዲለማመዱ እንዲሁም በጣም ዝቅ ብለዉ ለመብረር አካባቢዉ ላይ የልምምድ አጭር ቅኝት እንዲወስዱ ትእዛዝ ወጣ በዚህ ሁኔታ ላይ 3ቱም አብራሪዎች በአንድ ሐሳብ ተስማምተዉ ልምምዱን ጀመሩ!
ነገር ግን በበረራ ወቅት ላይ ለ33 ደቂቃ ድምጽእቸዉን አጥፍተዋል የተባሉት አብራሪዎች ከአየር ሐይሉ ከፍተኛ አመራር ጋር ድርድር በማድረግ በዚህ አደገኛ በሆነ ግዳጅ ላይ መሳተፍ እንደማይፈልጉ ግዳጁ አደገኛ መሆኑንና ህዝብ ላይ ይህንን ተግባር እንደማይፈጽሙ ቢናገሩም የአየር ሐይሉ አመራሮች ከወያኔ ሰዎች በተላለፈዉ ትእዛዝ መሰረት አመጽ ካልተነሳ በስተቀር አፋኝ የሆነዉን ጭስ እንደማይጠቀሙ ይነግሩዋቸዋልነገር ግን አብራሪዎቹ የጦር ጀቶቹ በእንደዚህ ያለ ባሕላዊ ክብረት ላይ ዝቅ ብለዉ መብረራቸዉ በራሱ ከፍተኛ ወንጀል ነዉ፡በፍጹም አናደርገዉም ይህን የማትቀበሉን ከሆነ ጀቶቹን የራስችን ወሳኔ እንፈጽምባቸዋለን በማለት አሻፈርኝ ይላሉ!
ነገሩ አጣብቂኝ ዉስጥ የከተታቸዉ የአየር ሐይሉ አመራሮች አብራሪዎቹ በሰጡት ዋስትና መሰረት በመደራደር ተስማምተዉ ወደ ምድር ኢንዲወርዱ ተደርገዋል!
ዉድ ወዳጄ ይህንን ግዳጅ ሊወጣ የሚችል የአየር ሐይል አብራሪ ይኖራል የሚል እምነት የተመናመምነባቸዉ ጨካኞች የማስበርገግና የማሳደድ የመርዝ ጭስ የመጠቀሙን እንዲሁም በመትረየሶች የማጥቃትን የጦር ወንጀል ግዳጅ ወደ የጦር ሄሊኮፍተሮች እና ታንኮች በማዞር ከየት እንደመጡ በምይታወቁ ፊታቸዉን በሸፈኑ ግለሰቦች አየር ሐይል ዉስጥ ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተዉ የግድያ እርምጃዉን በእሬቻ በል ላይ ወስደዋል፤
ይህንን መልእክት ለመላዉ ኢትዮጵያዊ አድርስልኝ ከእንግዲህ አንገናኝም፤
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
( ጉድሽ ወያኔ )
ሰበር ዜና.......
የህወሃት የጦር ጀቶች ለ33 ደቂቃ የገቡበት ጠፉ!!
በትናንትናዉ እለት 29/9/2016 ከደብረ ዘይት አካባቢ በመነሳት በአዳማ በኩል የተወንጨፉ የወያኔ አየር ሐይል 3 ጀቶች ለ33 ደቂቃ የገቡበት ጠፍተው የህወሃቱ አየር ሐይል በጭንቅ መዋሉን ከአየር ሐይል አካባቢ የደረሰን መረጃ ጠቆመ!
በግንኙነት መቋረት የሚል አናሳ እና የማያጠግብ ምክንያት የተሰጠዉ የአየር ሐይሉ ክትትል ቡድን ምርመራ እያደረገ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ላይ ጀቶቹን ያበሩ የነበሩ አብራሪዎች ከመመሪያ ዉጭ አንዳች የሙከራ ስራ ሳይሰሩ እንዳልቀረ እየተነገረ ይገኛል።
መረጃዉ በፍንጭ ደረጃ ከደረሰን ወዲህ ለማጣራት በሞከርነዉ መሰረት አብራሪዎቹ ላይ ጫና ላለማድረግና ሌሎችንም አብራሪዎች ላለማነቃቃት በሚል የጭንቅ ቋጠሮ ነገሩን በዉስጥ ለማፈን ተገደዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )
No comments:
Post a Comment