Tuesday, February 28, 2017
ሰሞኑን ከአንዲት የልብ ወዳጄ ጋር ስለ ውስብስቡ የኢትዮጵያ ፖለቲካና - የኢትዮጵያዊ ሕይወት በረጅሙ አወጋን። የወዳጄን ስም አልነግራችሁም። ለጊዜው አያስፈልግም ብላለች። እናላችሁ፦ በወጋችን መካከል - ቆም ብዬ እንዳስብ የሚያደርግ አንድ ጥያቄ ወርወር አደረገች። ጥያቄው ምን መሰላችሁ? “ኢትዮጵያውያንን በጋራ - “አሁን ገና በዐይኔ መጣህ” የሚያስብላቸው እሴት የትኛው ነው?” የሚል ነበር። ትንሽ እንደማሰብ አልኹና፦ “በሉዓላዊነታቸው ላይ ያላቸው . . . ” ብዬ ሐሳቤን ሳልቋጭ . . . . “ምንም እንኳ የTerritorial Integrity ጉዳይ ተስፋ የማይቆረጥበት ጉዳይ ቢኾንም” ብላ - በግራ መጋባት ዝምታ - በስልኩ ውስጥ ለሰከንድ ያህል ጠፋች። ወዲያው፦ “ለመናገር የተሻለ መረጃና ዕድል ያላቸው ሰዎች - ኢትዮጵያ በታሪኳ እስካሁንም ድረስ ባልታደለችው “ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ማድረግ ጉዳይ ላይ” ማተኮር አለባቸው” አለችኝ። ለወዳጄ ከምንም በላይ ያሳሰባት ነገር፤ እናውቅልኻለን የምንለው - የተሻለ ዕድልና መረጃ ያለን ሰዎች - መሬት ላይ ያለው ወጣትና አጠቃላዩ ማኅበረሰብ - ከእኛ ትንታኔ በተለየ የራሱን ዕይታና እውነታ በሚገለጽበትና - በሚረዳበት የመነጽር ስፋትና መጠን - ሐቁ ወደ ፖለቲካ ማዕከሉ እንዲመጣ ማድረግ አለመቻላችን ነው። MaMa - ማማ - በማስረሻ ማሞ ESAT Mama Feb 28 , 2017
አጼ ሚኒሊክን አለመውደድ ትችላለህ፤ በህይወት ዘመናቸው የሰሯቸውን እኒህን ድንቅ ተግባራት ግን መካድ አትችልም! ምክንያቱም በደማቅ ብእርና ብራና የተከተቡ ናቸውና!
1882 ዓ.ም. ---------------------ስልክ
1886 ዓ.ም. ---------------------ፖስታ
1886 ዓ.ም. ---------------------ባህር ዛፍ
1886 ዓ.ም. ---------------------ገንዘብ
1886 ዓ.ም. ---------------------የውሃ ቧንቧ
1887 ዓ.ም. ---------------------ጫማ
1887 ዓ.ም. ---------------------ድር
1887 ዓ.ም. ---------------------የሙዚቃ ት/ቤት
1887 ዓ.ም. ---------------------የፅህፈት መኪና
1889 ዓ.ም. ---------------------ኤሌክትሪክ
1889 ዓ.ም. ---------------------ዘመናዊ ህክምና
1889 ዓ.ም. ---------------------ሲኒማ
1889 ዓ.ም. ---------------------የሙዚቃ ሸክላ
1889 ዓ.ም. ---------------------ቀይ መስቀል
1890 ዓ.ም. ---------------------ሆስፒታል
1893 ዓ.ም. ---------------------ባቡር
1893 ዓ.ም. ---------------------ብስክሌት
1896 ዓ.ም. ---------------------መንገድ
1897 ዓ.ም. ---------------------ፍል ውሃ
1898 ዓ.ም. ---------------------ባንክ
1898 ዓ.ም. ---------------------ሆቴል
1898 ዓ.ም. ---------------------ማተሚያ
1898 ዓ.ም. ---------------------ላስቲክ
1899 ዓ.ም. ---------------------አራዊት ጥበቃ
1899 ዓ.ም. ---------------------የጥይት ፋብሪካ
1900 ዓ.ም. ---------------------ጋዜጣ
1900 ዓ.ም. ---------------------አውቶሞቢል
1900 ዓ.ም. ---------------------የሚኒስትሮች ሹመት
1901 ዓ.ም. ---------------------ፖሊስ ሰራዊት
1904 ዓ.ም. ---------------------የመድሃኒት መሸጫ ሱቆች
አጼ ሚኒሊክ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሀንዲስ!
ኦስሎ፡ እስታቫገር እና ትሮንደላግ ከተሞችና ዙርያው ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን፤ እኔ ለነጻነቴ ! በታላቌ የኖርዌይ ከተማ በሆነችው በርገን ከተማ ይካሄዳል ። Sat -March፡ 4፡ 2017 Time፡ ከ 2 ፡ 00 PM ጀምሮ የስብሰባውን ቦታ በቅርቡ እናስታውቃለን፡ ተጋባዥ እንግዳዶች፦ የአርበኞች ግንቦት 7 የውጭ አመራር አባላት የሆኑት፤ ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም እና አቶ ብዙነህ ጽጌ ክህዝቡ ጋር ይወያያሉ። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ለአንድነትና ለዴሞክርሲ የሚደረገው ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል። ይህ ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በመግባቱ ምክንያት ከመቸውም ግዜ ይልቅ የሚያስከፍለው ዋጋ እየጨመረ መጥቷል። በየዕለቱ በርካታ ታጋዮች የወያኔን ዘረኛ አምባገነን ቡድን አስወግዶ ፍትህ በሰፈነበት እኩልነት ያረጋገጠ የዲሞክራሲ ስርዓት ለመተካት በሚደረገው ትግል የመጨረሻውን የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ። በዚህ እጅግ አስቸጋሪ ሆኖም ምንም አማራጭ በሌለው ትግል ውስጥ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 የሕዝብን ትግል በማስተባበርና በመምራት የሚቻለውን ጥረት ሁሉ እያደረገ ይገኛል። በውጭ ሀገር የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን የህዝብ ወገኖች ለትግሉ ልናደርግ የምንችለውን አስተዋጽዖ መሃል ትግሉን በገንዘብ መደገፍ ነው። ይሄንንም አስተዋጽዖ ተግባራዊ ለማድረግ በከተማችን በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ በመገኘት አገራዊ ግዴታዎን ይወጡ ዘንድ አዘጋጅ ኮሚቴው ሲያስታውቅ በአክብሮት ነው። *እኔ ለነጻነቴ ! ዓለም አቀፍ የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ * ዝግጅት information ....47 40979331 /47 96815092 አዘጋጅ ፡ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርጫፍ ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር ! AG7 Public Meeting in Bergen - Norway - 4 March 2017
Monday, February 27, 2017
ፈረንጁን በካልቾ! ማን?- ፕሮፍ
“ይህች ወሬ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም አንድ ቀን እቤታቸው ለተገኘን ወጣቶች ያጫወቱን ጨዋታ ናት፦
...ኬንያ ናይሮቢ አንዲት መዝናኛ ቤት ተገኝቼ እየተዝናናሁ ነው። ቤቱ እንደ ፓርቲ ቤት ያለ ነው። ባንዱ ጥግ መጠጤን ይዤ፣ የዳንሱ ወለል ላይ ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚደንሱ ወጣቶችን አያለሁ።
በዚህ መሃል የባሕር ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ እንግሊዛዊያን ነጮች ገቡ። አንዱ እንግሊዛዊ ቀጥታ ወደ
Sunday, February 26, 2017
አጼ ሚኒሊክን አለመውደድ ትችላለህ፤ በህይወት ዘመናቸው የሰሯቸውን እኒህን ድንቅ ተግባራት ግን መካድ አትችልም! ምክንያቱም በደማቅ ብእርና ብራና የተከተቡ ናቸውና!
1835 ዓ.ም. ---------------------ወፍጮ
1882 ዓ.ም. ---------------------ስልክ
1886 ዓ.ም. ---------------------ፖስታ
1886 ዓ.ም. ---------------------ባህር ዛፍ
1886 ዓ.ም. ---------------------ገንዘብ
1886 ዓ.ም. ---------------------የውሃ ቧንቧ
1887 ዓ.ም. ---------------------ጫማ
1887 ዓ.ም. ---------------------ድር
1887 ዓ.ም. ---------------------የሙዚቃ ት/ቤት
1887 ዓ.ም. ---------------------የፅህፈት መኪና
1889 ዓ.ም. ---------------------ኤሌክትሪክ
1889 ዓ.ም. ---------------------ዘመናዊ ህክምና
1889 ዓ.ም. ---------------------ሲኒማ
1889 ዓ.ም. ---------------------የሙዚቃ ሸክላ
1889 ዓ.ም. ---------------------ቀይ መስቀል
1890 ዓ.ም. ---------------------ሆስፒታል
1893 ዓ.ም. ---------------------ባቡር
1893 ዓ.ም. ---------------------ብስክሌት
1896 ዓ.ም. ---------------------መንገድ
1897 ዓ.ም. ---------------------ፍል ውሃ
1898 ዓ.ም. ---------------------ባንክ
1898 ዓ.ም. ---------------------ሆቴል
1898 ዓ.ም. ---------------------ማተሚያ
1898 ዓ.ም. ---------------------ላስቲክ
1899 ዓ.ም. ---------------------አራዊት ጥበቃ
1899 ዓ.ም. ---------------------የጥይት ፋብሪካ
1900 ዓ.ም. ---------------------ጋዜጣ
1900 ዓ.ም. ---------------------አውቶሞቢል
1900 ዓ.ም. ---------------------የሚኒስትሮች ሹመት
1901 ዓ.ም. ---------------------ፖሊስ ሰራዊት
1904 ዓ.ም. ---------------------የመድሃኒት መሸጫ ሱቆች
An information verified from reliable sources!
አጼ ሚኒሊክ የኢትዮጵያ መሀንዲስ!
@ቆምጬ አምባው
አድዋ የነጻነት ድል
የካቲት ወር የአፍሪካውያን ወር ይባላል፡፡ ይህን ወር የአፍሪካውያን ወር ያሰኘው ብቸኛ ምክንያት የዓድዋ ድል ነው፡፡ ነጮች አፍሪካውያንን በግፍ በሚረግጡበት፣ በባርነት በሚገዙበት፣ ያሻቸውን ያለከልካይ በሚፈፅሙበት በዚያን ወቅት ” እምቢኝ! ሀገሬን በቅኝ አላስገዛም ” ብሎ በጀግንነት የተነሳ፣ ተነስቶም የቅኝ ገዢዎችን በትር በሀይል መስበር የተቻለበት ወር ይህ የካቲት ወር ነው፡፡
::ኢትዮጵያዊያን የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በወራሪው የጣሊያን ጦር ላይ ድል የነሱበት ታሪካዊ በዓል በወቅቱ የነበረውን ፍጹም የነጭ የበላይነት አስተሳሰብ በመስበር "የእንችላለን እናሸንፋለን" የሚል መንፈስን ያላበሰ የመላው ጥቁሮች ህዝብ ድል ነው።ኢትዮጵያ ከቅኝ ግዛት ተፅዕኖ ነፃ ሃገር በመሆን ህዝቦቿ የነፃነትን አየር እንዳሻቸው የሚምጉ የአፍሪካ ብሎም የአለም ተምሳሌት ነበረች፡፡ አሁን ግን በወያኔ መራሹ ፀረ ኢትዮጵያ ቡድን ነፃነትን ተነፍጋ ነፃነት አይታ የማታዉቅ ይመስል ነፃነትን አማትራ እያየች የምትገኝ ምስኪን አገር ሁና ትታያለች፡፡
Friday, February 24, 2017
ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ እና ሻለቃ አበበ ይመኑ ይናገራሉ – “ከብዙ ፈተና በኋላ የቀድሞውን ሠራዊትና ፖሊስ አባላትን በማሰባሰብ ረገድ የተሳካ ሥራ እየሠራን ነው”
ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ፤ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አርበኞች ማኅበር ምክትል ሰብሳቢ (ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ አውሮፕላን ይዘው የሄዱ) እና ሻለቃ አበበ ይመኑ፤ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አርበኞች ማኅበር ዋና ጸሐፊ፤ ስለ ማኅበራቸው ሚናና ትልሞች ይናገራሉ። ያነጋገራቸው የኤስ ቢኤስ ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ ነው – ያድምጡት::
በአንድ የክስ መዝገብ – በሽብርተኝነት ተከሰሱ !!! ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ዶ/ር መረራ ጉዲና
• አንፃራዊ ነፃነት በነበረበት በምርጫ 97 በከፍተኛ የሕዝብ ድምጽ የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች፣
• በውስጥም በውጭም – ከሌሎች ፓለቲከኖች ሁሉ በላይ የሕዝብ ድጋፍ ያላቸው መሆኑን ያስመሰከሩ፣
• በወጣትነታቸው ጊዜ የአገራችን ጉዳይ “ያገባናል” በማለት ባመኑበት መንገድ የታገሉ፣
• በጎልማሳነታቸው ጊዜም “ትግል በቃኝ” ሳይሉ ከቀድሞው የበለጠ ዋጋ በሚያስከፍል ትግል ተሳታፊዎች፣
• ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለአገር አንድነት … ከፍ ያለ ዋጋ በመክፈል ላይ ያሉ፣
• በተማሪዎቻቸው የተመሰገኙ መምህራን፣
• በሙያቸው የበቁ ብዙ የአካዳሚ የምርምር ጽሁፎችን ያወጡ ባለሙያዎች፣
• ቁምነገረኖች ሆኖም ፈገግታ የማይለያቸው ዜጎች፣
• ሩቅ ዓላሚዎች፣ ቀናዎች፣ በጎ ሰዎች፣ እና
• በተመሳሳይ የእድሜ ክልል ያሉ የኢትዮጵያ ምርጥ ልጆች
• በውስጥም በውጭም – ከሌሎች ፓለቲከኖች ሁሉ በላይ የሕዝብ ድጋፍ ያላቸው መሆኑን ያስመሰከሩ፣
• በወጣትነታቸው ጊዜ የአገራችን ጉዳይ “ያገባናል” በማለት ባመኑበት መንገድ የታገሉ፣
• በጎልማሳነታቸው ጊዜም “ትግል በቃኝ” ሳይሉ ከቀድሞው የበለጠ ዋጋ በሚያስከፍል ትግል ተሳታፊዎች፣
• ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለአገር አንድነት … ከፍ ያለ ዋጋ በመክፈል ላይ ያሉ፣
• በተማሪዎቻቸው የተመሰገኙ መምህራን፣
• በሙያቸው የበቁ ብዙ የአካዳሚ የምርምር ጽሁፎችን ያወጡ ባለሙያዎች፣
• ቁምነገረኖች ሆኖም ፈገግታ የማይለያቸው ዜጎች፣
• ሩቅ ዓላሚዎች፣ ቀናዎች፣ በጎ ሰዎች፣ እና
• በተመሳሳይ የእድሜ ክልል ያሉ የኢትዮጵያ ምርጥ ልጆች
እና
Thursday, February 23, 2017
ዶ/ር መረራ ጉዲና ክስ ተመሰረተባቸው ::
Ethiopia Human Rights Project
አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ንግግር ለማድረግ ተጋብዘው ሲመለሱ የግንቦት ሰባት አመራር እና ሊቀመንበር ከሆኑት ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ታይተዋል በሚል ለእስር የተዳረጉት ዶ/ር መረራ ጉዲና ከሶስት ወር የማእከላዊ ምርመር ቆይታ በኋላ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ የክስ ፋይሉ በዶ/ር መረራ ስም የተከፈተ ሲሆን ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሁለተኛ ተከሳሽ ፣ አቶ ጃዋር መሃመድ ሶስተኛ ተከሳሽ ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ ሶስቱም ተከሳሾች የተከሰሱት በወንጀለኛ መቅጫ ህጉን የተለያዩ አንቀጾች በመተላለፍ ሲሆን አራተኛ እና አምስተኛ ተከሳሽ የሆኑት የኢትዮጵያ ሳተላይ ቴሌቪዥን ( ኢሳት) እና ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ( ኢኤም ኤን) ተቋማቱ በሽብር ህጉን በመተላለፍ ተከሰዋል፡፡ በተጨማሪም ዶ/ር መረራ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የመተላፍ ተጨማሪ ክስ ተመስቶባቸዋል፡፡ የሚቀጥለው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የካቲት 25 2009 አም ነው ፡፡
Wednesday, February 22, 2017
እኔ ለነጻነቴ ! የአንድነትና የዲሞክራሲ የትግል ድጋፍና ውይይት በበርገን ከተማ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅት፡
Sat -March፡ 4፡ 2017
Time፡ ከ 2 ፡ 00 PM ጀምሮ
የስብሰባውን ቦታ በቅርቡ እናስታውቃለን፡
የክብር እንግዳ ተጋባዥ የንቅናቄው አመራሮች በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል..
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ለአንድነትና ለዴሞክርሲ የሚደረገው ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል።
ይህ ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በመግባቱ ምክንያት ከመቸውም ግዜ ይልቅ የሚያስከፍለው ዋጋ እየጨመረ መጥቷል። በየዕ
Tuesday, February 21, 2017
Monday, February 20, 2017
በውስጥ መሰመር የተላከመልዕክት ነው
share ይደርግ።አሁንኮ የወያኔ የስለላ መረብ ተበጣጥሷል ዋጋ የለውም አንድ ሚስጥር ላውራህ አሞራው ከሁለታችን ውጭ ማለፍ የለበትም እሺ ወያኔ እድሜው አልቋል ዋጋ የለውም ከወያኔ መከላከያ ከወያኔ ፌደራል ፖሊስ ከወያኔ ደህንነት የስለላ አባል ከወያኔ አጋዜ ከወያኔ አየር ሀይል ከወያኔ የፌደራል መስሪያ ቤት ከወያኔ የግር ጦር የሽምቅ ተዋጊ ከወያኔ የስምሪት የዘመቻ አላፊና የቁጥጥር ምድብውስጥ የከባድ መሳሪያ የቢኤም የሞርተር ድሽቃ እስናይፐር ላውንቸው ተኩዋሽ ውስጥ የተወርዋሪ ጦር ውስጥ ባስር አለቃ በአምሳ አለቃ መቶ አለቃ በመሆን አሁን በጠቀስኩልህ ውስጥ ሰርገን በመግባት እያበጣበጥነውና ስርአቱን ከድቶ ወደኛ እንዲመጣ በማድረግ ወደኛ ያልመጣውም መረጃ እንዲሰጠን በማድረግ የወያኔን መስሪያ ቤት እየገለባበጥነው በሌላ በኩል ለወያኔ ታማኝ ሁኜ አገለግላለሁ የሚለውን መከላከያ ወደኛ ጦርነት ሊከፍት ሲመጣ ከመነሳቱ በፊት እዛው ውስጥ ያሉት አባሎቻችን ቀድመው ለኛ መረጃውን ለኛ በማድረስ ያልጠበቀው ቦታ ላይ ቀድመን የማይችለውን የጥይት ዱላ እናሳርፍበታለን አሞራው ወያኔ አልሞት ባይ የሚፈራገጠው የህልም እሩጫ ነው ዋጋ የለውም የአማራውን ወጣት በሰፊው ሰዋራ ቦታ ላይ እያሰለጠን መሳሪያ እያስታጠቅነው ነው ኦሮሚያም ጀምረናል ቢኒሻንጉልንና ጋምቤላን በከፊል አስታጥቀነዋል ስራው ውስጥ ለውስጥ እየተፋጠነ ነው በርታልኝ ወንድሜ።
Saturday, February 18, 2017
አባይ ሚዲያ ዜና የወያኔን የጦርነት ግዳጅ ያልተቀበሉ በሶስት ተሽከርካሪዎች የተጫኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሸዋ ሮቢት እስር ቤት መታሰራቸው ተገለጸ
በዘርይሁን ሹመቴ
አገዛዙ የአማራና የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች የሆኑየመከላከያ ሰራዊት አባላትን በሶስት መካከለኛ የጭነትት ተሽከርካሪ ወደ ሸዋ ሮቢት እስር ቤት ማስገባቱን ምንጮች ገለጹ።
በኢትዮጵያዊነትና በኢትዮጵያ ሀገራዊ ኣንድነት ላይ የተቃጣው ጦርነትና የአርበኞች ግንቦት 7 ሀገር ኣድን ትግል | ነዓምን ዘለቀ
አባይ ሚዲያ
ራሱን ህዝባዊ ወይኔ ሃርነት ትግራይ በማለት በሚጠራው የጸረ-ኢትዮጵያ መሰሪዎች አምባገነናዊ አገዛዝ ላለፉት ሃያ አምስት አመታት የዘለቀ ስቃይ እና ጥቃት ኢላማዎች የነበሩት የኢትዮጵያ አንድነትና ኢትዮያዊነት ብቻ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችም በተናጠል እና በየተራ ግፍ እና ስቃይ ሲቀበሉ ቆይተዋል አሁንም በከፋ መልኩ ስቃዩ ቀጥሏል።
ጸረ ኢትዮጵያዊው ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በተደራጀ መልኩ የጥፋት ሰይፉን በዋናነት የመዘዘበት ኢትዮጵያዊነት ደግሞ አንዳንዶች እንደሚያምኑት የብሄር ብሄረስቦች ማለትም የኦሮሞው፣የአማራው የትግሬውየሶማሌው የሲዳማው፣የጉራጌው ፣ የአፋሩ፣የከምባታው እንዲሁም የሌሎች ብሄረሰቦች ድምር ማንነት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ከብሄሮች ድምር (The sum of its parts) በላይ ነው። ኢትዮጵያዊነት ለዘመናት የተገነባ ማንነት ነው። የየትኛውም ብሄር ወይም ነገድ ባህልና ቋንቋ ብቻውን ኢትዮጵያዊነትን አይገልጸውም፣ አይበቃውም፣ አይተረጉመውም።
Friday, February 17, 2017
Thursday, February 16, 2017
Wednesday, February 15, 2017
Tuesday, February 14, 2017
''በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአባይን ግድብ ለመጠበቅ በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ዋና ከተማ ደብረዘይት አልፎ ቦጎንዲ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከፍተኛ ቦታ የተተከለው ራዳር በስርዓቱ በተማረረ የፈጥኖ ደራሽ ፌድራል ፖሊስ አባል መመታቱ ተሰምቷል።
በራዳሩ የቴክኒክ ባለሙያወች ላይ ያነጣጠረው ጥቃቱ በራዳሩ ሲስተሚክ ክፍሎች ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ና አንድ የራዳሩ የአይሲቲ ባለሙያ በፈጥኖ ደራሽ የፌድራል አባል መገደሉ ታውቋል። በአከባቢው ከፈጥኖ ደራሽ ልዩ ሃይል የፌድራል ወታደሮች በተጨማሪ የ12 ክ/ጦር እንዲሁም የ7 ክ/ጦር በተለያዩ ሬጂመንቶች በተለያዩ የግድቡ ክፍሎች ና አከባቢው እንደተሰማሩ ይታወቃል።ራዳሩን የሚጠብቀው የፌድራል ልዩ ሃይል እርስ በርሱ መተማመን አቅቶታል ሁሉም እርስ በርሱ እየተጠባበቀ ይገኛል።ይሄንን ጉዳት ተከትሎ በሁለት በኩል ወታደሮችና የቴክኒካል ባለሙያወች ወደ አካባቢው ለመሄድ ያደረጉት ጥረት በአንደኛው በኩል በሸመቁ ሃይሎች በደረሰባቸው የደፈጣ ውጊያ በመኪናው ላይ ከነበሩት ወታደሮች 4ቱ ተገድለው ጉዟቸው ሳይሳካ ቀርቷል።'' የኢሳት ምንጮች የላኩት ዘገባ
ዝርዝሩን ከዛሬው የኢሳት ሬዲዮ መከታተል ይቻላል
Monday, February 13, 2017
የኢሳት ሬዲዮ ''በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአባይን ግድብ ለመጠበቅ በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ዋና ከተማ ደብረዘይት አልፎ ቦጎንዲ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከፍተኛ ቦታ የተተከለው ራዳር በስርዓቱ በተማረረ የፈጥኖ ደራሽ ፌድራል ፖሊስ አባል መመታቱ ተሰምቷል። በራዳሩ የቴክኒክ ባለሙያወች ላይ ያነጣጠረው ጥቃቱ በራዳሩ ሲስተሚክ ክፍሎች ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ና አንድ የራዳሩ የአይሲቲ ባለሙያ በፈጥኖ ደራሽ የፌድራል አባል መገደሉ ታውቋል። በአከባቢው ከፈጥኖ ደራሽ ልዩ ሃይል የፌድራል ወታደሮች በተጨማሪ የ12 ክ/ጦር እንዲሁም የ7 ክ/ጦር በተለያዩ ሬጂመንቶች በተለያዩ የግድቡ ክፍሎች ና አከባቢው እንደተሰማሩ ይታወቃል።ራዳሩን የሚጠብቀው የፌድራል ልዩ ሃይል እርስ በርሱ መተማመን አቅቶታል ሁሉም እርስ በርሱ እየተጠባበቀ ይገኛል።ይሄንን ጉዳት ተከትሎ በሁለት በኩል ወታደሮችና የቴክኒካል ባለሙያወች ወደ አካባቢው ለመሄድ ያደረጉት ጥረት በአንደኛው በኩል በሸመቁ ሃይሎች በደረሰባቸው የደፈጣ ውጊያ በመኪናው ላይ ከነበሩት ወታደሮች 4ቱ ተገድለው ጉዟቸው ሳይሳካ ቀርቷል።'' የኢሳት ምንጮች የላኩት ዘገባ ዝርዝሩን ከዛሬው የኢሳት ሬዲዮ መከታተል ይቻላል https://ethsat.com/2017/02/esat-radio-mon-feb-13-2017/
“ወደ ትጥቅ ትግሉ የገባሁት እንደ ኢትዮጵያዊነቴና ለመላው ኢትዮጵያዊ እንጂ እንደ ህውሃት የጠበበ የዘር ፓለቲካ አንግቤ አይደለም” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ
http://amharic.abbaymedia.com/%
ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር በቀጥታ በኔት ወርክ በ46 የአለማችን ከተሞች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ንግግር ማድረጋቸውና ለቀረበላቸው ጥያቄዎችም ምላሽ መስጥታቸው ታወቀ።
ከሊቀመንበሩ በተጨማሪም በበርሃ ለነጻነት የሚታገሉ አርበኞችም የትግሉን መንፈስ ፣ ትግሉን ፍሬያማ ለማድረግ የሚያስፈልገውን ቁርጠኝነትና ርብርቦሽ ከበረሃ በቪዲዮ የተቀረጸ መልክታቸውን ለተሰብሳቢዎች ማስተላለፋቸውንም መገንዘብ ተችሏል ።
ይህ በአይነቱ አዲስና ለየት ያለ ቁጥራቸው የበዛ በተለያዩ የአለም ክፍል የሚገኙ ከተሞችን በኔት ወርክ በቀጥታ በማገናኘት የተደረገው ህዝባዊ ስብሰባ በተሳካ መልኩ እንደተጠናቀቀ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
Prof. Berhanu Nega says front plays leading role in popular resistance
ESAT News (February 13, 2017)
Prof. Berhanu Nega, Chairman of the Patriotic Ginbot 7, an armed resistance group fighting the Ethiopian regime, says the uprising and popular resistance seen in Ethiopia over the last year have proven right the front’s strategy of employing all kinds of struggle against the authoritarian regime.
አርበኞች ግንቦት ሰባት በሰላሳ ከተሞች የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባና የድጋፍ ማሰባሰብ ዝግጅቶች ማድረጉን አስታወቀ
ኢሳት (የካቲት 6 ፥ 2009)
አርበኞች ግንቦት 7 “እኔ ለነጻነቴ” በሚል መሪ ቃል በሰላሳ ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባና የድጋፍ ማሰባሰብ ዝግጅት በስኬት ማጠናቀቁን ገለጹ።
ንቅናቄው እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ፌብሯሪ 11 እና 12 ቀን 2017 “እኔ ለነጻነቴ” የሚል ውይይትና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ያደረገው በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ የተለያዩ ግዛቶች፣ በአውሮፓ፣ በካናዳና፣ ደቡብ አፍሪካ መሆኑ ታውቋል።
ከተሞችን በሁለት ቀን በመክፈል በተመሳሳይ ሰዓት በቀጥታ ውይይት በተካሄደው ስብሰባ የድርጅቱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከትግሉ ስፍራ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን፣ በተሰብሳቢዎች ለተነሱ ጥያቄዎች በስካይፕ ተገኝተው በቀጥታ ምላሽ ሰጥተዋል።
የንቅናቄው ሊ/መንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባስተላለፉት መልዕክት “አርበኞች ግንቦት ሰባት የሚታገለው በአገራችን ዕውነተኛ የሆነ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ለማስጀመር እንጂ ስልጣን ለመያዝ አይደለም” በማለት ገልጸዋል።
በቅማንት ስም የእርስ በእርስ ግጭት በማስነሳት የታላቁዋን ትግራይ ሕልም ከማሳካት እንደማይመለስ የብሄሩን ተወላጆች ሰብስቦ አስፈራራ፣በኦሮሚያ ውስጥ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሲጠናቀቅ ለአዲስ ተቃውሞ እንደሚወጡ ተናገሩ
#Ethiopiaሕወሃት ፕ/ር ብርሃኑ የነጻነት እየተባለ የሚጠቀሰው የትግል እንቅስቃሴ የድርጅታቸው ትግል መሆኑን ገለጹ፣የሶማሊላንድ መንግስት ዛሬ የበርበራ ወድብን ለአረብ ኤሜሬት ወታደራዊ ሰፈርነት መፍቀዱ ከኢህአዲግ አገዛዝ በኩል ተቃውሞ ገጠመው፣በአገር ቤት በይስሙላ ድርድር የሚሳተፉ ተለጣፊ ተቃዋሚዎች አገዛዙ ከሕዝብ ጥቃት እንዲጠብቃቸው ጠየቁ ሌሎችም
Hiber Radio
እኔ ለነጻነቴ! ዓለም አቀፍ “የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ” ዝግጅት 2017
እኔ ለነጻነቴ ፌብሯሪ 11 ና 12 በታቀደው መሰረት በተሳካ ሁኔታ ከ 34 ከተሞች በላይ በጋራ በተደረገው የኢንተርኔት ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ ተኳሂዷል በስብሰባው ወቅትየድርጅቱ ሊቀመንበር እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ቀጥታ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ከተሳታፊው ለተነሱ ጥያቄዎች ቀጥታ አርበኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መልስ የሰጡ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች ላይ የጫረታ ና ከፍተኛ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደርጓል።
እኔ ለነጻነቴ!
Sunday, February 12, 2017
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ
የዕለተ እሁድ ፡ የካቲት 5- ቀን፡ 2009 የሬድዮ ስርጭት፡
ወያኔ ሱማሌ ብሎ በሚጠራው ክልል በተደረገው ውግያ በርካታ የወያኔ ወታደሮች ሲቆስሉ አንድ የልዩ ሃይል አዛዥ ተገደለ።
Saturday, February 11, 2017
እኔ ለነጻነቴ !
የሚገርመው በ30 ከተሞች በተመሣሳይ ቀንና ሰዓት ስብሰባ መደረጉ ብቻ ሳይሆን፤ ሁሉም የስብሰባዎቹ አዳራሾች ከአፍ እስከ ገደፋቸው ጢም ማለታቸው ነው።
የቀጥታ ስርጪቱና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞቹም ከተጠበቁት በላይ በስኬት መጠናቀቃቸውን አስተባባሪዎቹ እየገለጹ ናቸው።
Dereje Habtewold
እኔ ለነጻነቴ!ዓለም አቀፍ የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ ዝግጅት ፌብሯሪ 11/12, 2017
30+ ከተሞች በአንድ ላይ ቅዳሜና እሁድ ፌብሯሪ 11 እና 12 2017 ዓ.ም
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ለአንድነትና ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል፣ ይህ ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በመግባቱ ምክንያት ከመቼው ጊዜ ይልቅ የሚያስከፍለው ዋጋ እየጨመረ መጥቷል። በየዕለቱ በርካታ ታጋዮች የወያኔ ዘረኛ አምባገነን ቡድን አስወግዶ፣ ፍትህ በሰፈነበት፣ እኩልነትን ባረጋገጠ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመተካት በሚደረገው ትግል፣ የመጨረሻውን የሕይወት መሰዋትነት ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ። በዚህ እጅግ አስቸጋሪ፣ ሆኖም ምንም አማራጭ በሌለው ትግል ውስጥ፣ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7፣ የሕዝቡን ትግል በማስተባበርና በመምራት የሚቻለውን ጥረት ሁሉ እያደረገ ይገኛል። በውጭ ሀገር የምንገኝ ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ወገኖች፣ ለትግሉ ልናደርገው ከምንችለው አስተዋጽዖ መሀል፣ ትግሉን በገንዘብ መደገፍ ነው። ይሄንንም አስተዋጽዖ ተግባራዊ ለማድረግ በመላው ዓለም በሚገኙ ከ30 በላይ ከተሞች ውስጥ “እኔ ለነጻነቴ!ዓለም አቀፍ የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ ዝግጅት” በሚል ዝግጅት ተዘጋጅቷል። የዚህ ዝግጅት፣ የከተማ ዝርዝሮች፣ የአድራሻዎች እና መሰል መረጃዎች ከዚህ በታች ቀርቧል።
አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ
Friday, February 10, 2017
Thursday, February 9, 2017
ታሪክን ምርኮኛ የማድረግ ዘመቻ
ዶ/ር ነብዩ ጋቢሳ
ከሰሞኑ የፖለቲካችን የስበት ማእከል ታሪክ እና የታሪክ ባለሙያዎች ሆነዋል። ፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ የተባሉ የታሪክ ምሁር ከኢሳት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ በሶሻል ሚዲያው ከፍተኛ አዋራ ማስነሳቱ ሳያንስ፣ የተዳፈኑ የመሰሉ ጉዳዮችንም በመቀስቀስ ላይ ይገኛል። በመጀመሪያ የዶክተሩን ቃለምልልስ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በጽሞና ለመከታተል ሞክሬአለሁ። በዚህም ተጠያቂውን ዶ/ር ኃይለማርያም ላሬቦ ከሙያም ሆነ ስነምግባር አንጻር የበቃ ችሎታቸውን ለመታዘብ ችያለሁ።
ይሄ ሰንደቅ የጥቁር ህዝብ ኩራት ፣የነፃነት ቀንዲሉ የአሸናፊነት ምልክቱ ነው ሲባል ዝም ብሎ አይደለም።
ይህችን ውብ ሰንደቅ የትግላቸው ብቻ ሳይሆን የአምልኳቸውም መለያ እስከማድረግ የደረሱ አሉ።
ባህር አቋርጦ መላው ጥቁር ህዝብን ከእንቅልፍ አንቅቶ ከሰው ያላነሰ ፍጥረት መሆኑን እንዲያውቅ ያደረገ የልባምነት መለያ ነው።
ይህ ሰንደቅ ለመብት አታግሎ ብዙዎችን ነፃ ያወጣ አርማ ነው።
ከኢትዮጵያውያን ለመላው ጥቁር ህዝብ የተበረከተ የአሸናፊነት ሽልማት።
ዛሬም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚዘምሩለት።
አዎ ለኢትዮጵያዊነት ይዘፍናሉ፣ይገጥማሉ፣ይስላሉ፣ያወራሉ ..!!!
በኢትዮጵያ ፍቅር ተለክፈው በመንፈሷ ተመስጠው በቅድስናዋ ተቀድሰው በእምነቷ ተማምነው ይኖራሉ።
ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ነው።ይህ የማይገባህ እነዚህን የካረቢያን ህዝቦችን ሄደህ ጠይቃቸው።
ጊታራቸውን እየመቱ በሬጌ ስልት እየጨፈሩ አንተ ሰምተህ የማታውቀውን ብዙ ብዙ ነገር ይተርኩልሃል....በጥበብ ከሽነው !!!!!! ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን !!!!
Yoseph Yitna
ኦስሎ ፡ በርገን ፡ ይሰማል ወይ? እኔ ለነጻነቴ! ዓለም አቀፍ “የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ” ዝግጅት 2017
ኦስሎ ፡ በርገን ፡ ይሰማል ወይ?
እኔ ለነጻነቴ! ዓለም አቀፍ “የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ” ዝግጅት 2017
ላልሰማ ያሰሙ፣
እባክዎ ሼር ያድርጉ!
ሙሉ የዓለም አቀፍ አዳራሻዎች በአርበኞች ግንቦት 7 ድህረገጽ ይገኛል http://www.patriotg7.org/ene-le-netsanete-ag7-internationa…/
Wednesday, February 8, 2017
ሰበር መረጃ ! ! ጥር / 29 / 2009 የሰሜኑ እዝ ወታደራዊ የትጥቅ ማከማቻዎች ተፈተሹ !
በዋና እዝ ዉስጥ የሚገኙ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች በወረደላቸዉ ትእዛዝ መሰረት ወታደራዊ የትጥቅ ማከማቻዎችን እንዲፈትሹ በወጣዉ ትእዛዝ
የ8ኛ ብረት ለበስ ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጄ ጀማል መሐመድ፣ የ31ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ብ/ጄ ተስፋዬ ወ/ማርያም፣ የ35ተኛ ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጄ ምስጋናዉ አለሙ፣ የ24ተኛ ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጄ ሞሐመድ ተሰማ፣ የ22ተኛ ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጄ ገ/ እግዚያብሔር በየነ የ33ተኛ ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጄ አማሐ ገብሩ ባጠቃላይ የመሳሪያ መጋዘኖቻቸዉ ላይ ከፍተኛ ዘረፋ መፈጸሙን አምነዋል።
Tuesday, February 7, 2017
ወያኔ ለሱዳን ተጨማሪ ሰፊ መሬት አሳልፎ ሰጠ!
#Ethiopiaይህ በዚህ ሰሞን የተፈፀመው ክህደት ዝርዝሩ እንደሚከተለው ነው፡የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከማህበረሠቡ እና ከእንስሳት ግጦሽ የራቀ የሚያስደምም በአረንጓዴነቱ ለምነቱ እና የዱር እንስሳት መስህብነቱ ልዮ የሆነ ሞቃታማ መጠነ ሰፊ የሆነ በሰሜን ምስራቅ የአማራ ክልል አዲሱ አላጢሽ ብሄራዊ ፓርክ በምዕራብ የደቡብ ሱዳን ዲንደር ብሄራዊ ፓርክ የሚያዋስነው ነው፡፡ ታድያ የእናት ሀገራችንን ስትራቴጅክ መሬቶ እንደ ባእዳን የኢትዮጵያን የህዝብ ዉሳኔ እና እውቅና ወደ ጎን በማለት የሌብነት ብቻ ሳይሆን በቀጣይ የሚኖረውን ህዝብ ሰላምና ህልውና የሚያሳጣ ክህደት ነው የተፈፀመው።
Monday, February 6, 2017
እነሆ ታላቅ የውይይት መድረክ :-
የፊታችን ፌብሯሪ -11-2017 ዓ/ም የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ * እኔ ለነጻነቴ ! መሪ ቃል በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ህዝባዊ ውይይት መድረክና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተዘጋጅቱዋል።
በዚህ ፕሮግራም መርሐ ግብር መሰረት እኔ ለነፃነቴ ! ዓለም አቀፍ የአንድነት እና የዲሞክራሲ ትግል ድጋፍ ዝግጅት አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነት እና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በኖርዌይ ኦስሎ አካባቢ ለምትኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እኔ ለነፃነቴ ! በሚል መሪ መፈክር በሐገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ግልፅ ውይይት ለማድረግ እና የወያኔን ዘረኛና ፋሺስት ስርዓት ለማስወገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉትን የነፃነት ሐይሎች ድጋፍ በመስጠት አጋርነታችንን እንድናሳይ የኖርዌይ አርበኞች ግንቦት ሰባት February 11/2017 ከ 2pm ጀምሮ ይጠብቆታል።
Sunday, February 5, 2017
Saturday, February 4, 2017
ሰበር ዜና በተከዜ ተፋሰስ ላይ ያሉ የወያኔ ተቋማት ተጠቁ!
ተምዘግዛጊ ሚሳኤል/RPG ነገር ሲወድቅ ታይቷል!
#ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በታላቁ ዋልድባ ገዳም ላይ ወያኔ በድፍረት የጀመረው የስኳር አገዳ ተቋም ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት በመወሰዱ ድርጅቱ ስራውን ማከናወን ከተሳነው ቆይቷል። ይህን ጥቃት የሚፈፅሙት ሙሉ ትጥቅ የታጠቁ በጣም በፍጥነት የሚወረወሩ እጅግ የሚያስፈራ ግርማ ሞገስ ያላቸው የተደራጁ ሃይሎች ስለመሆናቸው በደስታ የተሞሉ የአካባቢው የአይን እማኞች በአድናቆት ይገልፃሉ።
#በዛሬው እለት ደግሞ እጅግ እንግዳ የሆነ ጥቃት ተፈፅሟል። ከርቀት እየተምዘገዘገ የመጣ እረጅም የእሳት አለሎ ወደ ተከዜ ድልድይ አቅጣጫ ይወረወርና ከድልድዩ በቅርብ እርቀት ላይ ያለ ጋራ ላይ ፈንድቶ በአካባቢው ከፍተኛ መናጋት ፈጥሯል። በቦታው የነበሩት ይህ ተምዘግዛጊ ሚሳኤል/RPG ነገር ከየት እንደተተኮሰና ማን እንደተኮሰው ባይታወቅም ለተከዜ ድልድይ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም ብለዋል። ለትግራይ ልዩ አገልግሎት እንዲውል በከፍተኛ ወጭ የተገነባው የተከዜ የሃይል ማመንጫ ግድብም በቅርብ ርቀት ላይ ነው የሚገኘው።
ሙሉነህ ዮሃንስ
ሰበር ዜና በሰሜን ጎንደር ወያኔ ኋይለኛ ፍተሽ እያካሂደ ነው
ፍተሻው የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ትደግፋለቹ ገንዘብ ታቀብላልቹህ በሚል ማነኛውም ህዝብ ከኪሱ ከ1500 ብር በላይ ይዞ ከተገኝ ውርስና ድብድባ ይፈጸምበታል ከትክል ድንጋይ እስከ ሳንጃ - ሶሮቃ- አብራጅራ አጥቃላይ አርማጭሆ ኋይለኛ የሆነ ፍትሻ እየተካሂድ ነው በቆላ ወገራም የነጻነት ኋይሎችን ካቅማቸው በላይ በመሆኑ እነሱን ለማግኘት ወደ ዋልድባ ገዳም የወያኔ ካድሪዎች መለኩሴ መስለው በመግባት ሥለላ እያካሂዱ መሆናቸውን የውስጥ አርበኛ አርጋገጡልኝ በሊላ በኩል ፍተሻ የሚያካሂዱት ወታደሮች አብዛኛዎች ቋንቋንቸው የማይሰማ የጋምቢላና የግሙዝ ተወላጆች ኒዮር ሊሎቹም ናቸው።
ራሳቸው እኒህ ወታደሮች እንደዚህ አሉ እኛ የተነገረን የአማራ ህዝብ ትቢተኛ ነው በዱላ በሉት እራስራሱን በሉት የተባለነው ከበላይ አካል የተላለፈ ትዛዝ ሁኖም እኛ ሥራቱን ፈልገነው ሳይሆን አማራጭ አትን እንጅ በኛ ዚጎች ላይም ስምታቹኋል በጋምቢላ ላይ በአኟክ ህዝብ ላይ እንዲት እንደጨፈጨፉት አልፎም የደቡብ ሱዳን መንግስት በባለፈው ህጻናት ሳይቀር በአሻጥር ሊጨፈጨፍ ችሏል ብለዋል ከውስጥ አዋቂ ያደርሱኝ መርውጃ ካምባጊወርጊስ ደባርቅ እንቃሽ አጠቃላይ ህዝቡን ያጋኙት በዱላና ባገኙት ይደበድቡታል አሞራው ምንአለ ባሻ ይሂን ሁሉ የምጽፍልህ እንባው እየተናነቀኝ በሆዴ እየተቃጠልኩኝ ነው የምጽፈው ከዚህ ውስጥ ግን አንድም የአማራ ወታደር ወይም የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ መከላከያ በፍጹም አታገኝም።
የአማራና የኦሮሞ መከላከያ ሠራዊት በጋምቢላና በየጠረፉ ያስማሯቸው በወገናቸው ላይ የዚህ አይነት ግፍ በህዝባቸው ላይ እንደማይፈጽሙ ሰላወቀ ከጠረፍ በባድሜና በተለየዩ ቦታ የሚያስቀምጣቸው።
በሊላ በኩል የቅማንትና የአማራን ህዝብ ለማጋጨትና እርስበርስ ለማጋደል ያደረገው ሴራ ሙሉ በሙሉ በህዝቦች ንቃት ሊከሽፍ ችሏል ይሂንም ያመጣቹሁት እራሳቹህ እናተው ሁለቱ ህዝቦች የተዋለዱና በሁሉም ሥነመግባር አንድ ነን በማለት አሳፍረው መልሰውታል፡ ካድሪዎች ብቻ ናቸው ውስጥ ለውስጥ ነገሩን የሚያከባልሉት ሊሳካላቸውም አልቻሉም ያላደርጉት ነገር የለም በህዝቡ ንቁ ተሳትፎ አክሽፈውታል።
ወሎ ውስጥ በዚህ ተመሳሳይ ሞክረ ሊሳካላቸው አልቻሉም። ጎጃምም በዚህው መንገድ አሉ አሉ ህዝቡ ከነሱ ቀድሞ ነቅቶባቸዋል።
አሁን የአማራን ህዝብ በፍተሻና በማሽማቀቅ ሆን ብሎ ተያይዞታል ነገሩ ግን ለድል መብቃቱ አይቀርም።
አዳዲስ ነገር ሲኖር እመለሳለሁ።
ሞት ለገዳይ ለአምባገነኖች
ድል ለጭቁኑ ህዝብ፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር በክብር ።
ካርበኞች መነደር አሞራው ምንአለ ባሻ ነኝ#
Friday, February 3, 2017
ሰበር ዜና አባይ ወልዱ ደም በደም እስኪሆኑ ተደበደቡ
የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ የአንፍጫው ደም በደም እስኪሆንና አንድ ዓይኑ እስኪያብጥ ድረስ ከፍተኛ የቦክስ ድብደባ ደረሰበት፡፡
ድብደባው የደረሰበት በትግራይ ክልል የማር ምርት እያቀረበ የሚገኝበት ብዙ ሚሊዮን ብር ያወጣበት ኢንቨስትመንቱ አደጋ ላይ በመውደቁ እንዲታደግለት ለአባይ ወልዱ ጥያቄ ሲያቀርብ አጥጋቢ ምላሽ አላገኘሁም ባለ ዲያስፖራ ነው።
ዲያስፖራም አቶ አባይ ወልዱ ላይ ከፍተኛ የቦክክስ ጥቃት በሁለት እጆቹ ሲያደርስበት መሬት ላይ ወደቀ፡፡ መሬት ላይ ወድቆም ሊተወው አልቻለም፡፡ በእግሩ ረገጠው፡፡ ይህን ሁሉ ሲሆን ፀሀፊዎቹ በእሪታ ሲያቀልጡትና ዘበኞቹ ወደ ሰማይ ሲተኩሱ ነበር፡፡
እንደ ምንጮቹ ገለጻ በአሁን ሰዓት ዲያስፖራው እስር ላይ ይገኛል፡፡ (የዜናው ምንጪ ወዳጃችን ፍስሀ ደስታ ሀጎስ ነው)
(ትናንት ማታ 9 የህወኃት ካድሬዎች ባህርዳር ላይ ክፉኛ በትር ቀምሰው ሆስፒታል እንደተኙ መዘገቡ ይታወሳል)
Dereje Habtewold
በሶማሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያ ወታደራዊ ሃላፊዎች በጦር መሳሪያ ንግድና በሌሎች የሙስና ወንጀሎች ውስጥ ተሰማርተው እንደሚገኙ ተገለጸ
በሶማሊያ ተሰርቶ በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በወታደራዊ አመራርነት የተቀመጡ ሃላፊዎች በጦር መሳሪያ ንግድና ሌሎች የሙስና ወንጀሎች ውስጥ ተሰማርተው መገኘታቸውን የሃገሪቱ መገኛኛ ብዙሃን ሃሙስ ዘገቡ።
ለበርካታ አመታት በሶማሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት በሃላፊነት በማገልገል ላይ ያሉ ሃይሌ ገብሬ በዚህ ህገወጥ ድርጊት በመሰማራት ከፍተኛ ንብረት በማካበት ላይ መሆናቸውን ሱና ታይምስ የተሰኘ ጋዜጣ የአመራሩን ፎቶ በማስደገፍ ለንባብ አብቅቷል።
በቅፅል ስማቸው በሶማሊውያን ዘንድ ጀኔራል ገብሬ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት እኝሁ ወታደራዊ መኮንን ከሶማሊያ መንግስት ጋር በመመሳጠር የጸጥታ ድጋፍ የሚለግስን ገንዘብ እየመዘበሩ እንደሚገኝ ጋዜጣው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የሃይሌ ገብሬ የቅርብ ባልደርቦች ዋቢ በማድረግ ለንባብ አብቅቷል።
Thursday, February 2, 2017
ሰበር መረጃ !
ሕገ-ትራንፕ ለህገ ህወሀት የአፈና ስልት አዲስ ምእራፍ ከፈተ::
የብሄራዊ መረጃው የውጭ ሥለላ ክትትል ቡድን በቦሌ አየር ማረፊያ አይኖቹን ሰክቶ ከአሜሪካ ተመላሽ ጥርዞችን ለማገት በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል !
እንደወረደ የከተብነው መረጃ እንደሚጠቁመው የወያኔ ሀርነት ትግራይ የውጭ ጉዳይ ስለላ መረብ በአለም አቀፍ ቦሌ አየር ማረፊያ ዴስክ ላይ ለተሰማሩ ኢምግሬሽን ባልደረባዋች በአሜሪካ ይኖራሉ የተባሉ ከፍተኛ ተቃዋሚዋችን ፎቶ ግራፍና የተለያዩ መረጃዋችን በማሳለፍ ልዩ ጥበቃ በማድረግ ላይ ይገኛል::
ህወሀት በትናትና እለት ከአሜሪካ የተመለሱ 2 ግለሰቦችን በቦሌ አየር ማርፊያ በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን የአሜርካ ተመላሽ ታጋቾች ከፍተኛ ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛሉ
ታጋቾቹ በህወሀት የፀጥታ ሀይሎች የመጉዋጉዋዣ ሰነድ ( Pasport ) እና ገንዘብ ከመነጠቃቸው በተጨማሪ የተቀባዮቻቸው ማንነትና የመኖሪያ አድራሻ እንዲሄሁም የዋስትና ማረጋገጫ ንብረቶች ባጠቃላይ በብሄራዊ መረጃ ውሳኔ ቁጥጥር ውስጥ ወድቀዋል::
በህወሀት የበቀል እቅድ ውስጥ በጉጉት የሚጠበቁ የእሜርካ ተመላሽ ስደተኞች በተቻላቸው መጠን ጥንቅቃቄ እንዲያደርጉ ከወዲሁ እናሳስባለን::
( ጉድሽ ወያኔ )
Subscribe to:
Posts (Atom)