Thursday, February 23, 2017

ዶ/ር መረራ ጉዲና ክስ ተመሰረተባቸው ::


Ethiopia Human Rights ProjectImage may contain: 1 person, eyeglasses, sunglasses and closeup
አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ንግግር ለማድረግ ተጋብዘው ሲመለሱ የግንቦት ሰባት አመራር እና ሊቀመንበር ከሆኑት ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ታይተዋል በሚል ለእስር የተዳረጉት ዶ/ር መረራ ጉዲና ከሶስት ወር የማእከላዊ ምርመር ቆይታ በኋላ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ የክስ ፋይሉ በዶ/ር መረራ ስም የተከፈተ ሲሆን ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሁለተኛ ተከሳሽ ፣ አቶ ጃዋር መሃመድ ሶስተኛ ተከሳሽ ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ ሶስቱም ተከሳሾች የተከሰሱት በወንጀለኛ መቅጫ ህጉን የተለያዩ አንቀጾች በመተላለፍ ሲሆን አራተኛ እና አምስተኛ ተከሳሽ የሆኑት የኢትዮጵያ ሳተላይ ቴሌቪዥን ( ኢሳት) እና ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ( ኢኤም ኤን) ተቋማቱ በሽብር ህጉን በመተላለፍ ተከሰዋል፡፡ በተጨማሪም ዶ/ር መረራ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የመተላፍ ተጨማሪ ክስ ተመስቶባቸዋል፡፡ የሚቀጥለው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የካቲት 25 2009 አም ነው ፡፡
የክስ ዝርዝሩ ተከሳሾች በዋና አድራጊነት ሽብር ተግባር መፈጸማቸውን እና ለኦሮሚያ እና አማራ ክልል አመጾች ተጠያቂ መሆናቸውን እና በሚሊኖች የሚቆጠር ንብረት መጥፋት የነሱ አመጽ ማነሳሳት መሆኑን ክሱ ያትታል፡፡ ሙሉ ክሱን ከስር በሚገኘው ሊንክ ላይ ዳውን ሎድ ማድረግ ይቻላል፡፡

No comments:

Post a Comment