Saturday, February 4, 2017

ሰበር ዜና በተከዜ ተፋሰስ ላይ ያሉ የወያኔ ተቋማት ተጠቁ!


ተምዘግዛጊ ሚሳኤል/RPG ነገር ሲወድቅ ታይቷል!Image may contain: outdoor and water

#ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በታላቁ ዋልድባ ገዳም ላይ ወያኔ በድፍረት የጀመረው የስኳር አገዳ ተቋም ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት በመወሰዱ ድርጅቱ ስራውን ማከናወን ከተሳነው ቆይቷል። ይህን ጥቃት የሚፈፅሙት ሙሉ ትጥቅ የታጠቁ በጣም በፍጥነት የሚወረወሩ እጅግ የሚያስፈራ ግርማ ሞገስ ያላቸው የተደራጁ ሃይሎች ስለመሆናቸው በደስታ የተሞሉ የአካባቢው የአይን እማኞች በአድናቆት ይገልፃሉ።
#በዛሬው እለት ደግሞ እጅግ እንግዳ የሆነ ጥቃት ተፈፅሟል። ከርቀት እየተምዘገዘገ የመጣ እረጅም የእሳት አለሎ ወደ ተከዜ ድልድይ አቅጣጫ ይወረወርና ከድልድዩ በቅርብ እርቀት ላይ ያለ ጋራ ላይ ፈንድቶ በአካባቢው ከፍተኛ መናጋት ፈጥሯል። በቦታው የነበሩት ይህ ተምዘግዛጊ ሚሳኤል/RPG ነገር ከየት እንደተተኮሰና ማን እንደተኮሰው ባይታወቅም ለተከዜ ድልድይ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም ብለዋል። ለትግራይ ልዩ አገልግሎት እንዲውል በከፍተኛ ወጭ የተገነባው የተከዜ የሃይል ማመንጫ ግድብም በቅርብ ርቀት ላይ ነው የሚገኘው።
ሙሉነህ ዮሃንስ

No comments:

Post a Comment