Monday, February 6, 2017

እነሆ ታላቅ የውይይት መድረክ :-




የፊታችን ፌብሯሪ -11-2017 ዓ/ም የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ * እኔ ለነጻነቴ ! መሪ ቃል በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ህዝባዊ ውይይት መድረክና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተዘጋጅቱዋል።Image may contain: 2 people, text

በዚህ ፕሮግራም መርሐ ግብር መሰረት እኔ ለነፃነቴ ! ዓለም አቀፍ የአንድነት እና የዲሞክራሲ ትግል ድጋፍ ዝግጅት አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነት እና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በኖርዌይ ኦስሎ አካባቢ ለምትኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እኔ ለነፃነቴ ! በሚል መሪ መፈክር በሐገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ግልፅ ውይይት ለማድረግ እና የወያኔን ዘረኛና ፋሺስት ስርዓት ለማስወገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉትን የነፃነት ሐይሎች ድጋፍ በመስጠት አጋርነታችንን እንድናሳይ የኖርዌይ አርበኞች ግንቦት ሰባት February 11/2017 ከ 2pm ጀምሮ ይጠብቆታል።

በዝግጅቱ ላይ የድርጅታችን ከፍተኛ አመራር * አቶ ደባሱ መሰሉ* በአካል የሚገኙ ሲሆን የንቅናቄያችን ሊቀመንበር *ፕሮፌሰር ብርሐኑ ነጋ* ከኤርትራ በረሐ በስካይፕ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው አጠቃላይ የትግል እንቅስቃሴ ሰፊ ማብራሪያ ይሰጣሉ በዚህ ስብሰባ ላይ የወያኔን ስርዓት ለማስወገድ እየተደረገ ያለውን ትግል እና ተዛማጅ የሆኑ ማናቸውም ጥያቄዎች እና ሐሳቦች የሚስተናገዱበት መድረክ ሲሆን በቦታው ተገኝተው ጥያቄዎን እና ሐሳቦትን እንዲያካፍሉ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።
ይህን ታሪካዊና ወቅታዊ ዝግጅት ለመሳተፍ ወገናዊ ግዴታዎን ይወጡ ዘንድ ስናሳውቅ በዕለቱ ወደ ስብሰባው ቦታ ለመግባት ምንም አይነት የመግብያ ክፍያ እንደሌለው ስናሳውቅ በትህትና ነው።
የስብሰባ አድራሻ በቅርቡ የምንገለፅ ሲሆን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 4796816160 /4746240132 ይደውሉ
ክብር በየዕለቱ የህይወት ዋጋ እየከፈሉ ላሉ አርበኛ ታጋዮች !!!
ድል ለአርበኞቻችን።
የኖርዌይ አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!!!!!

No comments:

Post a Comment